12 hours ago
ቶልሷ፦ ተወዳጁ የወላይታ ጥሬ ስጋ እና ማህበራዊ እሴት!
#ethiopia | ጥሬ ስጋ በወላይታ ህዝብ ዘንድ የምግብ አይነት ብቻ ሳይሆን፤ ከማህበራዊ እሴት፣ ከበዓላትና ከከፍተኛ የእንግዳ አቀባበል ስነ-ስርዓት ጋር የተሳሰረ የጠበቀ ባህል ነው።
በወላይታ ባህል የታወቁ የጥሬ ስጋ አዘጋጃጀት አይነቶች፦
ቶልሷ (ቁርጥ ሥጋ)፦ የወላይታ አዲስ ዓመት (ግፋታ) ሲከበር በተለየ ሁኔታ ከተቀለበ ሰንጋ በሬ ተመርጦ የሚዘጋጅ፣ ከዋና ዋና የጮማ እና የቀይ ስጋ ክፍሎች የሚቀርብ ልዩ ቁርጥ ነው።
ሱልሷ፦ ምንም ጮማ ሳይቀላቀል ቀይ ስጋ ብቻ ተመርጦ በደቃቁ ከተከተፈ በኋላ ከነጠረ ቅቤ ጋር ተሰርቶ "ሞቂያ" በተሰኘ ባህላዊ ማንኪያ የሚበላ ነው። ይህ ምግብ በተለይም ለአባወራ እና ለክብር እንግዳ የሚቀርብ እጅግ ተወዳጅ ባህላዊ ምግብ ነው።
አሿ ጢጣ (ጥብስ)፦ ገና በእሳት ላይ ሲጠበስ ምራቅ የሚያስውጥ፣ ልዩ ጣዕም ያለውና በጥብስነቱ በእጅጉ የሚወደድ ነው።
የአቀራረብ ስነ-ስርዓት
ጥሬ ስጋ ብቻውን አይበላም!
በቅመማቅመም እና በቅቤ ከተለወሰው "ሳዎ ባምባሪያ" (ዳታ በርበሬ) ጋር ይጣቀሳል።
ከእንሴት ውጤት ቆጮ (ጎዴታ ኡንጫ) እና ከበቆሎ ቅጣ (ባዳላ ኦይታ) ጋር በመሶብ ዙሪያ አምሮ ይቀርባል።
ዳታው የሚቀርበው "ሻትያ" በተሰኘ ባህላዊ የሸክላ እቃ ላይ ተደርጎ ነው።
"እማታ ፓያ ኤሆ" (መልካም እንግዳ ያምጣልን!)
የወላይታ ሰው እንግዳ አሳቦ ስጋ መብላት ስለሚወድ ሁልጊዜ መልካም እንግዳ እንዲመጣ ይመኛል። ድንገት እግር ጥሎት ወደ ወላይታ የመጣ እንግዳ ጥሬ ስጋ በዳታ አጣቅሶ ሳይበላ አይመለስም—በላ ማለት ደግሞ ቤተኛ ሆኖ የመቅረት ዕድሉ ሰፊ ነው!
በሴፉ ሳሙኤል
#wolaita #ethiopianfood #culture #tolsuwa #sulsuwa #ethiopia #giphata #traditionalfood

Comments