የ1993ቱ የመለስ ዜናዊ አባባል ለዛሬም ይሰራል?
------
ዛሬ የተሾሙት ባለስልጣን የፌስቡክ ሕዝባችን መነጋገሪያ ሆነዋል። ባለስልጣኑ መነጋገሪያ የሆኑት የተማሩት ትምህርት ከተሾሙበት መሥሪያ ቤት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙት የሌለው በመሆኑ ነው። እኒህ ወጣት ባለስልጣን በመጀመሪያ ዲግሪም ሆነ በሁለተኛ ዲግሪው የሰለጠኑት food and nutrition በሚባል discipline መሆኑን ብዙዎች መስክረዋል። ዛሬ የተሾሙት ግን "የኒውክለር ኃይል ኮሚሽን ኮሚሽነር" ተብለው ነው።
አቶ መለስ ዜናዊ በ1993 መጀመሪያ ላይ "የሚኒስትሮች ሹመት አሰጣጥ ከተማሩት ትምህርት ጋር አይዛመድም" የሚል ጥያቄ ሲቀርብላቸው "ሚኒስትሮች የሚሾሙት በፖለቲካ አስፈጻሚነት ነው። ፖለቲካችንን እስካስፈጸመ ድረስ መሃይምም ልንሾም እንችላለን" በማለት በጣም ያስገመታቸውንና ብዙ ተቃውሞ ያስነሳባቸውን ምላሽ ሰጥተው ነበር።
ዛሬ የተሾሙት ባለስልጣን የተማሩት ትምህርት ከኒውክለር ሳይንስ ጋር ምንም ተዛምዶ የሌለው መሆኑ ሲታይ "ሹመቱ ለፖለቲካ ታማኝነት የተሰጠ ነው እንዴ?" የሚል ጥያቄ ያጭራል።
ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ድሮ የተሰሩ ስህተቶችን ባይደግሙ ጥሩ ነው ባይ ነኝ። በኒውክለር ሳይንስ፣ በኒውክለር ኢንጂነሪንግ፣ በኒውክለር ፊዚክስ፣ በአቶሚክ ፊዚክስ፣ በራዲዮ ኢንጂነሪንግ (rays engineering) ወዘተ የሰለጠኑ ኢትዮጵያዊያን ሞልተዋል። እነርሱን ካሉበት አፈላልጎ በቦታው መሾም እየተቻለ በጣም sensitive እና secretive በሆነ ቦታ ላይ ስለምግብ እና nutrition ያጠና ሰው ማስቀመጥ በሕዝቡ ዘንድ የማይገባ ስሜትና ውጥረት ሊፈጥር ይችላል።
ስለዚህ ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስህተታቸውን ቢያርሙ የተሻለ ነው ብለን እናምናለን።
አፈንዲ ሙተቂ

10 months ago