2 months ago
አርሲ ከተማ የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች ቮሊቦል ሻምፒዮና አሸናፊ ሆነ
#ethiopia | ከነሐሴ 10 ቀን ጀምሮ በአዲስ አበባ ትንሿ ስታዲየም በደመቀ ሁኔታ ሲካሄድ የቆየው የኢትዮጵያ ክልል ክለቦች የቮሊቦል ሻምፒዮና በዛሬው እለት ፍጻሜውን አግኝቷል።
ስድስት የክልል ክለቦች ዋንጫውን ለማንሳት ባደረጉት ብርቱ ፍልሚያ፣ የአርሲ ክለብ የ2018 ዓ.ም ውድድር አሸናፊ ለመሆን ችሏል። በፍጻሜው ጨዋታ አርሲ ከተማ አዴት ከተማን 3 ለ 1 በሆነ ውጤት በመርታት ነው የሻምፒዮንነት ዘውዱን የተቀዳጀው።
በዚህም መሰረት ውድድሩን ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁት አርሲ፣ አዴት ከተማ እና ስኬት ባንክ ያሳዩትን ድንቅ ብቃት ተከትሎ ወደ 2019 ዓ.ም የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፕሪሚየር ሊግ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል።
በመዝጊያ ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ስሜነህ በሴ (ዶ/ር)፤ ለአሸናፊዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ካስተላለፉ በኋላ የስፖርቱን የወደፊት ጉዞ አስመልከተው ጠንከር ያለ ሃሳብ አንስተዋል። ፕሬዚዳንቱ እንደገለጹት የክለቦች በየጊዜው መፍረስ ለቮሊቦል ስፖርት እድገት ዋነኛ ማነቆ እና ፈተና በመሆኑ ይህ ችግር ሊቀረፍ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ይህንኑ ችግር ለመቅረፍ እና ክለቦች ቀጣይነታቸውን ጠብቀው እንዲዘልቁ ለማስቻል ፌዴሬሽኑ የፋይናንስና የትጥቅ ድጋፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ዶክተር ስሜነህ አበክረው ገልጸዋል። አክለውም የተለያዩ ተቋማት ለስፖርቱ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራዎች በትኩረት እንደሚሰሩ በመጠቆም፣ የቮሊቦል ስፖርት በሀገሪቱ ተገቢውን ስፍራ እንዲያገኝ ጥሪ አቅርበዋል።
ጌትነት ተመስገን
📷 ከበደ መክብብ
#ethiopianvolleyball #ጌጡ #getu
#ethiopianvolleyballfederation
#ethiopianpremierleague #refereetraining
#ethiopiansports #volleyballethiopia

7 months ago
የቮሊቦል ባለውለታው ኢንስትራክተር አለማየሁ ሸዋታጠቅ መታሰቢያ ውድድር ተጠናቀቀ
#ethiopia | በኢትዮጵያ ቮሊቦል ስፖርት ታሪክ ውስጥ ጉልህ አሻራ ያሳረፉትና በዓለም አቀፍ ደረጃ ከ150 በላይ በሚሆኑ ሀገራት የአሰልጣኝነት ስልጠና የሰጡት የሲኒየር ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር አለማየሁ ሸዋታጠቅ መታሰቢያ ውድድር ዛሬ በደማቅ ሁኔታ ተጠናቋል።
ኢንስትራክተር አለማየሁ ሸዋታጠቅ ከዚህ ዓለም በሞት ከተለዩ ሦስት ዓመታት የሞላቸው ሲሆን፣ ይህንን የቀድሞ ውጤታማ ስፖርተኛና የዘርፉ ባለውለታ ለመዘከር ሲካሄድ የሰነበተው ውድድር ላለፈው አንድ ሳምንት በበርካታ ክለቦች መካከል ሲካሄድ ቆይቷል።
በኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን አዘጋጅነት ከመጋቢት 5 እሰከ መጋቢት 12 ቀን 2018 ዓ.ም ሲደረግ የነበረው ይህ ውድድር በዛሬው የፍጻሜ ጨዋታ በወንዶች መቻል ስፖርት ክለብ እንዲሁም በሴቶች ብሔራዊ አልኮል ስፖርት ክለብ የዋንጫ አሸናፊ መሆናቸውን
አረጋግጠዋል።
በመዝጊያ መርሐግብር ላይ በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር የስፖርት ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ ወይዘሮ አበባ አማረ ፣ በባህልና ስፖርት የስፖርት ማህበራት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ዳንኤል ዳኜ ፣ የመከላከያ መቻል ስፖርት ክለብ ስራ አስፈፃሚ ብርጋዲየር ጄኔራል ኑሩ ሙዘይን ፣የሲኒየር ኢንተርናሽናል ኢንስትራክተር አለማየሁ ሸዋታጠቅ ባለቤት ወይዘሮ ትዝታ አባተ ጫኔ እና የኢትዮጵያ ቮሊቦል ፌዴሬሽን አመራሮች በመገኘት ለአሸናፊዎች የዋንጫና የሜዳሊያ ሽልማት አበርክተዋል።
የዕለቱ የክብር እንግዶች ለኮከብ ተጫዋቾችና አሰልጣኞች ልዩ እውቅና የሰጡ ሲሆን፣ ውድድሩ የኢንስትራክተሩን ሙያዊ ተጋድሎ ከማስታወስ ባለፈ በክለቦች መካከል ያለውን የተቀናጀ ስፖርታዊ መንፈስ ይበልጥ እንዲጎለብት ማድረጉ ተገልጿል።
በተለይም በባህልና ስፖርት ሚኒስቴር እና በቮሊቦል ፌዴሬሽን በኩል የተገኙት ከፍተኛ አመራሮች በዓለም አቀፍ ደረጃ ሀገራቸውን ያስጠሩ ባለሙያዎችን እንዲህ ባለ ደማቅ መድረክ መዘከር ለቀጣዩ ትውልድ ትልቅ መነሳሳትን እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
ጌጡ ተመስገን (Getu Temesgen
#getutemesgen #ethiopianvolleyball #instructoralemayehu #volleyballethiopia #sportsnews #addisababa #ethiopia #mechal #nationalalcohol

Comments