Logo
SeledaPost
ለትውልዱ እሴት መሸርሸር ዋነኛው ምክንያት የትምህርት ጥራት መጓደል ነው”-  ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

በትውልዱ ውስጥ ለሚስተዋለው የእሴት መሸርሸር ዋነኛው ምክንያት የትምህርት ጥራት መጓደል መሆኑን የኢፌዲሪ ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ።

ፕሪዚዳንት ታዬ ትናንትና በ6ኛው የሁለቱ ምክር ቤቶች 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ለትውልዱ እሴት መሸርሸር ዋነኛው ምክንያት የትምህርት ጥራት መጓደል መሆኑን ተናግረዋል።

“በትውልዶች መካከል ለሚስተዋለው የእሴት መሸርሸር ዋነኛው መነሻ የትምህርት ጥራት ችግር መሆኑን መንግሥት ያምናል” ያሉት ፕሬዚኣንት ታዬ፤ በመሆኑም መንግሥት ባለፈው ዓመት ለትምህርት ጥራት ጉዳይ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል።

በዚህም የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ቀርጾ ተግባራዊ አድርጓል። “ትምህርት ለትውልድ” በሚል መሪ ሃሳብ ማሕበረሰቡን በማንቀሳቀስ የትምህርት ተደራሽነትን የማረጋገጥ ሥራ ተሠርቷል። ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ተማሪዎች በትምህርት ቤት ምገባ ሥራ በማቀፍ ከትምህርት ገበታ እንዳይቀሩ ተደርጓል።

በተለይም ከተማሪዎች ምገባ ጋር ተያይዞ የተከናወነው ጉልህ ተግባር በዓለም አቀፍ ተቋማት ጭምር እውቅና የተሰጠው መሆኑንም ፕሬዚዳንቱ በንግግራቸው አመላክተዋል።

seledadotio
seledadotio
10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.