2 months ago
የአለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣና ጉባኤ ታዳሚዎች ጤናማ ህይወትን ለማበረታታት ያለመ የጋራ የእግር ጉዞ ማካሄዳቸው ተገለፀ
#ethiopia በአዲስ አበባ እየተካሄደ በሚገኘው 76ኛው የአለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ስብሰባ ላይ የተሳተፉ አካላት ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን ለመከላከልና ጤናማ የአኗኗር ዘይቤን ለማስፋፋት ያለመ የጋራ የእግር ጉዞ አድርገዋል።
ንግግርን ወደ ተግባር በሚል መሪ ቃል እየተካሄደ ያለው ይህ ጉዞ መነሻውን ከአድዋ ድል መታሰቢያ በማድረግ የመዲናዋን የእግረኛ መንገድ ተከተሎ መስቀል አደባባይ ላይ ፍጻሜውን ያደርጋል።
በዝግጅቱ ላይ የጤና ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባን ጨምሮ የእስያና የአፍሪካ ሀገራት የጤና ሚኒስትሮች፣ ከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች፣ የአለም ጤና ድርጅት አመራሮች፣ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን እና ሌሎች ታዋቂ አትሌቶች ተሳትፈዋል።
የጤና sector አመራሮቹ በህብረት ባደረጉት በዚህ ጉዞ የአካል እንቅስቃሴ እንደ ስኳር፣ የደም ግፊትና የልብ ህመም ያሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎችን በመከላከል ረገድ ያለውን ከፍተኛ አስተዋጽኦ በተግባር ለማሳየት አልመዋል።
በተጨማሪም ዝግጅቱ በጤና ፖሊሲዎች ላይ የተወሰኑ ውሳኔዎችን ወደ ተጨባጭ ተግባር ለመቀየርና በአህጉሪቱ ህዝቦች ዘንድ ጤናማ የአኗኗር ልምድን ለማጎልበት ያለመ መልእክት የሚያስተላልፍ ነው።
የአለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ቀጣናዊ ኮሚቴ 76ኛው ጉባኤ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ሲሆን፣ በአህጉሪቱ የጤና ስልቶችና በቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ መክሮ ውሳኔዎችን ያሳልፋል ተብሎ ይጠበቃል።
#who #afro76 #health #walkthetalk #healthylifestyles #noncommunicablediseases #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments