ሙሴ አሥርቱን ትእዛዛት የተቀበለበት ስፍራ !
ትራምፕን የምታስተናግደዉ የቀይባህር ዉብ ከተማ ሻርም ኤል ሼክ ግብፅ !
እነሆ ሃማስ እና እስራኤል ከአመታት አዉዳሚ መተላለቅ በኋላ ወደ አይቀሬው ድርድር መጥተው ስምምነት ፈፅመዋል ። ይህን ታሪካዊ ሁነት ያስተናገደችው ደግሞ አፍሪካዊቷ ሀገር ግብፅ ሻርም ኤል ሼክ ከተማ ናት ።
የሁለቱን ስምምነት ተከትሎም የአፍሪካን ምድር ለመርገጥ ፍላጎት እንደሌላቸዉ ሲነገሩ የሚደመጡት ትራምፕ የጋዛ የሰላም ስምምነት ዋስትና ሰጪዎች ጋር በፊርማ ስነ ስርዓት ላይ ለመሳተፍ በቀይ ባህር ዳርቻዋ ሻርም ኤል ሼክ ከተማ ለመገኘት ቀጠሮ ይዘዋል ።
ኧረ ለመሆኑ ይህቺ ከተማ ይህን ታሪካዊ ሂደት ለመከወን እንዴት ተመራጭ ሆነች ማለታችን አይቀርም ። እኛም ለመረጃ ያህል ጥቂት ስለከተማዋ ልታጫዉታችሁ ወድደናል አብራችሁ ዝለቁ ።
ውበት በሚያረብባት የውቧን ሻርም ኤል ሼክ ጎዳናዎች ይዘው ግራ ቀኟን እየቃኙ በእግርዎ ዞር ዞር ቢሉ በሚያዩት ነገር ሁሉ መደመምዎ አይቀሬ ነው። እፁብ ድንቅ ሕንፃዎቿ፣የቅንጦት ሪዞርቶቿ ፣ አውራ ጎዳናዎቿ፣ ውብ ዛፎች እና አበቦች ጥንታዊ ገበያዎች እና ወርቃማ መስጊዶች ከቀይ ባህር ነፋሻማ አየር ጋር ተባብረው የሚረጩት የውበት ቃና ያለማጋነን መቼም አይረሴ ሆነው በህሊናችሁ ውስጥ ታትመው ይቀራሉ።
በሲና ባሕረ ገብ መሬት ደቡብ ምስራቅ የባህር ዳርቻ ላይ ጨዋማዉን የቀይ ባህር ተንተርሳ በምትገኘዉ የመዝናኛ ከተማ በእግር እየተዟዟሩ ከተማዋን ሲጎበኙ መንገዱ ዳር ለከተማው ውበት ከሆኑት አንዱን የሻርም ኤል ሼክ የድሮ ከተማ መሀል ላይ የቆመው ግርማ ሞገስ ያለው የአል ሰሀባ መስጊድ አስደናቂ ሥነ ሕንፃ ተገርመው ሳይጨርሱ ከባህር ዳርቻዎች እና የቱሪስት አካባቢዎች ባሻገር ባለዉ በቅመማ ቅመም ሽታዎች፣ ጌጣጌጥ የእደ ጥበብ ዉጤቶች የሚገበይበትን በእጅ የተሰሩ መብራቶች ያጌጠዉን በከተማው አሮጌ ገበያ ፍፁም ባህላዊ ይዘት ይደመማሉ።
በዚህ ግርምት ላይ እያሉ ከፊት ለፊት በፕላኔታችን ላይ ካሉት ምርጥ የመጥለቅያ መዳረሻዎች አንዱ የሆነዉን በቀይ ባህር ውስጥ ያለ የውሃ ውስጥ ገነት ያገኙታል ።
የቀይ ባህር ውሃ አስደናቂ የባህር ህይወት ካሻዎት ጠልቀዉ አልያም በጀልባ እየቀዘፉ ሃሴት ያደርጋሉ ።
ዘወር ሲሉ ደግሞ የሻርም ኤል ሼክ የመዝናኛ ህይወት ማዕከል ናት የሚባልላትን በነጭ-አሸዋ የባህር ዳርቻ እና በሚወዛወዙ የዘንባባ ዛፎች የተከበበችው ናአማ ቤይ ወደብ ያገኛሉ በቅንጡ ሪዞርቶች ሬስቶራንቶች፣ ካፌዎች እና የቅርስ መሸጫ መደብሮች የግብፅን ቆይታቸው አይረሴ ያደርጋል ።
