7 months ago
" የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ መክፈል አቃተኝ " አለ የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር።
ጊዚያዊ አስተዳደሩ የካቲት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ፅፎ ለመንግስታዊ መስሪያ ቤቶች ባሰራጨው ሰርኩላር ከያዝነው የካቲት ወር 2018 ዓ.ም ጀምሮ ለመንግስት ሰራተኛ የሚከፈል ገንዘብ እንደሌለ አስታውቋል።
ጊዚያዊ አስተዳደሩ የመንግስት ሰራተኞች ወርሀዊ ደመወዝ መክፈል ያቆመው ከፌደራል መንግስት በጀት ስላልተለቀቀለት መሆኑ እንደ ምክንያት ጠቅሷል።
" የሰራተኛ መንግስት ወርሀዊ ደመወዝ መቼ መከፈል እንደሚጀምር በደብዳቤ አስታውቃለሁ ብሏል " ጊዚያዊ አስተዳደሩ።
ካለፈው ወርሃ ጥር 2018 ዓ.ም ጀምሮ በከፊል የተከፈለው ወርሃዊ የመንግስት ሰራተኛ ደመወዝ በያዝነው የየካቲት ወር ሙሉ ሙሉ መከፈል መቆሙን ይፋ አድርጓዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#tikvahethiopiafamilymekelle
@tikvahethiopia

8 months ago
#update
🔴 ዛሬ አብዛኞቹ በመቐለና ዙሪያዋ የሚገኙ የመንግስትና የግል ባንኮች ለደምበኞቻቸው ጥሬ ገንዘብ መስጠት አቁመዋል።
⚫️ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዛሬም ለሁለተኛ ቀን ወደ ትግራይ አልበረረም።
➡️ የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል ፤ ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎችን ደብቀዋል ያላቸውን ነጋዴዎች አስጠንቅቋል የስራ ቦታቸው አሽጓል ፤ ወርሷል።
ካለፉት አራት ቀናት ወዲህ በአገራችን የሰሜኑ ክፍል ትግራይ አከባቢ እየታዩ ያሉ የግጭት ምልክቶችና የጫሩት ስጋት በማስመልከት የዛሬ ዓርብ ጥር 22/2018 ዓ.ም ውሎ ምን እንደሚመስል ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዳሷል።
በትግራይ መልሶ ጦርነት ይቀሰቀስ ይሆን ? በሚል ስጋት ህዝቡ ከባንኮች በርከት ያለ ጥሬ ገንዘብ የማውጣት እንቅስቃሴ ብሶበት ጥር 21/2018 ዓ.ም በሁሉም የክልሉ አከባቢዎች የሚገኙ የመንግስትና የግል ባንኮች በረጃጅም ወረፋዎች ተጨናንቀው ታይተዋል።
ባንኮቹ በጥሬ ገንዘብ ለቆጣቢ ደምበኞች ሲሰጡ የነበረው ቁጥሩ እየቀነሰ ሄዶ ዛሬ " ካሽ ተሟጦ አልቌል " በሚል ከሂሳብ ወደ ሂሳብ ማሸጋገርና ገቢ የማድረግ አገልግሎት ከመስጠት ውጪ አብዛኞቹ ጥሬ ገንዘብ መስጠት አቁመዋል።
ባንኮቹ የሚሰጡት ጥሬ ገንዘብ ማቆማቸው ተከትሎ ትናንት ጥር 21/2018 ዓ.ም የነበረው የገበያተኛ ግርግርና መጨናነቅ ዛሬ ቀንሶ ታይቷል።
የክልሉ ጊዚያዊ እስተዳደር በተጋነነ የዋጋ ጭማሪ የሚሸጡ ፣ ምርት የሚደብቁ በህግ እንደሚጠይቅ የሚያስጠነቅቅ መግለጫ አውጥቷል።
መግለጫውን ተከትሎ በአክሱም ከተማ በተጋነነ ዋጋ ሸጠዋል የተባሉት የንግድ ቤቶች ታሽገዋል።
