Logo
FastMereja
De-Next-Ev የተሰኘ ዲፕሎማቲክ ባዛር ተዘጋጀ
#fastmereja I Elvezet international Events ከDeleopol Hotel እና Next Fasion Design ጋር በጋራ በመሆን De-Next-Ev የተሰኘ ዲፕሎማቲክ ባዛር ማዘጋጀታቸውን ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግሯል።

ለሶስት ተከታታይ ቀናት የሚቆይ በዓይነቱ ለየት ያለ ዲፕሎማትክ ባዛር ከህዳር 19 እስከ ህዳር 21/2018 ዓ.ም ድረስ በዲሊኦፖል ሆቴል እንደሚካሄድ ተገልጿል።

ባዛሩ ላይ የተለያዩ መስተንግዶች እንዲሁም በውስጡ ራሳቸውን የቻሉ ሌሎች ኢቨንቶች ያሉ ሲሆን፤ ዲፕሎማቶች፣ የተለያዩ የኤምባሲ ተወካዮች፣ የንግድ ተቋማት መሪዎች እና በተለያዩ ሙያ ላይ ያሉ እንግዶች ይገኛሉ።

የተለያዩ ተቋማትን ማቀራረብ እንዲሁም በስራቸው ጠንካራ የሆኑ ጀግና ሴቶችን ማበረታታት እና ለወደፊትም ለእንደዚህ አይነት ዓላማ ለሚሳተፉ ምቹ ሁኔታን መፍጠር ዓላማ ያደረገ መሆኑ ተነግሯል።

በባዛሩ የመዝናኛ እንዲሁም በከተማው ላይ እጅግ ተፈላጊና ተወዳጅ የሆኑ የተለያዩ ምርቶችን የያዙ ቬንደሮች የሚገኙበት ይሆናል ተብሏል።

በምሽት ፕሮግራም ላይ ከቀኑ የተለየ በአማራጭ የቀረቡ የተለያዩ የምግብ አይነቶችን እና መጠጦችን ይዘው የሚዝናኑበት የሙዚቃ ዝግጅት ወይም የጃዝ ምሽት እንደሚኖር ተገልጿል።

ህዳር 20/2018 ዓ.ም በዓይነቱ ለየት ያለ ዓመታዊ የሆነው በNext Fasion Design የተዘጋጀ AFFA Award ይካሄዳል።

ዝግጅቱ በአመት ሶስት ጊዜ ማለትም በአዲስ ዓመት፣ ገና እና የፋሲካ ሰሞንን ምክንያት በማድረግ በየጊዜው ለማዘጋጀት የታቀደ ሲሆን መግቢያ በነጻ ነው።
#ኹነት

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.