አሜሪካ ኒኮላስ ማዱሮን ለመያዝ ከ150 በላይ አውሮፕላኖችን ተጠቅማለች ተባለ
ለዚህ ዘመቻ የአሜሪካ ኃይሎች ለወራት ሲዘጋጁ የቆዩ ሲሆን የማዱሮን እንቅስቃሴዎች በሙሉ ያውቁ ነበር። ዛሬ ከሰአት በኋላ የአሜሪካ የጦር ኃይሎች የጋራ ኢታማዦር ሹም የሆኑት ዳን ኬይን፣ በኒኮላስ ማዱሮ እና ባለቤታቸው በቁጥጥር ስር መዋል የተጠናቀቀውን ኦፕሬሽን ዝርዝር መረጃ ሰጥተዋል።
ኬይን ንግግራቸውን የጀመሩት "ፍጹም ቁርጠኝነት" (Absolute Resolution) የተሰኘው ስትራቴጂ ለወራት የታቀደ መሆኑን በመጥቀስ ነው። በአንድ ወቅት ማዱሮ የት እንደሚኖር፣ የት እንደሚጓዝ እና የት እንደሚመገብ ጭምር ያውቁ እንደነበር ገልጸዋል።
እንዲሁም ምን ዓይነት ልብስ እንደሚለብስና የቤት እንስሳቶቹ እነማን እንደሆኑ ጭምር መረጃው ነበራቸው።
እንደ ወታደራዊ ባለስልጣኑ ገለጻ፣ በኦፕሬሽኑ ላይ ከ20 ጣቢያዎች የተነሱ ከ150 በላይ አውሮፕላኖች ተሳትፈዋል።
"ዋናው ቁልፍ ነገር፣" ሲሉ ተከራክረዋል፣ "በሲቪሎች ላይ ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት ለመቀነስ፣ ድንገተኛ ጥቃቱን ለማሳደግ እና ተከሳሾቹ ለፍትህ እንዲቀርቡ በአካላቸው ላይ የሚደርሰውን ጉዳት ለመቀነስ ትክክለኛውን ቀን መምረጥ ነበር።"
አክለውም "የአየር ሁኔታው አንዱ ምክንያት ነበር... ለሳምንታት የአሜሪካ ወንዶች እና ሴቶች ወደ ተግባር የሚመራቸውን ትክክለኛ ቅጽበት በትዕግስት ሲጠባበቁ ነበር። ትላንት ምሽት የአየር ሁኔታው ፈቀደ፦ ለአየር ኃይሉ አባላት መንገዱን ጠረገላቸው" ብለዋል።
ጨምረው ሲያስረዱ "በምስራቃዊ ሰዓት አቆጣጠር ከምሽቱ 4:46 ላይ ፕሬዝዳንት ትራምፕ ወታደራዊ ኃይሎች ወደፊት እንዲገሰግሱ አዘዙ። እርሳቸውም 'መልካም ዕድል፣ ከፈጣሪ ጋር ሂዱ' አሉን" ብለዋል።
"ይሄን የትራምፕን ቃላት ወታደራዊ ኃይሉ ሁሉ ሰምቷል። በሌሊቱ ክፍለ ጊዜ በምዕራብ ንፍቀ ክበብ ከሚገኙ 20 የተለያዩ የምድር እና የባህር ጣቢያዎች አውሮፕላኖች ተነስተዋል፤ ከ150 በላይ አውሮፕላኖች፣ የስለላ ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች እና ሄሊኮፕተሮች በአየር ላይ ነበሩ" ብለዋል።
በዚህ ዘመቻ ውስጥ የተሳተፈው ትንሹ አባል የ20 ዓመት ወጣት ሲሆን፣ ትልቁ ደግሞ 49 ዓመታቸው እንደሆነ ገልጸዋል።
"ምሽት ሲሆን ሄሊኮፕተሮቻችን የህግ አስከባሪ መኮንኖችን ያካተቱ የጠለፋ (extraction) ኃይሎችን ይዘው ተነሱ፤ ከባህር ወለል በላይ በላይ በ100 ጫማ ከፍታ ላይ መብረር ጀመሩ። የቬንዙዌላ የባህር ዳርቻዎች ላይ ሲደርሱ ዩናይትድ ስቴትስ መንገድ ለመፍጠር የስለላ መረጃዎችን በቅደም ተከተል መጠቀም ጀመረች። እነዚያ ኃይሎች ከባህር ኃይል፣ ከአየር ኃይል እና ከብሔራዊ ጥበቃ በመጡ ሌሎች አውሮፕላኖች ጥበቃ ይደረግላቸው ነበር" ሲሉ አብራርተዋል።
"በካራካስ ምሽት ሲሆን የቬንዙዌላን የአየር መከላከያ ስርዓት የማፍረስ እና ከጥቅም ውጭ የማድረግ ዘመቻ ተጀመረ። ይህም የሄሊኮፕተሮችን ደህንነቱ የተጠበቀ ጉዞ ለማረጋገጥ ጥቅም ላይ የዋሉ መሳሪያዎችን ይጨምራል" ብለዋል።
"የሄሊኮፕተር ኃይሉ በዝቅተኛ ከፍታ ወደ ኢላማው ሲገባ፣ ማዱሮ ባለበት ቦታ ላይ በምስራቃዊ ሰዓት አቆጣጠር ከሌሊቱ 7:01 (በካራካስ ሰዓት አቆጣጠር 8:01) ደረስን። ወታደራዊ ኃይሎቹ ማዱሮ ወዳለበት ቦታ ደርሰው የምድር ኃይሎቻችን ተከሳሾቹን በቁጥጥር ስር በሚያውሉበት ወቅት ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ አካባቢውን ለይተው መያዝ ችለዋል" ብለዋል።
"ከአውሮፕላኖቻችን አንዱ ተመትቶ ነበር፣ ነገር ግን መብረር የሚችልበት ሁኔታ ላይ ነበር" ሲሉም ተናግረዋል።
"ተከሳሾቹ ማዱሮ እና ባለቤቱ እጃቸውን የሰጡ ሲሆን፣ በዩኤስ ኃይሎች ድጋፍ በፍትህ ሚኒስቴር ቁጥጥር ስር በከፍተኛ ጥንቃቄ እና ሙያዊ ብቃት ውለዋል" ሲሉ አክለዋል።
መኮንኑ ሲያጠቃልሉ "ኃይሎቹ ከሌሊቱ 9:29 ላይ ከተከሳሾቹ ጋር ባህር ላይ ነበሩ። ማዱሮም ሆኑ ባለቤታቸው 'አዮ ጂማ' በተሰኘችው መርከብ ላይ ተሳፍረዋል" ብለዋል።

5 months ago