Logo
Getu Temesgen
ዕጅ እና እግሩን ተጠቅሞ በመሮጥ የዓለም ክብረ ወሰን የሰበረው ጃፓናዊ
#ethiopia | የ22 ዓመቱ ጃፓናዊ ስፖርተኛ ራዩሴይ ዮኔ ዕጁ እና እግሩን ተጠቅሞ በፍጥነት መሮጥ በ100 ሜትር የጊነስ ወርልድ ሪከርድን አስመዝግቧል።

አትሌቱ ከዚህ ቀደም አሜሪካዊው ኮሊን ማክሉር ያስመዘገበውን 15.66 ሰከንድ በማሻሻል ርቀቱን በ14.55 ሰከንድ ማጠናቀቅ ችሏል።

ወጣቱ በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በነበረበት ወቅት አስተማሪው እንስሳት በአራት እግሮች እንደሚሮጡ ሲያስተምሩ ካዳመጠ በኋላ እሱም ለዚህ እንቅስቃሴ መነሳሳት እንደተፈጠረበት ተናግሯል።

ለውድድሩ ለመዘጋጀትም ውሾች፣ ድመቶች እና ጦጣዎች እንዴት እንደሚንቀሳቀሱ ማጥናቱን ይናገራል።

ወጣቱ ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ጠንክሬ እለማመዳለሁ፣ ይህ የስፖርት ዘርፍ በየትኛውም ቦታ ማሳደግ እፈልጋለሁ” ብሏል።

በሴራን ታደሰ
#worldrecord #athletics

8 months ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.