የኢትዮጵያ ልዑካን ቡድን በተባበሩት መንግስታት የቱሪዝም ድርጅት 26ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተሳተፈ
#ethiopia | በቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር እንደገና አበበ የተመራው የአገራችን ልዑካን ቡድን እና በሳዑዲ አረቢያ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛ እና ባሙሉ ሥልጣን ክቡር አምባሳደር ዶ/ር ሙክታር ከድር በተባበሩት መንግስታት ቱሪዝም ድርጅት 26ኛው ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተሳትፏል።
ጉባኤው ከጥቅምት 28 እስከ ህዳር 2 ቀን 2018 በሪያድ፣ ሳዑዲ አረቢያ "AI-Powered Tourism: Redefining the Future" በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ሲሆን ፣በጉባኤው ከ160 አባል ሀገራት የተውጣጡ ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ከተለያዩ የኢንዱስትሪ እና የሲቪል ማህበረሰብ መሪዎችን ተገኝተዋል።
የጠቅላላ ጉባኤው አጃንዳ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘላቂ እና ሁሉን አቀፍ እድገትን እንዴት ማፋጠን እንደሚቻል ውይይቶችን በማካሄድ እንዲሁም በቱሪዝም ዘርፍ ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር በማለም የተዘጋጀ ነው።
በጉባኤው የኢትዮጵያ ልዑክ በአገራችን በከፍተኛ ትኩረት እየተሰራበት የሚገኘውን እና የኢኮኖሚ አንዱ ዋልታ የሆነውን የቱሪዝም ዘርፍ ይበልጥ ለማሳደግ ልምድ የሚቀስምበት እንደሚሆን ይጠበቃል።
በጉባኤው ላይ የተባበሩት መንግስታት የቱሪዝም ዋና ፀሐፊ ሆነው የተመረጡ የተባበሩት አረብ ኤሚሬትስ ዜግነት ያላቸው ሻይካ አል ኖዌይስ የተገኙ ሲሆን ተመረጯ በድርጅቱ በ50 ዓመታት ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያዋ ሴት ዋና ፀሐፊ ናቸው።
ተመረጯ በዓለም አቀፍ ቱሪዝም ልምድ ያካበቱ መሪ ሲሆኑ፣ ለተባበሩት መንግስታት የቱሪዝም ራዕይ በተለይም እንደ አፍሪካ ባሉ ክልሎች በቱሪዝም አማካኝነት ዘላቂነት፣ ዲጂታል ለውጥ እና ሁሉን አቀፍ የኢኮኖሚ ልማት ላይ እንደሚያተኩሩ ገልጸዋል።
ዋና ፀሐፊዋ ከጃንዋሪ 2026 ጀምሮ እስከ 2029 በኃላፊነት እንደሚያገለግሉ ይጠበቃል።
#un #visitethiopia #tourism

7 months ago