በመቐለ ከተማ በድብቅ ከቦታ ወደ ቦታ ሲጓጓዝ የተገኘ 40 ኩንታል ስኳር ተወርሶ ወድያውኑ ለሸማቾች በፍትሀዊ ዋጋ እንዲሸጥ ተደርጓል።
ከኢትዮጵያ አየር መንገድ የዲጂታል የጉዞ ገፅ በተገኘው መረጃ መሰረት ትናንት ጥር 21/2018 ዓ.ም እስካሁን ምክንያቱ ባልተገለፀ ሁኔታ የተቋረጠው የአውሮፕላን ጉዞ ዛሬ እንደሚቀጥል ለተጋዦች ተነግሮ የነበረ ቢሆንም " ተሰርዟል " የሚል መልእክት ወደ ተጓዦች ተልኳል።
ለሁለት ቀናት በተቋረጠው የአውሮፕላን ጉዞ ለአጭር ቆይታ ከትግራይ አዲስ አበባ፤ ከአዲስ አበባ ወደ ትግራይ የተጓዙ ለከፍተኛ እንግልትና ስቃይ መዳረጋቸው በመግለፅ ላይ ይገኛሉ።
ነገ ቅዳሜ ጥር 23/2018 ዓ.ም የተቋረጠው ጉዞ ይቀጥላል ወይስ አይቀጥልም የሚለውን ያለማወቃቸው ደግሞ ስጋታቸው እጅግ ከባድ አድርጎታል።
የአየር ላይ ጉዞ በመስተጓጎሉ ምክንያት በአውቶቡስ በሚደረገው ጉዞ ከ50 በመቶ በላይ የናረ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ ታይቷል።
ተጓዦች 5 ሺህ ብር ሲከፈልበት የነበረው ከ8 - 10 ሺህ ብር በደላላ በመክፈል ለመጓዝ እየተገደዱ መሆናቸው መረጃ አግኝተናል።
ከአራት ቀናት በፊት እየተከሰተ ያለው " መልሶ ግጭት ይቀሰቀስ ይሆን ? " የሚል ስሜት በኮንትሮባንድ ሲሸጥ በነበረው ነዳጅ የዋጋ ጭማሪ እስከትሏል ይህንንና ሌላ ተደምሮ የመቐለ ከተማ እንቅስቃሴ ተቀዛቅዟል።
ባለፉት ጥቂት ቀናት በትግራይና አጎራባች አከባቢዎች ግጭት ቀስቃሽ እንቅስቃሴ እንዳሳሰበው የገለፀው የአፍሪካ ህብረት ተደራዳሪዎች የፕሪቶሪያ ስምምነት ከሚጉዱ ተግባራት እንዲቆጠቡ አሳስቧል።
የኮሚሽኑ ሊቀ-መንበር ማሕሙድ ዓሊ ዮሱፍ እየታየ ያለው ሁኔታ በቅርበት እየተከታተሉት እንደሚገኙና እንዳሳሰባቸው ገልፀዋል።

በትግራይ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል ?
" በጥሬ ማውጣት የሚቻለው ገንዘብ ብር 2 ሺህ ብቻ ነው ፤ አንዳንዶቹ ሲስተም የለም በሚል ምክንያት ጥሬ ገንዘብ መስጠት ያቋረጡ አሉ " - የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች
(ቲክቫህ ኢትዮጵያ - መቐለ)
በትግራይ ክልል ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ተጀምሮ ከሦስት ዓመታት እጅግ አስከፊ የጦርነት ጊዚያት በኃላ ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የመሬትና የሰማይ ተኩስ ቆሞ በክልሉ ተነፃፃሪ ሰላም ተረጋግጧል።
ስምምነቱ ከተፈረመ በኃላ ትግራይ ፍፁም መረጋጋት መጎናፀፍ ቢያቅታትም ባለፉት ሦስት አራት ቀናት ያለው ሁኔታ ግን ባስ ያለ በመሆኑ ህዝቡ " ዳግም የተሟላ ጦርነት ይቀሰቀስ ይሆን ? " በሚል እንቅልፍ አጥቷል።
ከጥር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሰሜን ምዕራብ አካባቢዎች የግጭት ምልክቶች መታየታቸው ህዝቡን ከፍተኛ ጭንቀት ላይ ጥሏል።
በትግራይ ያለውን መጥፎ የጦርነት ስሜቱን ተከትሎ በተለይ ከመቐለ ውጭ በሚገኙ የክልሉ ከተሞች ከባንኮች ጥሬ ገንዘብ መጥፋት ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል።
