የገንዘብ ሚኒስቴር የገቢ ግብር (ማሻሻያ) አዋጅ ቁጥር 1395/2017 አፈጻጸም ላይ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት፣ በተለይ በአከፋፋይ ነጋዴዎች ላይ የሚሰላውን አማራጭ አነስተኛ ግብር በተመለከተ ከፍተኛ እፎይታ የሚሰጥ ማብራሪያ ሰጥቷል።
ይህ ውሳኔ ቀደም ሲል የንግዱን ማህበረሰብ አስጨንቆ የነበረውን የትርፍ ህዳግ (Profit Margin) ግዴታ የሚያነሳ በመሆኑ በነጋዴዎች ዘንድ በደስታ ተቀባይነትን አግኝቷል።
በሚኒስቴሩ ማብራሪያ መሰረት፣ የአከፋፋዮች አማራጭ አነስተኛ ግብር የሚሰላበት መንገድ ግልጽ ሆኗል።
በዚህ መሰረት ፤ ጅምላ ሻጭ/አከፋፋይ ከአምራቹ ወይም ከአስመጪው ጋር ባደረገው ውል የሚሸጥበት ዋጋ እና የሚያገኘው መቶኛ (ትርፍ ህዳግ) በግልጽ የተወሰነ ከሆነ፣ አማራጭ አነስተኛ ግብሩ የሚሰላው በጠቅላላ የሽያጭ ገቢው ላይ ሳይሆን፣ በውል ወይም በሕግ በተፈቀደለት የትርፍ መቶኛ ላይ ብቻ ይሆናል ተብሏል።
ይህ አዲስ አፈጻጸም የገቢዎች ሚኒስቴር በትንሹ 15 በመቶ ማትረፍ አለባችሁ በሚል ያስቀመጠው ግዴታ በንግዱ ላይ የፈጠረውን ጫና የሚያቃልል ነው።
ይሁንና፣ ይህንን ውሳኔ ለመጠቀም አከፋፋዩ የመሸጫ ዋጋ እና የትርፍ ህዳግ በውል መወሰኑን የሚያረጋግጥ ሕጋዊ ሰነድ ለግብር ባለስልጣናት ማቅረብ ይኖርበታል።
ይህን የገንዘብ ሚኒስቴር ማብራሪያ ተከትሎ ነጋዴዎች ለካፒታል ጋዜጣ በሰጡት አስተያየት፣ ውሳኔው የንግዱን እንቅስቃሴ የሚያነቃቃ እና ከገበያ እውነታ ጋር የሚጣጣም ፍትሃዊ እርምጃ እንደሆነ ተናግረዋል። viacapital
seledadotio

9 months ago