ከወዲያ ደግም የሲና ባሕረ ገብ መሬት ከፍተኛ ታሪካዊ መዳረሻ፣ የሆነዉ የቅዱስ ካትሪን ገዳም በሲና ተራራ ሥር ተቀምጧል፣ በዚያም ሙሴ አሥርቱን ትእዛዛት እንደተቀበለ ይነገራል።
በዓለም ላይ ካሉት አንጋፋ ገዳማት አንዱ የሆነው ይህ የግሪክ ኦርቶዶክስ ትሩፋት የብሉይ ኪዳን ዝነኛ "የሚነድ ቁጥቋጦ" የሚገኝበት ቦታ ሲሆን በርካታ ክርስቲያን ምዕመናን ጉብኝት ከሚያደርጉት አበይት ነገሮች አንዱ የገዳሙ ቤተመጻሕፍት የተመረጡ የሃይማኖታዊ ሥዕሎችና ጥንታዊ የብራና ጽሑፎች ስብስብ የሚያሳይበት ሙዚየም ነው።
ከተማዋ ከቱሪስት መስህቧ በተጨማሪ በአረብ-እስራኤል ግጭት ላይ ያተኮሩ በርካታ አለም አቀፍ ስብሰባዎችን አስተናግዳለች። እነዚህ ክስተቶች የሻርም ኤል ሼክን ቦታ በካርታው ላይ እንደ አስፈላጊ የዲፕሎማሲያዊ መሰብሰቢያ ቦታ እንድትሆን አስችሏታል ።
እንደ ከተማዋ ታሪክ ከሆነ ከ1960ዎቹ በፊት ሻርም ኤል ሼክ በእንቅልፍ የተሞላ ጥቂት ጀብደኛ አሳ አጥማጆች ዉጭ የማይታወቅ ነበር
ከስዊዝ ቀውስ በኋላ ነዉ ሁሉም ነገር የተለወጠ።
እ.ኤ.አ. በ 1967 የስድስት ቀን ጦርነት እስራኤል ሻርም ኤል ሼክን ጨምሮ የሲና ባሕረ ገብ መሬትን ተቆጣጠረች እና እስከ 1982 ድረስ ተቆጣጥራለች ።በዚህ ጊዜ አካባቢው ቀደምት ልማት መንገዶችን እና መሰረታዊ መሰረተ ልማቶችን ጨምሮ ለወደፊት የቱሪስት መዳረሻነት መሠረት ጥሏል።
የካምፕ ዴቪድ ስምምነት እና የግብፅ-እስራኤል የሰላም ስምምነትን ተከትሎ ሻርም ኤል-ሼክ ወደ ግብፅ በሰላም ተመለሰ። በኋላም የበርካታ የሰላም ኮንፈረንስ እና የዲፕሎማሲያዊ ስብሰባዎች ተምሳሌታዊ ቦታ ሆና “የሰላም ከተማ” የሚል ቅጽል ስም አግኝታለች።

በ1980ዎቹ እና 1990ዎቹ የግብፅ መንግስት ቁጥጥርን ካገኘ በኋላ የሻርምን አቅም ተገንዝቦ
ኢንቨስትመንቶች በህንፃ ሪዞርቶች ፣ ዳይቭ ማእከላት እና የመጓጓዣ አውታሮችን በመገንባት ዛሬ ላይ የአለም ቱጃሮች ለመዝናናት የሚመርጡት የግብፅ ቱሪዝም የጀርባ አጥንት መሆን የቻለው ከተማዋ ለበርካታ ታዋቂ የመካከለኛው ምስራቅ ባለሃብቶች የሚጎርፉባት የቅንጦት ለበርካታ አለምአቀፍ የሰላም ኮንፈረንሶች ስብሰባባዎች የሚካሄዱባት ዉብ መዳረሻ አድርገዋታል ይህን የታዘበዉ ዩኔስኮም ሻርም ኤል ሼክ የሰላም ከተማ የሚል ልዩ እውቅና አግኝታበታለች ።
የኔታ ቲዩብ በታዴ የማመይ ልጀ

10 months ago