ከባንክ በቀን እስከ ብር 50 ሺህ ፤ ከATM እስከ 10 ሺህ ማውጣት የሚፈቅደው የብሄራዊ ባንክ አሰራር መስራት ካቆመ ቆይቷል።
የእንዳስላሰ-ሽረና አከባቢዋ ATM ማሽኖች ስራ ካቆሙ ሰነባብተዋል። ረጅም ወረፋ በመጠበቅ በባንክ ገብቶ በጥሬ ገንዘብ ማውጣት የሚቻለው ብር 2 ሺህ ብቻ ነው።
ሁኔታው በጦርነት ስጋት የመጣ ነው የተባለ ሲሆን ከመቐለ ውጪ ባሉ ከተሞች የታየው የጥሬ ገንዘብ አቅርቦት እጥረት ወደ ዋናዋ ከተማዋ ድረስ ዘልቆ ነዋሪዎችን ማስጨነቅ ከጀመረ ቀናት ተቆጥሯል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን ሪፖርታዥ እስካዘጋጀበት ጊዜ ድረስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ መግለጫ ባልሰጠበት ዛሬ ሀሙስ ጥር 21 ቀን 2018 የአውሮፕላን በረራ ተቋርጦ ውሏል።
ይህን ተከትሎ በመቐለ የሚስተዋለው አየር ጥቅምት 2013 ዓ.ም ጦርነቱ ሊጀመር ሲል የነበረውን መጥፎ ጊዜ የሚያስታውስ ሆኗል።
ዛሬ ሀሙስ ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም በመቐለ በሚገኙ የመንግስትና የግል ባንኮች ከወትሮ በተለየ በጥሬ ገንዘብ ፈላጊዎች ተጨናንቀው ቢታዩም ባንኮቹ ለማስተናገድ ተቸግረዋል።
በርካታ የኢትዮጵያ ንግድ ቅርንጫፎች " ሲስተም የለም " በሚል ምክንያት ከአገልግሎት ውጪ ሆነው ሲውሉ ጥቂቶቹ ለአንድ ደምበኛ 2 ሺህ ብር ሲሰጡ ነበር።
ጥቂት የግል ባንኮች ጠዋት ላይ የብሄራዊ ንግድ ባንክን አሰራር በመከተል እስከ ብር 50 ሺህ ጥሬ ገንዘብ መስጠትና በATM ማሽን ማስተናገድ ቢጀምሩም በተገልጋይ ብዛት ከሰዓት በኋላ 10 ሺህ ወደ መስጠት ወርደዋል።
" ሁኔታው ተረጋግቶ በቢሊዮን የሚገመት ከባንኮች ውጭ ያለው ብር ካልተመለሰ በሚቀጥሉት ቀናት ጥሬ ገንዘብ ከባንክ የማውጣት አገልግሎት ሊቆም ይችላል " የሚል ስጋታቸውን የባንክ ባለሞያዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ከወቅታዊው ሁኔታ ተያይዞ የመቐለ ከተማ በርካታ ነዋሪዎች ምግብና ምግብ ነክ እቃዎች በስፋት ሲገዙ የተስተዋለ ሲሆን እንደ ዘይት በመሰሉ በቆየው የመግዣ ዋጋ በአንድ ባለ 5 ሊትር እስከ 500 ብር ጭማሪ ተስተውሏል።
ዛሬ ሀሙስ ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ ሁሉም የትግራይ አውሮፕላን ማረፍያዎች የተቋረጠው በረራ ነገ አርብ ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚኖር የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተጓዦች ዲጂታል ሲስተም ያሳያል።
የዛሬው በረራ ለምን እንደተቋረጠ ለመቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ጥያቄ ያቀረበው ቲክቫህ ኢትዮጵያ " በረራው የተቋረጠው በመጥፎ አየር ሁኔታ እንዳልሆ " እና ከዚህ ውጭ ያለው ምክንያት ምን እንደሆነ ከበላይ አካላት እንዳልተነገራቸውና እንደማያውቁ ተናግረዋል።

9 months ago
