ዩኒቨርስ የህክምና ማዕከል ተመረቀ!
#fastmereja I ዩኒቨርስ የህክምና ማዕከል ተደራሽነቱን በማስፋት የጤና ሚኒስቴር ሚንስትር ዴኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች በተገኙበት በዛሬዉ እለት ተመርቋል።
ላለፉት አመታት በውስጥ ደዌ ህክምና እስፔሻሊቲ ክሊኒክ ማህበረሰቡን ሲያገለግል የነበረው ዩኒቨርስ ክሊኒክ አሁን ተደራሽነቱን ለማስፋት ቀድሞ የነበሩ ስመጥር እስፔሻሊስት ሃኪሞች በተጨማሪ ሌሎች በሞያው ጥርሳቸውን የነቀሉ እስፔሻሊስት ሃኪሞች እና ዘመናዊ የህክምና መሳሪያዎችን በመጨመር የአገልግሎት አድማሱን በማስፋት ወደ ዩኒቨርስ ህክምና ማዕከል አድጎ መከፈቱን ነዉ የተገለፀዉ።
ዩኒቨርስ የህክምና ማዕከል ከፍተኛ ቴክኖሎጂን የሚጠይቁ እንዲሁም ጥራቱን የጠበቁ ህክምናዎችን ከብቁ ባለሙያዎች ጋር በመያዝ የ24 ሰዓት አገልግሎት ለመስጠት ዝግጅት አጠናቆ ወደ ስራ ገብቷል።
ድርጅቱ ብዙ የህክምና ምርመራዎችንና አገልግሎት ማድረግ እንደሚችል ገልፀዉ አገልግሎቱን ይበልጥ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ለማድረግ ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁንም እንዲሁም በቀጣይ ሁለት አመታት ተደራሽነቱን አስፍቶ ወደ ሆስፒታል ለማሳደግ እንደታቀደ የዩኒቨርስ ህክምና ማዕከል መስራች እና ባለቤት ዶ/ር ጉደታ ይመና ገልፀዋል።
ይህ የህክምና ማዕከል በቋሚነት ለ40 ሰዎች የስራ ዕድል እንደከፈተም ተገልፆ የደም ልገሳ መርኃ ግብርም ተከናዉኗል።

6 months ago