በካናዳ የኢትዮጵያ ኤምባሲ በላቀ አገልግሎት አሰጣጥ ተሸለመ
#ethiopia | በካናዳ ኦቶዋ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የ 'World African Researchers, Engineers, Entrepreneurs and Scientists Award (WARESA) 2025 መድረክ ላይ መልካም አፈጻጸም ያስመዘገቡ አፍሪካውያን ተቋማት በሚሸለሙበት ካታጎሪ “Outstanding Embassy Service Award” ተሸላሚ ሆኗል።
ኤምባሲው ለሽልማቱ የተመረጠው ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን በስፋት በሚገኙባቸው የካናዳ ከተሞች በመገኘት አገልግሎትና ድጋፍ በመስጠት፣ ተደራሽነቱን ለማስፋት በሰራው መጠነ-ሰፊ ስራ እንደሆነ በመድረኩ ላይ ተገልጿል።
ክቡር አምባሳደር ቴዎድሮስ ግርማ በእለቱ ባስተላለፉት መልእክት፤ ኤምባሲው ተሸላሚ ሆኖ በመመረጡ የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ፤ እውቅናው መላውን የኤምባሲውን ዲፕሎማቶች ለተሻለ ስራ የሚያተጋ ነው ብለዋል።
በቀጣይም በካናዳ ነዋሪ የሆኑ ኢትዮጵዊያንና ትውልደ ኢትዮጵውያን ምሁራንን፣ የስራ ፈጣሪዎችንና ተማሪዎችን በማበረታታትና በመደገፍ፣ በአገር ቤት ካሉ ተቋማት ጋር በማስተሳሰር እውቀትና ችሎታቸውን ለአገር ልማት ለማዋል በትኩረት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
በካናዳ ከሚገኙ የጥናትና ምርምር ተቋማት ጋር በቅርበት በመስራትም ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የሚሰጠውን የስኮላርሺፕ የትምህርት እድልን ለማስፋት በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

8 months ago