Logo
YenetaTube
ክርስቲያኖች የምድራችን ተቅበዝባዥ ሁነዋል !/ የፔው የምርምር ማዕከል/

በዓለም አቀፍ ፍልሰት ውስጥ የክርስቲያኖች ቁጥር ከፍተኛውን ስፍራ እንደሚይዝ እና ከዓለም አቀፍ ስደተኞች ውስጥ ግማሽ ያህሉ ማለትም 47 በመቶው ክርስቲያኖች መሆናቸውን ተነገረ ።

እ.አ.አ. በ 2004 ዓ.ም. በዋሽንግተን ዲ.ሲ.ላይ የተመሰረተዉና ከዬትኛውም የፓርቲ አስተሳሰብ ነፃ የሆነ በማህበራዊ ጉዳዮች፣ በሕዝብ አስተያየት እንዲሁም በስነ-ሕዝብ ላይ ዓለምን የሚረዱ ጥናታዊ መረጃዎችን የሚሰጠዉ በአሜሪካ የሚገኘው የፔው የምርምር ማዕከል አዲስ ባዉጣዉ ጥናት
በኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች፣ ፖለቲካዊ አለመረጋጋትና ግጭቶች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ክርስቲያኖችን ወደ ሌላ በህጋዊና ህገወጥ መልኩ ወደ ሌሎች ሃገራት አዳዲስ እድሎችንና ደኅንነትን ለማግኘት ለስደት ይዳረጋሉ ። ብሏል

በአዲሱ የዚህ ተቋም ዘገባ ይፋ የተደረገው መረጃ ክርስቲያኖችን በስደት ከአንድ ስፍራ ወደ ሌላ ስፍራ ከሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ሃይማኖተኞች መካከል 47 በመቶ ገደማውን የሚሸፍን ትልቁ የሃይማኖት ቡድን እንደሆነ የገለጸ ሲሆን፥ ይህም በመነሻ እና በመድረሻ ሀገራት በሃይማኖታዊ ስነ-ሕዝብ ቁጥር ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ እንደሚያሳድር አመላክቷል።

እንደ መካከለኛው ምስራቅ ላቲን አሜሪካ፣ አውሮፓ እና ከሰሃራ በታች ካሉ ክርስቲያናን ከሚበዛባቸው ክልሎች የሚደረገው ፍልሰት ለዚህ ጥናት ውጤት ትልቁን አስተዋፅዖ እንዳደረገም ተገልጿል።

በዘገባው መሰረት ኢኮኖሚያዊ ሁኔታዎች፣የመደጋገፍና ህብረት መረዳዳት ባህል አለመዳበር ፖለቲካዊ አለመረጋጋትና ግጭቶች በሚሊዮን የሚቆጠሩ ክርስቲያኖችን ወደ ሌላ ሃገራት አዳዲስ እድሎችንና ደኅንነትን ለማግኘት ለስደት እንደሚያነሳሳቸው ጭምርም ተመላክቷል።

“ሰዎች በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ተለያዩ የዓለም አቀፍ ክፍሎች ይንቀሳቀሳሉ” የሚለው ጥናቱ፥ ከነዚህም ውስጥ ሥራ ለማግኘት፣ ለትምህርት፣ ወይም ከቤተሰብ አባላት ጋር ለመቀላቀል እንደሚሰደዱ በማብራራት፥ ነገር ግን ሃይማኖት እና ስደት ብዙ ጊዜ የተሳሰሩ ናቸው በማለትም ይገልፃል።

የክርስትያን ማህበረሰብ ፍልሰት በተለይም የእምነቱ መነሻ በሆነዉ ግጭት ካለባቸው እንደ መካከለኛው ምስራቅ ካሉ ክልሎች በ አይሁዶችና በሙስሊሞች በአይሁዳውያን ግጭትና ማህበራዊ መገለል መዳረጉን ጠቁሟል ።

