Logo
YenetaTube
ሰሜን ኮርያን እና ሩሲያን የሚለያይ ምድራዊ ሃይል የለም ! /ኪም ጆንግ ኡን/

የሰሜን ኮርያው ሁለንተናዊ መሪ ኪም ጆንግ ከሞስኮ ጋር ያላቸው ወዳጅነት ከብረት የጠነከረ በከፍታም በዝቅታም የማይናወጥ መሆኑን መናገራቸው ተሰማ ።

የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እንደተናገሩት ጥምረታቸው "ትላንትም ዛሬም ወደፊትም ሁልጊዜም የሚቀጥል ይሆናል" ሲሉ ፒዮንግያንግ እና ሞስኮ ሩሲያ ከዩክሬን ጋር እያደረገችዉ በሚገኘዉ ጦርነት ወታደራዊ ትብብርን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል ።

ኪም ይህን ያሉት የሩሲያውን መሪ በልደታቸው ቀን እንኳን ደስ ያላችሁ በማለት ለፑቲን በላኩት ደብዳቤ ነው ሲል የሰሜን ኮሪያ ማዕከላዊ የዜና አገልግሎት (KCNA) ዘግቧል።

"ታላቁን የድል ቀን የተቀበሉት የሁለቱ ሀገራት የትብብር ግንኙነት ወደ ፊት ወደፊት እንደሚቀጥል አልጠራጠርም ። በመካከላችን ላለው ሞቅ ያለ ወዳጅነት እና የቅርብ ወዳጃዊ ግንኙነት ምስጋና ይግባውና የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን ሁለንተናዊ እድገት በሃይል ለማስፋፋት እና ፍትሃዊ እና ባለብዙ-ፖላራይዝድ የአለም ስርአት እንዲፈጠር ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት አልጠራጠርም ሲል ኪም ለፑቲን ተናግረዋል ።
ካለፈው አመት ጥቅምት ወር ጀምሮ ሰሜን ኮሪያ 15,000 የሚጠጉ ወታደሮችን እና የጦር መሳሪያዎችን ለሩሲያ በመላክ የጦርነት ጥምረቷን እያሳየች ነዉ ሲል የደቡብ ኮሪያ የስለላ ድርጅት አስታውቋል።

በደብዳቤው ላይ ኪም ሩሲያ ብሄራዊ ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ የምታደርገውን “ፍትሃዊ ትግል” ሙሉ በሙሉ እንደሚደግፉ ገልፀው ሞስኮ ከዩክሬንና ከኔቶ ጋር የገባችበትን ጦርነት እንዲያሸንፉ እያገዙ ነዉ ሲል ዮንሃፕ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

ቀደም ብሎ በነሀሴ 13 የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከሩሲያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት ሁለቱ ሀገራት ወታደራዊ ትብብር እያሳደጉ በመሆናቸው ለሩሲያ ያላቸውን "ሙሉ ድጋፍ" ገልፀው ነበር። በማለት ከሰሞኑን የአዉሮጳ ህብረት አባለ ሀገራት ሞስኮን በኢኮኖሚ በአቅርቦት በወታደራዊ የበላይነት ለመዉሰድ የጀመሩትን ትብብር ለማክሸፍና አሸናፊ ለመሆን ኪም እና ፑቲን የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን ኬሲኤንኤ ዘግቧል።

የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.