በትግራይ ስም የሚንቀሳቀሱ የፓለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ቦርድ እውቅና የተነፈጋቸው ጨምሮ ቁጥራቸው ከደርዘን በላይ ሆኗል።
ኢሮብ ማብሎ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ (Irob Mablo Democratic Party) ከብሄራዊ የምርጫ ቦርድ ቅድመ እውቅና ማግኘቱ ይፋ አድርጓል።
ፓርቲው ታህሳስ 29/2018 ዓ.ም በማህበራዊ የትስስር ገፁ ይፋ እንዳደረገው ከመስከረም 30/2018 ዓ.ም ጀምሮ ከሚመለከተው አካል ቅድመ እውቅና አግኝቶ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል።
ፓርቲው በትግራይ ካሉ ብሄረሰቦች አንዱ ለሆነው የኢሮብ ብሄረሰብ መብት መከበር ቅድምያ ሰጥቶ ይታገላል።
የተሰረዘውን ህወሓት እና እውቅና የተነፈጋቸውን ጨምሮ በክልሉ በትግራይ ስም የሚንቀሳቀስ 18ኛ የፓለቲካ ፓርቲ ሆኗል።
1. ህወሓት
2. ዓረና
3. ባይቶና
4. ሳወት
5. ቀንጪ
6. ዓዴፓ
7. ትዴፓ
8. ወለዶ
9. ስምረት
10. ናፅነት
11. ራያ ራዩማ
12. ፎረም
13. ምንቅስቓስ ፓርቲ ኢትዮጵያውያን
14. ሹም ተምቤን
15. ኢሮብ ማብሎ
16. ሰብዓ እንደርታ
17. ኣክሱማይ ዋዕላ
18. ሽረታይ
ትግራይን ማእከል አድርገው ከሚንቀሳቀሱ ፓርቲዎች ተጠቃሽ ሲሆኑ ህወሓት የተሰረዘ ሲሆን ዓዴፓና ኣክሱማይ ዋዕላ ከብሄራዊ የምርጫ ቦርድ የፓርቲ እውቅና የተነፈጋቸው ናቸው።
ከዚህ በተጨማሪ ገዢው ብልፅግና ፓርቲም ትግራይ ውስጥ ለመንቀሳቀስ ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ፍቃድ ያለው ፓርቲ ነው።

11 months ago
" ቦምቡ ሆን ብሎ ህዝብ ለማሸበር የተጣለ ነው " - የመቐለ የሰላምና ፀጥታ ፅህፈት ቤት
➡️ " በሰውም ይሁን በንብረት ያጋጠመ አደጋ የለም "
ትናንት ሀሙስ ህዳር 18/2018 ዓ.ም ከሌሊቱ 4:25 በመቐለ ዩኒቨርስቲ ዓዲ ሓቂ ግቢ አጥር ዙሪያ ከባድ የቦንብ ድምፅ ፍንዳታ ተሰምቶ ነበር።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ዛሬ አርብ ህዳር 19/2018 ዓ.ም ከባድ የፍንዳታ ደምፅ ወደ ነበረበት ቦታ በአካል በመሄድ ተመልክቷል።
በቦምብ ፍንዳታው በሰው ህይወት ያጋጠመ አደጋ የሌለ ሲሆን ፍንዳታው በነበረበት አቅራቢያ ያሉ ቤቶች መስተዋቶቻቸው መሰባበሩ መመልከት ችለናል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ በቦታው ያገኛቸው ነዋሪዎች " ፍንዳታው በእጅ የተጣለ ቦምብ ሳይሆን ለረጅም ጊዜ ተቀብሮ የቆየ ፈንጅ ሊሆን ይችላል " የሚል አስተያየት አጋርተዋል።
የመቐለ የሰላምና ፀጥታ ፅህፈት ቤት የትናንት ምሽት ፍንዳታው አስመልክቶ ለ104.4 ሬድዮ የመቐለ ኤፍ ኤም በሰጠው መረጃ ፍንዳታው ሆን ተብሎ ህዝብ ለማሸበር የተፈፀመ ነው ብሏል።
የድርጊቱን ፈፃሚዎች ማንነት እንደሚያጣራ የገለፀው ፅህፈት ቤቱ ፤ ህዝቡ ድርጊቱ እንዲያወግዘው አስገንዝቧል።

12 months ago
#update
ወደ መቐለ የሚያመሩ መንገዶች ዛሬም ለሁለተኛ ቀን በሁለት አቅጣጫ በትግራይ ኃይል ሰልፈኞች ተዘግተዋል።
