የግብፅ ሚዲያዎች በታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ጉዳይ ዜጎችን ዋሽተዋል - ግብጻዊ አክቲቪስት
#ethiopia | የግብጽ ሚዲያዎች ስለ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ አሳሳች መረጃ በማቅረብ ሕዝቡን ሲያሳስቱ ነበር አሉ ግብጻዊው አክቲቪስት ሃምዲ ሱሌይማን፡፡
ከፋና አረብኛ ፖድካስት ጋር ቆይታ ያደረጉት ሱሌይማን፥ ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በግብፅ እና ሱዳን ላይ ምንም አይነት ስጋት እንደሌለው ተናግረዋል።
ግድቡ በዋነኛነት የሀይድሮ ኤሌክትሪክ ኃይል ለማመንጨትና ኃይል ካመነጨ በኋላ ውሃው ተፈጥሯዊ ሂደቱን ጠብቆ ወደ ተፋሰስ ሀገራት የሚሄድ በመሆኑ ለግብጽም ሆነ ለሌሎች የተፋሰሱ ሀገራት ስጋት የለውም ነው ያሉት፡፡
ስለ ግድቡ መፍረስና ስለ ግብፅ የውሃ ደህንነት ስጋት የሚሰራጩ የስጋት መረጃዎች ትክክል እንዳልሆኑ ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ለሰላም፣ ለትብብርና ከግብፅ ጋር ጥሩ ግንኙነት ለመመስረት እውነተኛ ፍላጎት እንዳላት መረዳታቸውን ተናግረዋል፡፡
የግብጽ መንግሥት ሌሎች የአፍሪካ ሀገራት ሕዝቦችን የሚመለከትበት መንገድ ልክ እንዳልሆነም አስረድተዋል፡፡
ግብጻዊው አክቲቪስት ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ፕሮጀክትን ከኢትዮጵያ ይልቅ የአፍሪካ ፕሮጀክት አድርገው እንደሚመለከቱ አብራርተዋል፡፡
በዚህም የላይኛው ተፋሰስ ሀገራት ባላቸው የተፈጥሮ ሀብት ላይ የራሳቸውን ውሳኔ እንዲሰጡ ያደርጋል ነው ያሉት፡፡
በግብፅ የአስዋን ግድብ የኑቢያ ነዋሪዎችን እንደሚያፈናቅልና ለበሽታ እንደሚያጋልጥ ገልጸው፥ ግድቡ የግብፅን የኤሌክትሪክ ፍላጎት ማሟላት አለመቻሉን ጠቁመዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በመላው አፍሪካ አዎንታዊ ተጽዕኖ እንደሚኖረው ጠቅሰው፥ ኢትዮጵያ የባሕር በር በማግኘት የኢኮኖሚ ዕድገቷን ታጠናክራለች ነው ያሉት፡፡
የኢትዮጵያ መንግሥት በግብርና እና በመሠረተ ልማት ዘርፍ ልማትን ለማፋጠን የሚያደርገውን ከፍተኛ ጥረት መመልከታቸውንም ገልጸዋል። #fmc

6 months ago