የአለም ምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ ለ780 ሺህ ስደተኞች የሚሰጠውን የምግብ ድጎማ ከ60% ወደ 40% ለመቀነስ ተገደደ
👉 ፕሮግራሙ 230 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ ካላገኘ በሚቀጥሉት ወራት እርዳታውን ያቋርጣል
የተባበሩት መንግስታት የዓለም ምግብ ፕሮግራም (WFP) ወሳኝ በሆነ የገንዘብ እጥረት ሳቢያ በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ 780,000 ስደተኞችን የምግብ ድጎማ ከ60 በመቶ ወደ 40 በመቶ ለመቀነስ መገደዱን አስታወቀ።
ይህ ቅነሳ በስደተኛ ካምፖች ውስጥ የረሃብና የተመጣጠነ ምግብ እጥረት አደጋን በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል።
ድርጅቱ በጥቅምት ወር በ27 ካምፖች ለሚኖሩ ስደተኞች የዕለት ምግብ ድጎማውን ለመቀነስ የተገደደ ሲሆን፣ ይህም ማለት እያንዳንዱ ሰው አሁን በቀን ከ1,000 ካሎሪ በታች የሆነ የምግብ እርዳታ እያገኘ ነው ሲል ለካፒታል በላከው መግለጫ አስታዉቋል።
የፕሮግራሙ እንዳስታወቀዉ የሁኔታውን ክብደት ሲገልጹ፣ "የማይቻል ምርጫ እያደረግን ነው" ብለዋል። በተጨማሪም፣ "እያንዳንዱ የምግብ ድጎማ ቅነሳ ማለት ይበልጥ የተራበ ህፃን፣ ምግብ የመዝለል ግዴታ የደረሰባት እናት፣ እና ወደ አደጋ ጠርዝ የተገፋ ቤተሰብ ማለት ነው" በማለት አደጋው አሁን እየተከሰተ መሆኑን አስጠንቅቋል።
ከሱዳንና ደቡብ ሱዳን ግጭት ሸሽተው የመጡ 70,000 አዲስ ስደተኞች ብቻ ከፍተኛ የሆነ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት ስላለባቸው ለቀጣዩ ስድስት ወራት ሙሉ ድጎማ ማግኘታቸውን እንደሚቀጥሉ ተገልጿል።
የአለም ምግብ ፕሮግራም ለቀጣዩ ስድስት ወራት የሰብዓዊ ዕርዳታ ሥራውን ለማስቀጠል በአስቸኳይ 230 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር የሚጠይቅ ጥሪ አቅርቧል። አፋጣኝ የገንዘብ ድጋፍ ካልተገኘ፣ ድርጅቱ በሚቀጥሉት ወራት ለሁሉም ስደተኞች የሚሰጠውን የምግብ እርዳታ ሙሉ በሙሉ ሊያቆም እንደሚችል አስታውቋል።
seledadotio

8 months ago