14 days ago
አሜሪካና ሳውዲ አረቢያ ታሪካዊ ስምምነት አደረጉ።
#ethiopia | አሜሪካ እና ሳውዲ አረቢያ በሲቪል የኑክሌር ቴክኖሎጂ ዘርፍ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ታሪካዊ የተባለ ስምምነት መፈራረማቸውን አስታወቁ።
ይህ ስምምነት የአሜሪካ ኩባንያዎች የኑክሌር ቴክኖሎጂን፣ መሣሪያዎችን እና አገልግሎቶችን ለሳውዲ አረቢያ ለማቅረብ እንዲችሉ ያደርጋቸዋል።
የአሜሪካ መንግስት ስምምነቱ የአሜሪካን የኑክሌር ኢንዱስትሪ ተጠቃሚ ከማድረጉም በላይ በዓለም አቀፍ ደረጃ የኑክሌር መስፋፋትን የመቆጣጠር መስፈርቶችን እንደሚያጠናክር ተገልጿል።
ስምምነቱ ሳውዲ አረቢያ የኃይል ፍላጎቷን ለማሟላት ለሲቪል አገልግሎት የሚውል የኑክሌር ኃይል ማመንጫ እንዲኖራት ያስችላል።
ስምምነቱ ሳውዲ አረቢያ በግዛቷ ውስጥ ዩራኒየም የማበልጸግ አቅም እንዲኖራት ሊፈቅድ እንደሚችል እየተዘገበ ይገኛል።
ይህ ስምምነት የተፈረመው በአሜሪካ እና በአጋሮቿ እንዲሁም በኢራን መካከል ያለው ውጥረት በተባባሰበት ወቅት መደረጉ ትኩረት እንዲስብ አድርጓል።
የሳውዲ አረቢያው ልዑል መሐመድ ቢን ሳልማን ከዚህ ቀደም ኢራን የኑክሌር መሣሪያ ከታጠቀች ሳውዲ አረቢያም ተመሳሳይ ለመያዝ እንደምትገደድ ማሳሰባቸው ይታወሳል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #usandsaudiarabia #nuclearcooperationdeal

Comments