''የዱባዩ ንጉሥ መርከብ ሸለሙኝ ''
ሰሞነኛ
#ethiopia | ከጥቂት አመታት በፊት ዱባይ ላይ በተደረገ ያለም አቀፍ የስነጽሁፍ ፌስቲቫል ላይ አንድ ግጥም አነበብሁ፤ የዱባዩ ልኡል በግጥሜ እጅግ ስለተደመሙ አልሩሚ የተባለ መርከብ ብድግ አርገው ሸለሙኝ፤ ችግሩ መርከቡ ከዱባይ ተነስቶ ቀበና እንዴት ይደርሳል የሚለው ነበር፤ ሲጀመር የባህር በር ስለሌለን በባህር መስኮት በኩል እንደምንም እንዲገባ ተደረገ ፤ ከዚያ ጣናነሽ በተጉዋጉዋዘችበት መኪና ተጭኖ ሲመጣ ከተራራ ጋር ሲጋጭ ከዛፍ ጋር ሲላተም፤ ከመብራት ምሶሶ ጋር ሲኮራኮም በየአቅጣጫው ተሸራርፎ ተቦደድሶ ቀበና ሲደርስ ባጃጅ ሆኖ ቁጭ አለ ፤
እኔም ባለው መጽናናት ነው ብየ በማንጎራጎር ውስጡ ገብቼ ፎቶ ተነሳሁ፤ አሁን ያንን ፎቶ ሰርሰረው በማውጣት አጋርተው የመኪና እናዋጣለት የሚሉ ሰዎች ተነስተዋል፤ ያሳዝናል! እኔ ግን ከርግማን በሁዋላ ስድስት እግሩን እንደተነጠቀው አጅሬ በደረቴ እሳባታለሁ እንጂ የመዋጮ መኪና አልቀበልም፤
በነገራችን ላይ፥ በቀደም አንድ ተዋናይ አምሽቶ ለመግባት ሲሞክር አከራዩ “ከምሽቱአራት ሰአት በሁዋላ የግቢ በር አንከፍትም “ብለው ሲከለክሉት የሚየሳይ ቪድዮ ወጥቶ ተናኘ፤ ቫይራል ሆነ ማለቴ ነው! አዶናይ የተባለው ቸር ቲክታከርም ይህንን ሲያይ “ ለአርቲስቱ አዋጥተን ቤት እንግዛለት የሚል ዘመቻ ጀመረ፤
ይሄንን የሰማው አብሮ -አደግ ገዋደኛው ምን አለ?
“ግዴለም፤ ገንዘቡን ለኔ ከሰጣችሁኝ እኔ መክሬ በጊዜ እንዲገባ አደርገዋለሁ”
ለማንኛውም፥ ዛሬ ምሽት የተወዳጆቹ ድምጻውያን የሳምቮድ እና የናቲ ኮንሰርት በሚሊኒየም ይካሄዳል ፤ የዘጠና ሙዚቃ አፍቃሪዎች ተገኝታችሁ እንድትቀውጡ ተጋብዛችሁዋል፤ ሳምቮድን የምትወዱ ወይዛዝርት እድላችሁን የምትሞክሩበት ቀን ዛሬ ነው ፤ ከሳምቮድ ትንሽ ጠና ፥ ያለ የምትፈልጉ ካላችሁ እኔም በቦታው እገኛለሁ !
በእውቀቱ ስዩም

7 months ago