Logo
Getu Temesgen
ዴምቤሌ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ተባለ
#ethiopia | የ 2025 የፊፋ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች በኳታር መዲና ዶሃ እየተደረገ በሚገኘው የአመቱ ምርጥ አሸናፊዎች ስነ-ስረዓት ላይ ይፋ ተደርጓል።

በዚህም መሰረት የፒኤስጂው የፊት መስመር ተሰላፊ ኡስማን ዴምቤሌ የ 2025 የአለም ምርጥ ተጨዋች በመባል መመረጥ ችሏል።

ፈረንሳዊው የፊት መስመር ተሰላፊ ኡስማን ዴምቤሌ የፊፋ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች ክብርን ለመጀመሪያ ጊዜ መቀዳጀት ችሏል።

ዴምቤሌ በአመቱ ውስጥ ምን አሳካ ?

- የፈረንሳይ ሊግ አሸናፊ

- የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ አሸናፊ

- የ ኮፕ ዴ ፍራንስ አሸናፊ

- የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የአመቱ ምርጥ ተጨዋች

- የባሎን ዶር አሸናፊ

በሴቶች ስፔናዊቷ የባርሴሎና የመሐል ሜዳ ተሰላፊ አይታና ቦንማቲ ማሸነፍ ችላለች።
#ts #sports #gtmc

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.