Logo
Getu Temesgen
🧠 የ2 ዓመት ስቃይ በ4 ሰዓት ኦፕራሲዮን ተቀረፈ!
#ethiopia | በአገው ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል የተመዘገበ አስደናቂ የኒውሮሰርጀሪ (የጭንቅላት ቀዶ ህክምና) ስኬት
​የጭንቅላት ዕጢ የሚጥል በሽታ (Epilepsy) ሊያመጣ እንደሚችል ያውቃሉ?

​ለ2 ዓመታት ያህል በሚጥል በሽታ ሲሰቃዩ የቆዩት የ45 ዓመት ታካሚ፤ ህመማቸው ከመድኃኒት ቁጥጥር ውጭ ሆኖ እጅና እግራቸው ሽባ እስከመሆን እንዲሁም የፊት መጣመም ደርሶባቸው ነበር። በራሳቸው መመገብ እስኪያቅታቸው ድረስ የተሰቃዩት እኚህ ታካሚ ወደ ሆስፒታላችን መጡ።

​ምርመራና መፍትሔ:

በሆስፒታላችን በተደረገላቸው የሲቲ ስካን (CT Scan) ምርመራ በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት ትልቅ የጭንቅላት ዕጢ እንዳለባቸው ተረጋገጠ።

​የሆስፒታላችን የኒውሮሰርጀሪ ባለሙያዎች፣ ከሰመመን (Anesthesia) ባለሙያዎች እና ከኦፕራሲዮን ክፍል ነርሶች ጋር በመሆን ባደረጉት የ4 ሰዓት ርብርብ ዕጢውን ሙሉ በሙሉ ማውጣት ተችሏል።

​ውጤት:

በሽባነት ተይዘው የመጡት ታካሚ፤ ከቀዶ ህክምናው በኋላ በ3ኛው ቀን እያወሩ እና በእግራቸው እየተራመዱ ወደ ቤታቸው ገብተዋል።

​መልዕክት:

የሚጥል በሽታ፣ የሰውነት መዛል ወይም የፊት መጣመም ምልክቶች ሲያዩ ቶሎ ወደ ህክምና ተቋም ይሂዱ።

​ለዚህ ውስብስብ ህክምና ስኬት የለፉትን የህክምና ቡድን አባላት ከልብ እናመሰግናለን! 🙏

​አገው ምድር ጠቅላላ ሆስፒታል
የጤንነትዎ ቋሚ ካፒታል

📍 እንጅባራ፣ ኢትዮጵያ

​#neurosurgery #braintumor #successstory #agewmidirhospital #injibara #ethiopia #healthhero

5 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.