የተዘጉት መንገዶች በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ከመቐለ በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት በምትገኘው የኣጉላዕ ከተማ ፤ በደቡባዊ ዞን ከመቐለ 100 ኪሎ ሜትር አከባቢ በምትርቀው የመኾኒ ከተማ መሆኑ ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ መረጃ ደርሶታል።
በተጨማሪ በሰሜን ምዕራብ ዞን ወደ እንዳስላሰ-ሽረ ከተማ የሚወስደው መንገድ ከከተማዋ 20 ኪሎ ሜትር ርቀት በሚገኘው እንዳባጉና ከተማ በሰልፈኞች ተዘግቷል።
ሰልፈኞቹ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም ከመቐለ ከተማ ወደ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ የሚወስደው ዋና መንገድ ዘግተው ውለው በዚያው ቀን ምሸት ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕረዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) ተወያይተው " ጥያቄያችሁ ልክ ነው ፤ በየደረጃው ይመለሳል " ተብለው ነበር።
ጉዳዩን ተከታትለን መረጃውን የምንልክ ይሆናል።

" ሰላምን እንሻለን ! " - የትግራይ ኃይል አባላት
➡️ " የኛን ጥያቄ መመለስ ከማይችል አመራር የሌላው ህዝብ ጥያቄ ሊመልስ አይችልም ! "
የትግራይ ኃይል አባላት ዛሬ ሰኞ ጥቅምት 3/2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 2:30 ጀምረው የመብት ጥያቄ አንስተው በከተማዋ ዋና ዋና መንገዶች ሰላማዊ ሰልፍ አካሂደዋል።
ሰልፈኛቹ ቁጣን ባዘለ ድምፅ ፦
- " የደመወዝና ጥቅማጥቅም ጥያቄያችን ይመለስ ! "
- " የሰራዊት ጥያቄ የማይመልስ አመራር የሌላው ህዝብ ጥያቄ መመለስ አይችልም ! "
- " የሰራዊት ድምፅ ይሰማ ! "
- " ሰላምን እንሻለን ! "
- " ክብር ለሰራዊትና ለተሰው ቤተሰብ አባላት ! "
የሚሉና ሌሎች መፈክሮች አሰምተዋል።
ሰላማዊ ሰልፈኞቹ መፈክራቸው እያሰሙ ወደ ትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር የፕሬዜዳንት ፅህፈት ቢያመሩም ፕሬዜዳንቱ ማግኘት አልቻሉም።
ጥያቄያቸው ስምቶ መልስ የሚሰጥ ሃላፊ በማጣታቸው የተቆጡት ሰልፈኛቹ ከቀኑ 7:00 እስከ 11:00 ከመቐለ ወደ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ የሚወስደው ዋናው የመኪና መንገድ በድንጋይና በአካል ዘግተውት ውለዋል።
ይህንን መረጃ ከተዘጋጀበት ጥቂት ደቂቃዎች በፊት የሰላማዊ ሰልፈኞቹ ተወካዮቹ ከጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ለውይይት መቀመጣቸው ተከትሎ የተዘጋው መንገድ መከፈቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ አረጋግጧል።
በተጀመረው ውይይት የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) መገኘታቸውና አለመገኘታቸው ማረጋገጥ አልቻልንም።
