Logo
Getu Temesgen
የ60 ሚሊዮን ብር ሎተሪ ዕጣ ሊወጣ 30 ቀናት ብቻ ቀሩት

📍የልዩ እድል ሎተሪ የአንደኛ ዕጣ 10 ሚሊየን ብር ሽልማቷን ተረከች
#ethiopia | በሀገራችን የሎተሪ ሽልማት ታሪክ ትልቁና በዲጂታል ብቻ ገበያ ላይ የዋለው የ60 ሚሊዮን ብር ሎተሪ ዕጣ ሊወጣ 30 ቀናት መቅረቱን
የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት እና ታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽንስ በጋራ በዛሬው እለት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አሳውቀዋል።

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ህብረተሰቡ ከአሁን በፊት በወረቀት ከሚያውቃቸውን ሎተሪዎች በተጨማሪ አዳዲስ የሎተሪ አይነቶችን በመጨመር ለገበያ እያቀረብ ሲሆን ካለፈው ጥቅምት ወር ጀምሮ ደግሞ በኢትዮጵያ የሎተሪ ታሪክ ከፍተኛው ሽልማት የሆነውና ለመጀመሪያ ጊዜ በዲጂታል መንገድ ብቻ የቀረበውን የ60 ሚሊዮን ብር ሎተሪ ዕጣ ሊወጣ 30 ቀናት ብቻ ቀርተውታል፡፡

የ60 ሚሊዮን ብር ሎተሪ እድሜያቸው ከ18 አመት በላይ የሆኑ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በየትኛውም አይነት ስልክ(በማንኛውም አይነት ተንቀሳቃሽ ስልክ)

*8989# ላይ ማንኛውንም አይነት ፊደል በመላክ እንዲሁም በቀጥታ ወደ 8989 በመደወል፣ በቴሌ ብር ሱፐር አፕ እና በድርጅቱ ኦፊሻል ድረ-ገፅ ethiolottery.et ላይ በመግባት ትኬቱን መቁረጥ ይቻላል።

የ60 ሚሊዮን ብር ሎተሪ ከጠቅላላ ሽያጭ ላይ ከ125 ሚሊዮን ብር በላይ ወይንም ከግማሽ በላይ ትኬቶች ለዕድለኞች ሽልማት የሚውሉ ሲሆን ከአጠቃላይ ሽያጩ ለሽልማት የሚወጣው የገንዘብ መጠን ወደ 53 በመቶ አድጓል።

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ሎተሪው ገበያ ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ ዋናውና ትልቁ ሽልማት እስከሚወጣበት ጥር 9 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የተለያዩ እድለኞች የተሸለሙ ሲሆን እስካሁንም ከ1200 በላይ እድለኞች በገንዘብና በአይነት የተለያዩ ሽልማቶችን ማሸነፍ ችለዋል።

የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት በ1954 ለመጀመሪያ ጊዜ እድለኞችን ሲሸልም በ50,000 ብር የጀመረ ሲሆን በዚህ አመት ሽልማቱን አሳድጎ የአንደኛውን ዕጣ ሽልማት 60 ሚሊዮን ብር አድርሷል፤ ይሄም በሃገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ የሚኖረውን አስተዋጽኦ ከፍ ያደርገዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የተቋሙ ድረ ገጽ ከተዋወቀበት ጊዜ ጀምሮ ከ1.5 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የዲጂታል ቤተሠብ የሆኑ ሲሆን ይሄም በአጭር ጊዜ የተገኘ ትልቅ ስኬት ነው ።

እለታዊ ሎተሪን በተመለከተ ሎተሪው በዲጂታል መንገድ በ5 ብር ብቻ በተጠቀሱት መንገዶች ሁሉ ገበያ ላይ የሚገኝ ሎተሪ ሲሆን በየ24 ሠአቱ የሚወጣና ደንበኞች እስከ 25,000 ብር አሸናፊ የሚሆኑበት ነው።

በዛሬው ፕሮግራም የመቂ ከተማ ነዋሪዋና በዲጅታል በቆረጠችው ትኬት አሸናፊ የሆነችው ወ/ሮ ስምረት ኢቲቻ ህዳር 1 ቀን 2018 ዓም የወጣው የልዩ እድል ሎተሪ የአንደኛ ዕጣ 10 ሚሊየን ብር ሽልማቷን ተረክባለች።

በመጨረሻም ይሄ የዲጂታል ሎተሪ እንዲሳካ በአጋርነት አብረውን እየሠሩ ያሉትን የኢትዮ ቴሌኮም ቴሌ ብር አገልግሎት፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣
አዋሽ ባንክ፣ የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ፣
ዳሽን ባንክ፣ አቢሲኒያ ባንክ፣ ዘረጋው ክላውድ አገልግሎት፣ ኤዲሲ ሪሰርችና ዴቨሎፕመንት እንዲሁም ሌሎች አጋሮች የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት እና ታምኮን ሶፍትዌር ሶሉሽንስ አመስግነዋል።

📷 ከበደ መክብብ

6 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.