በአሁኑ ወቅት በደቡበ ኢትዮጵያ ከልል የተከሰተውን ሄሞራጅክ ፊቨር (Hemorragic Fever ) በሽታ አስመልክቶ ከጤና ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የተሰጠ ወቅታዊ መረጃ
የጤና ሚኒሰቴር ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት እና ከክልል ጤና ቢሮዎች ጋር በመተባበር የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎችን እንዳይከሰቱ የመከላከል እና ከተከሰቱም በአፋጣኝ የማረጋገጥና የተቀናጀ የቅኝትና የምላሽ ስራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
በዚህም መሰረት በደቡበ ኢትዮጵያ ክልል በጅንካ ከተማ የሄሞራጅከ ፊቨር (Viral Hemorragic Fever) በሽታ መከሰቱን እና የበሽታዉን ምንነት በማረጋገጥ ላይ መሆኑን አስቀድመን መግለፃችን ይታወቃል፡፡
በኢትዮጵያ ሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ብሄራዊ ሪፈረንስ ላብራቶሪ በተሰራው የዘረመል ምርመራ መሰረት የበሽታዉ መንስኤ ማርበርግ ቫይረስ (Marburg Virus) መሆኑን መለየት ተችሏል ። በዚህም የዘረመል ምርመራ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያ ውስጥ የተገኘዉ ቫይረስ ሌሎች ምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ላይ ከዚህ በፊት ከተከሰቱት ጋር ተመሳሳይ ዝርያ ያለዉ መሆኑ ታዉቋል።
በዛሬው እለትም አዲስ የበሽታውን ምልክት ያሳየ ወይም በቫይረሱ የተጠረጠረ ሰው ያልተገኘ ሲሆን፤ በአሁኑ ሰዓት የተለያዩ የሙያ ስብጥርያካተተ ከፍተኛ ፈጣን ምላሽ ሰጭ ቡድን ወደ ክልሉ በመላከ በሽታዉን የመከላከል እና የመቆጣጠር ስራዎች እየተሰሩ ይገኛሉ።ከነዚህም ውስጥ የማህበረሰብ አቀፍ የቅኝት ስራዎች፣ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ለይቶ ማከም፤ የማህበረሰብ ግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎች እና ከተጠረጠሩ ሰዎች ጋር ንክኪ ያላቸዉን ሰዎች የመለየት ስራዎች እየተከናወኑ ሲሆን በሃገር አቀፍ እንዲሁም በክልል ደረጃ የሕብረተሰብ ጤና አደጋዎች የክስተት አስተዳደር ስርዓት (Incident Management System) 14ሞ የፈጣን ምላሽ ስራዎችን በማስተባበር ላይ ይገኛል።
ስለበሽታው አዲስ እና ተጨማሪ መረጃዎች በሚኖሩበት ግዜ በጤና ሚንስቴር ይፋዊ ማህበራዊ ሚዲያ ገጾች ላይ የምናሳውቅ መሆኑን እየገለጽን መላዉ ሕብረተሰባችንና የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት በበሽታው ክስተት ሳይደናገጡ በሽታዉን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የሚከተሉትን ምከረ-ሃሳቦች በተረጋጋ መልኩ ተግባራዊ እንዲያደርጉ እናሳስባለን፡፡
➢ ከጤና ሚኒስቴር እና ከኢትዮጵያ የሕብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የሚተላለፉ መረጃዎችንና የጥንቃቄ መልዕከቶችን መከታተልና መተግበር፥
➢ የበሽታው ምልከት የሆኑትን በአፍ፣አፍንጫ እና ሌሎች የሰውነት ከፍሎች የመድማት፣ትኩሳት፣ማስቀመጥ እና ማስመለስ ምልከት ሲኖር ወደ ህክምና ተቋማት መሄድና በወቅቱ የላቦራቶሪ ምርመራ ማድረግ፣
➢ ምልክት ከታየበት ማንኛዉም ሰዉ ጋር ንክኪ በሚኖርበት ግዜ ራስን የመከላከያ ዘዴዎችን መጠቀም፣
➢ ሁልጊዜ እጅን በውሃና ሳሙና መታጠብ ወይም በሳኒታይዘር ማጽዳት፣
ማንኛውም ጤና ተቋም ለታካሚዎች ልየታ ልዩ ትኩርት በመስጠት የማርበርግ በሽታ (Marburg viral disease) መሰል በሸታ መለየት፣ ማከም እና በአፋጣኝ ሪፖርት ማድረግ ያስፈልጋል።
ለተጨማሪ መረጃ ወደ 8335 እና 952 ነጻ የስልክ መስመሮች በመደወል ተጨማሪ መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል፡፡
ዶ/ር መቅደስ ዳባ
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር
ህዳር 05/2018 ዓም
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

9 months ago