Logo
Getu Temesgen
“ ሜዳ ላይ ማሸነፍ ሲያቅታችሁ በጓሮ በር አትሞክሩ “ዲሞክራቲክ ኮንጎ

“ አለም ዋንጫን የምትጫወተው በራስ መተማመን እንጂ በጠበቃ አይደለም “
#ethiopia | ዲሞክራቲክ ኮንጎ ናይጄሪያ ለፊፋ ቅሬታ ማስገባቷ የሜዳ ላይ ሽንፈትን በጠበቃ ለማሸነፍ የተደረገ ሙከራ ስትል አጣጥላዋለች።

የናይጄሪያ ብሔራዊ ቡድን በ ዲሞክራቲክ ኮንጎ በተሸነፈበት የአለም ዋንጫ ጥሎ ማለፍ ፍፃሜ ጨዋታ ዙሪያ ለፊፋ ቅሬታ አስገብቷል።

ናይጄሪያ ቅሬታውን ያስገባችው ዲሞክራቲክ ኮንጎ ያልተገባ ተጨዋች አሮን ዋን ቢሳካን አሳልፋለች በማለት ነበር።

ናይጄሪያ በተጨማሪም ኮንጎ ጥምር ዜግነት እንደማትፈቅድ ገልፃ ዋን ቢሳካ የእንግሊዝ ፓስፖርት እንዳለው አሳውቃለች።

እንዲሁም ሌሎች ተጨዋቾች የቤልጅየም እና ኔዘርላንድ ፓስፖርት እያላቸው በጨዋታው ተሰልፈዋል በማለት ከሳለች።

ስለ ጉዳዩ ምላሽ የሰጡት የ ዲሞክራቲክ ኮንጎ እግርኳስ ዳይሬክተር ሄሪታ ኢሉንጋ “ ጉዳዩ ያ ከሆነ አያስኬድም አፍሪካ ዋንጫ ላይ ትኩረት እንድታደርጉ እመክራለሁ “ብለዋል።

“ ፊፋ ህጋዊ ዜግነት ሳይሆን ለማን መጫወት ትችላለህ የሚለውን የስፖርት ዜግነት ነው የሚያየው “ ሲሉ ሀላፊው ተናግረዋል።

አክለውም “ ሜዳ ላይ ማሸነፍ ካልቻላችሁ በጓሮ በር ለማሸነፍ አትሞክሩ ፤ አለም ዋንጫ በክብር እና በራስ መተማመን የምትጫወትበት እንጂ በጠበቃ ብልሀት አይደለም “ ብለዋል።
#ts #sports #gtmc

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.