20 days ago
በዜጎች ደም የከሸፈው መፈንቅለ መንግስት
በንፁሀን ዜጎች ደም የከሸፈው የቱርክ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አስረኛ አመቱን ደፈነ
#ethiopia | በተርክዬ ታሪክ ውስጥ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣውና በ2016 የተካሄደው የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ አስረኛ ዓመቱን ደፍኗል።
ይህ ክስተት የቱርክን የፖለቲካ የህግ እና የውጭ ግንኙነት ገጽታን በሙሉ ቀይሮታል።
በፈረንጆቹ 2016 የቱርክ ወታደራዊ ክፍል ውስጥ የተወሰነ ቡድን ራሱን የሰላም ምክር ቤት ብሎ የሰየመ በፕሬዝዳንት ረሲብ ጣይብ ኤርዶጋን መንግስት ላይ መፈንቅለ መንግስት ለማድረግ ተንቀሳቀሰ።
በዚያ ምሽት ታንኮች ወደ ኢስታንቡልና አንካራ ዋና ዋና መንገዶች የወጡ ሲሆን የፓርላማ ህንፃ በጦር አውሮፕላኖች ተደብድቧል።
ይሁን እንጂ ፕሬዝዳንቱ ህዝቡ ወደ አደባባይ እንዲወጣ ባስተላለፉት ጥሪ እና ታማኝ መንግስት የፀጥታ ሃይሎች ባደረጉት ተጋድሎ ሙከራው በሰአታት ውስጥ ከሸፈ።
በዚያች አጭር እና አስጨናቂ ምሽት
251 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
ከሟቾቹ አብዛኞቹ በመሪያቸው ጥሪ መፈንቅለ መንግስቱን ለመከላከል የወጡ ንፁሀን ዜጎች ናቸው።
መፈንቅለ መንግስት ሙከራው ከከሸፈ በኋላ ቱርክ የፓርላማ ስርአቷን ጠቅልላ በመጣል በ2017 በተካሄደው ህዝበ ውሳኔ መሰረት ወደ ፕሬዝዳንታዊ ስርአት ተሸጋገረች።
ይህም ለፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ሰፊ ስልጣን ሰጥቷል።
በመንግስት መዋቅር ውስጥ በጦር ሰራዊት በፍርድ ቤት እና በትምህርት ተቋማት ውስጥ ተሳትፎ አላቸው የተባሉ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከስራ በማሰናበት ለእስር ዳርጓል።
ለአስር ዓመታት ያህል በሀገሪቱ ላይ የተጣለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና የተለያዩ የደህንነት ማሻሻያዎች የመንግስትን ቁጥጥር እንዲጠናከር አደረገው።
ዛሬ ቱርክ ውስጥ የዲሞክራሲና የብሔራዊ አንድነት ቀን እየተከበረ ይገኛል።
የአስረኛው ዓመት በዓል አገሪቱ ከከፍተኛ የፖለቲካ ቀውስ ወጥታ አዲስ የፖለቲካ ምዕራፍ ውስጥ መሆኗን የሚያሳይ ነው።
ይሁን እንጂ በአስር ዓመታት ውስጥ የተወሰዱት የፖለቲካ እና የፍትህ እርምጃዎች በአለም አቀፍ ደረጃ በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ የተለያዩ ትችቶች ሲሰነዘሩባቸው ቆይተዋል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #getunews #turkeyistanbulpresident #ersibtaipeerdogan

Comments