Logo
YenetaTube
እንኳን ደስ አላችሁ !

ዶ/ር መንሱር ዑስማን ዶ/ር አሸናፊ አምሳሉ አለም አለኝ ከምትላቸው 4000 የቀዶ ህክምና ሀኪሞች መካከል ሆኑ ።

በጎንደር ዩኒቨርሲቲ የቀዶ ህክምና ሀኪሞች የሆኑት ዶ/ር መንሱር ዑስማን አጠቃላይ እና የኮሎሬክታል ሰርጀን እና ዶ/ር አሸናፊ አምሳሉ በአሜሪካ ዋና መቀመጫውን ያደረገው FACS (Fellow, American College of Surgeons) የተሰየመው በትምህርታቸው፣ በሥልጠናቸው፣ በሙያዊ ብቃታቸው፣ በቀዶ ሕክምና ብቃታቸው እና በሥነ ምግባራቸው ላይ ጥብቅ ግምገማ ላደረጉ የቀዶ ጥገና ሐኪሞች እዉቅና በመስጠት አባል የሚያደርገው (ኤፍኤሲኤስ) በአባልነት መቀላቀላቸው ተሰማ ።

ለሁለቱ በጎንደር ዩንቨርስቲ አሉ ለሚባሉ ዶክተሮች አባልነት የሰጠው ጄኔራል፣ ሄፓቶቢላይሪ እና የጣፊያ እና ላፓሮስኮፒክ የቀዶ ጥገና ሐኪም የአሜሪካ ኮሌጅ ኦፍ ሰርጀንስ (ኤፍኤሲኤስ) በአለም ላይ የስነ-ምግባር ብቃት እንዲሁም ሙያዊ ብቃታቸዉ የተመሰከረላቸው በአካባቢያዊ, ክልላዊ እና ብሔራዊ የቀዶ ጥገና ልዩ ማህበራት በአባልነት በማስተማር ፕሮግራሞች እና በሆስፒታል ኮሚቴዎች ውስጥ ተሳትፎ ያደረጉ በመለየት ለጥቂቶች ብቻ አባልነት የሚሰጥ ሲሆን ዶ/ር መንሱር ዑስማን አጠቃላይ እና የኮሎሬክታል ሰርጀን እና ዶ/ር አሸናፊ አምሳሉም በዓለም ላይ ትልቁ የቀዶ ጥገና ሐኪሞች ድርጅት በሆነዉና እስካሁን ድረስ ለ4,000 አለምአቀፋዊ ዶክተሮችን አባል ያደረገው ተቋም ተቀላቅለዋል ።

በጎንደር ዩንቨርስቲ ታሪክም ዶር. ኡስማን እና አምሳሉ ይህን በሙያው ላሉ ባለሙያዎች አስደናቂ ስኬት የሚታይ ክብር ማግኘት የቻሉ የመጀመርያዎቹ የቀዶ ህክምና ሀኪሞች አድርጓቸዋል ።

የኔታ ቲዩብ በታዴ የማመይ ልጅ

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.