Logo
YenetaTube
በጭቁኑ የማዳጋስካር ህዝብ ላይ ቃታ አናስብም ! /መከላከያ /

እ.ኤ.አ. በ2009 በሀገሪቱ በተደረገ መፈንቅለ መንግስት ፕሬዚዳንት አንድሪ ራጆኤሊ ከብክበዉ ቤተመንግሥት ያስገቡት የስልጣናቸው መሰረት የነበሩት
የማዳጋስካር ወታደሮች አመፁን በመደገፍ በዋና ከተማው ከተሰበሰቡ ፀረ-መንግስት ተቃዋሚዎች ጋር መቀላቀላቸው ተነገረ።

በማዳጋስካር በውሃ እና በመብራት መቆራረጥ በተማረሩ ዜጎች መስከረም 25 ቀን የተቀሰቀሰውና በወጣቶች እየተመራ ከእለት ወደ እለት በፍጥነት እየሰፉ በሄደው ተቃዉሞና አመፅ ቅዳሜ ከሰአት በኋላ በዋና ከተማው ጎዳናዎች ላይ በተካሄደው ተቃውሞ
የመንግስቱ ምርጥ የተባሉት ካፕሳት ክፍል ወታደሮች ተቃውሞን ተቀላቅለዋል። ተብሏል

የፕሬዚዳንት አንድሪ ራጆኤሊናን አገዛዝ በመቃወም የተቃውሞ ሰልፎች እየጨመሩ በመጡበት ወቅት የማዳጋስካን ወታደሮች ትእዛዝን በመጣስ በሺዎች የሚቆጠሩ የመንግስት ተቃዋሚዎችን በዋና ከተማይቱ አንታናናሪቮ ባዘጋጁት አመፅ መቀላቀላቸው የተገለፀ ሲሆን ሰልፈኞቹ ከሬጅመንቱ ጋር በመሆን ሰልፍ የወጡ ሲሆን በህዝቡ ላይ ጥይት አንተኩስም ሲሉ ቀደም ብለው ተናግረው እንደነበር ተዘግቧል ።

ከዚህ ቀደም ብሎ በከተማዋ ወጣ ብሎ በሚገኝ የጦር ሰፈር ውስጥ በተደረገ ስብሰባ፣ በ2009 በራጆኤሊና መነሳት ውስጥ ትልቅ ሚና የተጫወተው የ CAPSAT ክፍል ውስጥ ያሉ ወታደሮች፣ የፕሬዚዳንቱን መልቀቅ ለሚጠይቁ ተቃዋሚዎች ያልተለመደ ህዝባዊ የአብሮነት ጥሪ አቅርበዋል።

በሶኒዬራና አውራጃ የሚገኘው የጦር ሰፈር ወታደሮች በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በተለጠፈው ቪዲዮ ላይ "ሀይልና ፣ ወታደር፣የህዝብ ጠባቂ እንጂ የወንበር ማስጠበቂያ አይደለም ።
ጄንዳርሮችን እና ፖሊሶችን ለለዉጥ እንተባበር እና ጓደኞቻችንን፣ ወንድሞቻችንን እና እህቶቻችንን ለመተኮስ ደሞዝ አንከፍልም" ብለዋል።

በተመሳሳይ በአውሮፕላን ማረፊያው የሚገኙ ወታደሮች "ሁሉም አውሮፕላኖች እንዳይነሱ ። የአለቆቻችሁን ትእዛዝ አትታዘዙ። እና በሌሎች ካምፖች ውስጥ ያሉ "ጓደኞቻችሁን እንዲተኩሱ ትእዛዝ እንዳይሰጡ"“በሮቹን ዝጋ እና መመሪያችንን ጠብቅ” ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል ።

ጥቅምት 11 ቀን 2025 ከሰአት በኋላ ከአንታናናሪቮ በስተደቡብ ከምትገኘው ሶኒየራና ከሚገኘው ካፕሳት ክፍል ወታደሮች ጋር በመሆን የታጠቁ ተሽከርካሪዎችን እየነዱ የማዳጋስካር ባንዲራ እያውለበለቡ መታየታቸውን የዘገቡት ሮይተርስ አልጀዚራ ሲኤንኤን የዜና ወኪሎች ናቸው ።

የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.