1 month ago
የታይሰን ፊዩሪ እና አንቶኒ ጆሹዋ ታላቅ የከባድ ሚዛን ፍልሚያ የሚካሄድበት ቀን እና ስፍራ ይፋ ሆነ
#ethiopia | ለረጅም ጊዜ በስፖርት አፍቃሪዎች ዘንድ ትልቅ ጉጉትን ፈጥሮ የነበረው የታይሰን ፊዩሪ እና አንቶኒ ጆሹዋ የከባድ ሚዛን ቦክስ ግጥሚያ የሚካሄድበት ቦታ ተለይቶ የመጨረሻ ስምምነት ላይ መደረሱ ተታውቋል።
የብሪታኒያውያን ፍልሚያ የሚል ስየሜ የተሰጠው ይህ ታላቅ የቦክስ መርሃ ግብር በመጪው ህዳር ወር በኒውዮርክ ማዲሰን ስኩዌር ጋርደን ውስጥ እንደሚካሄድ ታይሰን ፊዩሪ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አማካይነት ይፋ አድርጓል።
ሁለቱ የብሪታንያ ከባድ ሚዛን ስፖርተኞች የስምምነት ሰነዱን በሳዑዲ አረቢያ የተፈራረሙ ሲሆን ውድድሩ በሀገሪቱ የቦክስ ታሪክ ውስጥ እጅግ ግዙፉ እንደሚሆን ተገምቷል።
ዕድሜው 38 ዓመት የደረሰው ታይሰን ፊዩሪ በፈረንጆቹ 2024 ማጠቃለያ ላይ ከቦክስ ዓለም መገለሉን አስታውቆ የነበረ ቢሆንም በ2026 መጀመሪያ ላይ ወደ መድረኩ መመለሱን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
ፊዩሪ በሙያዊ የቦክስ ጉዞው 36 ጊዜ ማሸነፍ የቻለ ሲሆን ብቸኛ ሽንፈት የገጠመው ደግሞ በ2024 ከዩክሬኑ ኦሌክሳንደር ኡሲክ ጋር ባደረገው ፍልሚያ ነበር።
በ2021 ሁለቱ የከባድ ሚዛን ኮከቦች እንዲገናኙ ጥረት ተደርጎ በተለያዩ ምክንያቶች ሳይሳካ ቀርቶ የነበረ ቢሆንም የአሁኑ ስምምነት ግን የስፖርቱን አፍቃሪዎች የዓመታት ጥበቃ እውን አድርጎታል።
#tysonfury #anthonyjoshua #boxing #madisonsquaregarden #sportsnews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments