Logo
SeledaPost
ልዩ መለያ ኮድ የሌለው ነባሩ የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝ ከነገ ጥር 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ሥራ ላይ እንደማይውል ገቢዎች ሚኒስቴር አሳውቋል።

ሚኒስቴሩ " የታክስ ማጭበርበርን ለመከላከል ልዩ መለያ ኮድ (QR Cod) ያለበት የማንዋል ደረሰኝ ከባለፈው ዓመት ታሕሣሥ ወር ጀምሮ ወደ ሥራ ገብቷል " ሲል አስታውሷል።

ነባሩ የእጅ በእጅ ሽያጭ ደረሰኝም ከነገ ጀምሮ ሥራ ላይ እንደማይውል አሳውቋል።

በዚህ መሰረትም ከነገ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ ልዩ መለያ ኮድ (Unique QR Code) ያለበት የማንዋል ደረሰኝ ብቻ ለአገልግሎት እንደሚውል ገልጿል፡፡

የሕትመት ጥያቄ አቅርበው የታተመላቸውን ደረሰኝ ያልወሰዱ ግብር ከፋዮች ደግሞ በሚከፍሉበት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ወይም በየታክስ ማዕከላቸው በመገኘት ደረሰኞቻቸውን እንዲረከቡ አሳስቧል።

በተመሳሳይ ግብር ከፋዮች እጃቸው ላይ የሚገኘውን የቀድሞ ደረሰኝ ለየታክስ ማዕከሎቻቸው በመመለስ የመልቀቂያ ሰነድ መውሰድ እንዳለባቸው አመልክቷል፡፡

መመሪያውን በማይተገብሩ አካላት ላይ ሚኒስቴሩ አስፈላጊውን ርምጃ እንደሚወስድም አስጠንቅቋል።
FMC

seledadotio
seledadotio
7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.