Logo
Getu Temesgen
137 ቲሸርቶችን ደራርቦ ግማሽ ማራቶን የሮጠው ግለሰብ
#ethiopia | ዩፒአይ በዘገባው ግለሰቡን የክብረ ወሰን አዳኙ ብሎ ጠርቶታል። ይህንንም ለማድረግ ዴቪድ ራሽ በአይዳሆ ግማሽ ማራቶን ተካፍሏል።

ዴቪድ በድንቃድንቅ መዝገብ ስሙን ለማስፈር ካለው ጉጉት የተነሳ በአውሮፓውያኑ አቆጣጠር 2019 አንድ መቶ አስራ አንድ ቲሸርቶችን ደራርቦ በግማሽ ማራቶን ውድድር ተሳትፏል።

የድንቃድንቅ መዝገብም 'ይሄማ አዲስ ነገር ነው' ብሎ ድርጊቱን መዘገበለት። ይሁንና ከጥቂት ዓመታት በኃላ 127 ቲሸርቶችን በደራረበው ተሳታፊ ስሙን እና ክብሩን ተነጠቀ።

ዳግም ክብሩን በስሙ ለማፃፍም ዴቪድ ከፍተኛ ልምምድ አደረገ። በ2024 ወደ አይዳሆ ፖታቶ ግማሽ ማሮቶን ዳግም በመሳተፍ 114 ቲሸርቶችን እንደለበሰ አንገቱ ተጨማሪ ልብሶችን ማጥለቅ ባለመቻሉ እና ከደም ዝውውር ጋር በተያያዘ ባጋጠመው ችግር እቅዱን ማሳካት አልቻለም ነበር።

በዚህ ዓመት ግን ዴቪድ የተነጠቀውን ክብር ዳግም አስመልሷል። በአይዳሆ ግማሽ ማራቶን ላይ ተሳትፎ 137 ቲሸርቶችን በመልበስ ውድድሩን ሲያጠናቅቅ የድንቃድንቅ መዝገብ ደግሞ አዲስ ክብረ ወሰን በማለት መዝግቦለታል።

ዴቪድ 21 ኪሎ ሜትሩን ሲያጠናቅቅ 21.77 ኪሎ ግራም የሚመዝን ቲሸርት ተሸክሞ እንደሆነ ሳማ ቲቪ ዘግቧል።
#etventertainment

7 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.