26 days ago
ኮንጎ ከፍተኛ ወታደራዊ በጀት በመመደብ ከአህጉሪቱ ቀዳሚ ሆናለች
#ethiopia | የአፍሪካ ሀገራት ወታደራዊ በጀት እንደ ጸጥታ ተግዳሮቶቻቸው ለጂኦፖሊቲካዊ ጉዳዮች ቅድሚያ የሚሰጧቸው ጉዳዮች እና እንደ የኢኮኖሚ አቅማቸው ይለያያል።
የወርልድ ባንክ ኦፕን ዳታ በ2026 ያወጣው ወታደራዊ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ኮንጎ ቀዳሚ ብትሆንም አብዛኛዎቹ የሰሜን አፍሪካ ሀገራት በወታደራዊ ወጪ ቀዳሚውን ስፍራ ይዘዋል።
የሰሃራ በታች ያሉ ሀገራትም በአህጉሪቱ የጸጥታ እቅድ ውስጥ ወሳኝ ሚና አላቸው።
በዚህም መሠረት በመሆኑ ዕድን ሀብቷ የምትታወቀው ኮንጎ ለወታደራዊ ወጪ በአመት 30 ቢሊዮን ዶላር ወጪ በማውጣት ከአህጉሪቱ ቀዳሚ ሆናለች።
የሰሜን አፍሪካዊቷ ሀገር አልጀርያ
ከ25 ቢሊዮን ዶላር በላይ በአህጉሪቱ ለወታደራዊ ወጪ በበመደቅ በሁለተኛ ስፍራ ላይ ትገኛለች።
አልጀርያ በአየር በመሬት እና በድንበሯ የጸጥታ ጉዳዮች ላይ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ በማፍሰስ ለሰፊው የበርሃ ድንበሯ ጥበቃና ለአሸባሪዎች መከላከል ስራዎች ቅድሚያ በመስጠት ላይ ትገኛለች።
ከአልጀርያ ጋር በድንበር ጉዳይ የምትወዛገበው ሞሮኮ 13.4 ቢሊዮን ዶላር በወታደራዊ ዘርፏ ላይ ወጪ ታደርጋለች።
የግብፅ ወታደራዊ በጀት በአፍሪካ ትልቅ ከሚባሉት አንዱ ሲሆን በአህጉር ደረጃም ሆነ በአለም አቀፍ ደረጃ በሰፊው ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ላይ የተሰማራ ልምድ ያለው ጦር ባለቤት ሆናለች።
በዚህም ግብጽ ለመከላከያ ዘርፏ 6.9 ቢሊዮን ዶላር ትመድባለች።
ከአህጉሪቱ ለመከላከያ ዘርፏ ከፍተኛ ወጪ የምታወጣው አምስተኛ ደረጃ ላይ የምትገኘው ናይጄርያ ናት።
ሀገሪቷ በየአመቱ 3.4 ቢሊዮን ዶላር ለመከላከያ ዘርፏ ትመድባለች።
እነዚህ ቁጥራዊ አሀዞች በ2026 የተሰበሰቡ መረጃዎች ሲሆኑ እንደ ሀገራቱ የኢኮኖሚ እድገት እና የጸጥታ ሁኔታ ሊቀያየሩ እንደሚችሉ ነው የተገለጸው።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #worldbankopendata #africamilitryexpenditure #congo #algeria #egypt #morocco

Comments