በዘመኑ ዋና ዋና የሚባሉትን የክርስቲያን ማዕከላትንም በአጭር ጊዜ ውስጥ በመቆጣጠር የተደረጉ ታሪካዊ ሃደቶችን ያስታወሰዉ ዘገባዉ በ635 ደማስቆ በጂሃድ ሠራዊት እጅ ከወደቀች በኋላ አንፆኪያ በ636 ተያዘች፡፡ በ640 በሦርያ የነበሩት ክርስቲያኖች በአረብ ሙስሊሞች ምድራቸውን ተነጠቁ፡፡ በ641 ፋርስና ግብፅ ለጂሃድ ሠራዊት እጅ መስጠት ጀምሮ በአካባቢው ያሉ ክርስትያኖች ለፍልሰትና ግዞት ተዳርገዋል ብሏል ።

ብዙ ስደተኞች ከሃይማኖታዊ ጭቆና ለማምለጥ ወይም ተመሳሳይ ሃይማኖታዊ እምነት ካላቸው ሰዎች ጋር ለመኖር ሲሉ ይሰደዳሉ” የሚለው የፔው የምርምር ማዕከል ዘገባ፥ “ብዙውን ጊዜ ሰዎች ሲሰደዱ ሃይማኖታቸውን ይዘው ሲሆን፥ በጊዜ ሂደት አዲስ በተሰደዱበት ሃገር ባለው ሃይማኖታዊ አስተሳሰብ የመለወጥ ዕድላቸው ከፍተኛ ነው” ይላል ጥናቱ።

ይፋ የሆነው ጥናት ከዚህም በተጨማሪ “አንዳንድ ጊዜ ስደተኞች ያደጉበትን ሃይማኖት በመተው አብዛኛው ሰው የሚከተለውን የአዲሱ የስደት ሃገራቸውን ሃይማኖት ወይም ሌላ ሃይማኖት መከተል ይጀምራሉ፥ ካልሆነም ሃይማኖት-አልባ ይሆናሉ” ሲል አክሏል።

ይህ ፍልሰት በሁለቱም ማለትም በታሪካዊ ምክንያቶች እና በአንዳንድ ክልሎች ውስጥ ባሉ የክርስትያን ማህበረሰቦች በሚያጋጥሟቸው ወቅታዊ ፈተናዎች ተጽዕኖ ስለሚደረግባቸው ተብሏል።

ጥናቱ በተጨማሪም እንደሚያመለክተው ስደት ቀደም ሲል የሃይማኖት ውስንነቶች ወደ ነበረባቸው በተለያዩ የመዳረሻ አገሮች የሃይማኖት ብዝሃነት እንዲኖር በማድረግ፣ ብዙ ጊዜ አዳዲስ ሃይማኖታዊ ማህበረሰቦችን በማስተዋወቅ አስተዋጽዖ ያደርጋል በማለት ያትታል።

በጥናቱ መሰረት የሙስሊሞች ፍልሰት በዓለም አቀፍ ስደተኞች መካከል ሁለተኛው ትልቁ የሃይማኖት ቡድን ሲሆኑ፥ ከጠቅላላው የስደተኞች ቁጥር 29 በመቶውን እንደሚሸፍን ተጠቁሟል።

አይሁዶች ምንም እንኳን ቁጥራቸው በጣም አነስተኛ ቢሆንም፣ ከፍተኛ የመሰደድ እድል እንዳላቸው እና ከዓለም አቀፉ የአይሁድ ህዝብ ቁጥር 20 በመቶው አካባቢ ከትውልድ አገራቸው ውጭ ይኖራሉ ተብሏል ።

ለዘገባዉ በአሜሪካ የሚገኘው የፔው የምርምር ማዕከልን የአለምአቀፉ የክርስቲያን መረጃ ቋትን ተጠቅመናል ።

የኔታ ቲዩብ ዘጋቢ ፦ ታዴ የማመይ ልጅ

10 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.