የውይይቱን ውጤት ተከታትለን እናቀርባለን።
#update - በአሁኑ ሰዓት የሰላማዊ ሰልፈኞቹ ተወካዮች የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀ) ከሚገኙባቸው ከፍተኛ ወታደራዊና የስቪል አመራሮች በመነጋገር ላይ ይገኛሉ።

Sponsored by
Surafel
1 year ago
በቤት ውስጥ ተቀምጦ የነበረ ተተኳሽ ፈንድቶ በአንድ ቤተሰብ ላይ ሞትና ጉዳት አስከተለ።
ነሓሴ 26/2017 ዓ.ም በትግራይ ማእከላዊ ዞን የጭላ ከተማ ያጋጠመው የተተኳሽ መፈንዳት አደጋ አባትና የ8 ዓመት ልጅ ህይወት ቀጥፎ የ3 ዓመት ህፃን አቁስሏል።
በተካሄደው ደም አፋሳሹ ጦርነት ምክንያት በጭላ ኣበርገለ ተበትነው ያልተወገዱ ተተኳሾች እያደረሱት ያለው ውድመት እንዲቆም የመንግስትና የባለሞያ ትኩረት ይሻል ብለዋል አከባቢው ነዋሪዎች።
በጭላ ኣበርገለ ተበትነው የሚገኙ ያልተወገዱ ተተኳሾች በሰውና እንስሳት ህይወት እንዲሁም ንብረት ላይ አደጋ እያስከተሉ መሆናቸው በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#tikvahethiopiafamilymekelle
@tikvahethiopia
ነሓሴ 26/2017 ዓ.ም በትግራይ ማእከላዊ ዞን የጭላ ከተማ ያጋጠመው የተተኳሽ መፈንዳት አደጋ አባትና የ8 ዓመት ልጅ ህይወት ቀጥፎ የ3 ዓመት ህፃን አቁስሏል።
በተካሄደው ደም አፋሳሹ ጦርነት ምክንያት በጭላ ኣበርገለ ተበትነው ያልተወገዱ ተተኳሾች እያደረሱት ያለው ውድመት እንዲቆም የመንግስትና የባለሞያ ትኩረት ይሻል ብለዋል አከባቢው ነዋሪዎች።
በጭላ ኣበርገለ ተበትነው የሚገኙ ያልተወገዱ ተተኳሾች በሰውና እንስሳት ህይወት እንዲሁም ንብረት ላይ አደጋ እያስከተሉ መሆናቸው በተደጋጋሚ መዘገባችን ይታወሳል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#tikvahethiopiafamilymekelle
@tikvahethiopia
1 year ago
በትግራይ አክሱም ከተማ የተፈጠረው አሳዛኝ ክስተት ምንድን ነው ?
ባለትዳሮቹ በጨርቅ ታስረው ውሃ ወደሞላው ኩሬ ገብተው ሞተው ተገኝተዋል።
አሳዛኝ ክስተቱ ነሀሴ 16/2017 ዓ.ም በአክሱም ከተማ ቓላሚኖ የኩሬ ውሃ በሚገኝበት ፅልዐ ተብሎ በሚጠራ ልዩ ቦታ ነው ያጋጠመው።
ጥንዶቹ የክርስትና እምነት ተከታዮች በመሆናቸው ምክንያት በመካከላቸው ለመጋባት የሚከለክል የስጋ ዝምድና ቢኖርም ከመጋባት አልፈው ልጅ እስከመውለድ ደርሰዋል።
የአብራካቸው ክፋይ የ4 ወር ዕድሜ ያለው ጨቅላ ህፃን አፍርተዋል።
የቅርብ የሩቅ ቤተሰብ በመካከላቸው ባለው የስጋ ዝምድና ምክንያት እንዲለያዩ ከምክር ባለፈ የተለያዩ ጫናዎች ያሳድርባቸው እንደነበረ የአከባቢውን ማህበረሰብ ጠቅሶ የትግራይ ፓሊስ ገልጿል።
' ተለያዩ ' የሚል የዘመድ አዝማድ ጫና የበረታባቸው ጥንዶቹ በአንድ ኩሬ ውስጥ ህይወታቸው አልፎ ተገኝቷል።
ፊት ለፊት ተጣብቀው ራሳቸው በጨርቅ ታስረው ውሃ ወደ ሞላ ኩሬ ገብተው ሞተው ተገኝተዋል ይላል የፓሊስ መረጃ።
" ስለ ጥንዶቹ አሟሟት እስከ አሁን የተገኘው መረጃው በቂና የመጨረሻ አይደለም " ያለው ፓሊስ " ስርዓተ ቀብሩ ቢፈፀምም ምርመራው ይቀጥላል " ብሏል።

" ሀኪሞቹ ከአግባብ ውጪ ከታሰሩበት በአስቸኳይ ይፈቱ የህግ የበላይነት ይከበር " - ማኅበሩ
የትግራይ ህክምና ማኅበር በአክሱም ዩኒቨርስቲ የሚስተምሩና በሞያው ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ ሁለት የስፔሻሊቲ ሀኪሞች ታስረዋል።
ታሳሪዎቹ ዶ/ር ብርሃኑ ጥላሁን እና ዶ/ር ሙሉ ዳኘው እንደሚባሉ የገለፀው ማህበሩ ከስራ ገበታቸው በፓሊስ ቁጥጥር መዋላቸውን አስታውቋል።
ማንኛውም ሰው ሆነ ባለሞያ ከህግ በታች መሆኑ ያስታወሰው ማህበሩ የአባላቱ መታሰር ከህክምና ህግ (Medco legal ) እንደሚያያዝ ጠቁሞ ህጉ የራሱ የሆነ የአፈፃፀም ስርዓት አለው ብሏል።
የኢፌዲሪ የጤና አገልግሎት አስተዳደርና ቁጥጥር አዋጅ ቁጥር 1362/2006 አንቀፅ 37 ቁጥር 1 ና 2 አንድ ባለሞያ በህክምና አሰጣጥ ወቅት ባጋጠመ ስህተት የሚፈፀም ወንጀል ተጠያቂ የሚሆንበት የህግ አገባብ ተቀምጧል ሀኪሞቹ ግን ይህንን የህግ አካሄድ ተጥሶ ነው የታሰሩት ብሏል።
ስለሆነም ሀኪሞቹ ከአግባብ ውጪ ከታሰሩበት በአስቸኳይ እንዲፈቱና የህግ የበላይነት እንዲከበር የትግራይ ህና ማህበር ጥሪውን አቅርቧል።

በመብረቅ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።
ነሀሴ 12/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ክልተ ኣውላዕሎ ወረዳ ታሕታይ ዓድቕሳንድድ ቀበሌ " ሞፅቖ " በተባለ ልዩ ቦታ ጎድጓዳማና ሀይለኛ ዝናብን ተከትሎ በወደቀው መብረቅ የሁለት ሰው ህይወት ጠፍቷል።
የአከባቢው ተወላጆች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ - መቐለ በሰጡት መረባ የመብረቅ አደጋው በእረኝነት ላይ የነበሩ የ13 እና 19 ዓመት ዕድሜ ያላቸው የሁለት ወንዶችን ህይወት ወዲያው አጥፍቷል።
መብረቁ በአከባቢው ባለው ሰፊ ዋሻ ተጠልለው ከነበሩት እንስሳት በ21 ጉዳት አድርሷል።
ከመብረቅ አደጋ ራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንችላለን ?
(ተባባሪ ፕሮፌሰር ታደሰ ተረፈ የዘርፉ ተመራማሪ - ለኢቢሲ ተናግረው ከነበረው)
- በዝናብ ወቅት የቤት በርና መስኮትን መዝጋት፣
- ከከፍታ ቦታ መራቅ፣
- በመኪና ውስጥ ከሆኑ ዘጋግቶ መቀመጥ፣
- ሜዳ ላይ ለብቻ አለመገኘት፣
- መብረቅ ወደ የኤክትሪክ ገመድ ገብቶ ተጨማሪ የኤሌክተሪክ ፍሰት በመጨመር ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ሊያቃጥል ይችላል፡፡ ስለዚህ ሬጉሌተር መግጠም ወይም በመብረቅ ሰዓት ሶኬቶችን መንቀል ያስፈልጋል።
- ህንጻዎች እንዳይመቱ አናታቸው ላይ የብረት ገመድ ተዘርግቶ አንዱን ጫፍ ወደመሬት በመቅበር መከላከል ይቻላል።

#tigray
በትግራይ መኾኒ ከተማ በታጣቂዎች መካከል በተከፈተ ቶክስ 8 ስቪሎች ቆሰሉ።
ያጋጠመ ሞት ባይኖርም ከቆሰሉት መካከል እንዱ በሞት አፋፍ ይገኛል ተብሏል።
የቶክስ ልውውጡ ዛሬ ነሀሴ 12/2017 ዓ.ም ከቀትር በፊት እንደነበረ የገለፁት የቲክቫህ ኢትዮጵያ የመቐለ ