Logo
Getu Temesgen
ቤንጃሚን ሴስኮ በካሪንግተን ይቆያል
#ethopia | የማንችስተር ዩናይትዱ የፊት መስመር አጥቂ ቤንጃሚን ሴስኮ ወደ ብሔራዊ ቡድኑ እንደማያመራ ተገልጿል።

በሳምንቱ መጨረሻ ጉዳት ያጋጠመው ሴስኮ በብሔራዊ ቡድኖች ጨዋታ እረፍት ወቅት በካሪንግተን እንደሚቆይ ተነግሯል።

ማንችስተር ዩናይትዶች ቤንጃሚን ሴስኮ ያጋጠመው ጉዳት ከባድ ይሆናል የሚል እምነት #እንደሌላቸው ተጠቁሟል።

የስሎቬኒያ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ በሰጡት አስተያየት ከማንችስተር ዩናይትድ የደረሰን ምንም መልዕክት የለም ሲሉ ተናግረዋል።

አሰልጣኙ አክለውም የብሔራዊ ቡድናችን የህክምና ቡድን ጉዳዩን እንዲመለከተው እንፈልጋለን ብለዋል።
#ts #gtmc #sport

11 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.