Logo
Getu Temesgen
#ቀይ_ባህር_ለኢትዮጵያ_ሀገራዊ_ጥቅም
#ethiopia | ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ (ዶ/ር) ቀይ ባህርን በተመለከተ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረቡት ሀሳብ የኢትዮጵያን ዘላቂ ህልውና የሚያረጋግጥ ሳይንሳዊና ኢኮኖሚያዊ እውነታ ነው። ይህን መሰረታዊ ሀቅ በተለያዩ መመዘኛዎች ለማሳየት እሞክራለሁ :-

የህዝብ ብዛት እና የኢኮኖሚ ግዴታ፦ኢትዮጵያ ከ130 ሚሊዮን በላይ ህዝብ ያላት በፍጥነት እያደገች ያለች ሀገር ናት።የዓለም አቀፉ የንግድና ልማት ኮንፈረንስ (UNCTAD) መረጃ እንደሚያሳየው፣ የባህር በር የሌላቸው ሀገራት (Landlocked Countries) ከባህር በር ካላቸው ሀገራት በአማካይ ሁለት እጥፍ የበለጠ የትራንስፖርት ወጪ ይሸከማሉ። ይህም የሀገሪቱን ምርት ተወዳዳሪነት በመቀነስ፣ የዋጋ ግሽበትን በማባባስ እና የኢኮኖሚ ዕድገትን ይገድባል። ለአንድ ትልቅ ኢኮኖሚ የባህር በር ወሳኝ መሠረታዊ መብት ነው።

ጂኦ-ፖለቲካዊ እና የንግድ ደህንነት፦የቀይ ባህር መስመር ለዓለም ንግድ ወሳኝ ስትራቴጂካዊ ቦታ ሲሆን፣ የኢትዮጵያ ንግድ ደህንነት ከሌሎች ሀገራት ወደቦች ጋር መያያዝ በፖለቲካዊ እና ሎጂስቲካዊ ውሳኔዎች ላይ ጥገኛ ያደርጋታል።የራሷን የባህር በር በሰላማዊ መንገድ ማግኘት የንግድ መስመሯን አደጋ የመከላከል እና የብሔራዊ ጥቅሟን የማስጠበቅ ጂኦ-ስትራቴጂካዊ አስፈላጊነት አለው።

የታሪክና የህግ እውነታ፦ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት፣ ኢትዮጵያ የባህር በርዋን በህጋዊና ተቋማዊ ውሳኔ አለማጣቷ፣ ለጉዳዩ ፍትሃዊ እና ዘላቂ መፍትሄ የመፈለግን የታሪክ ግዴታ ያሳያል። የኢትዮጵያ ጥያቄ የጦርነት ሳይሆን የጋራ ተጠቃሚነትና የሰላማዊ ድርድር ነው።

ኢትዮጵያ የባህር በር ፍላጎቷን በሰላማዊ፣ ህጋዊና ዲፕሎማሲያዊ መንገድ ሁሉን ስልት እና አቅም በማየት ተጠቃሚ በሚያደርግ መንገድ ማሳካት አለባት። ይህ የህልውና ጥያቄ ከፖለቲካ በላይ፣ የኢኮኖሚ ፍትህና የልማት መብት ጉዳይ ነው ።

የዚህ ዘመን ትውልድ( Politically Active Person )እንዲሆን እና ትናንት በተለያየ ፖለቲካዊ ምክንያት እና ሁኔታ ለውይይት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሳይቀር ለማሰብ የተገታን ጉዳይ እንደገና ለንግግር መነሻ እና የብሔራዊ የልማት አጀንዳ አድርጎ ማቅረብ ኢትዮጵያ በቀጣይነት እና በዘላቂነት ለማሳካት ከምትፈልጋቸው የልማት ትልሞች መሰረት የሚጥል ነው ። የዜጎች ህይወት እንዲሻሻል እና ለውጥ እንዲመጣ ከተፈለገ እንዲህ አይነት ጉዳዬችን በድፍረት ወደ ፖለቲካ መድረክ መምጣታቸው ሊደነቅ ይገባል ።
#ኢትዮጵያ #ሀገራዊ_ጥቅም #ቀይባህር #ሰላምናልማት

በሀብታሙ ደባሱ አዲሱ

9 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.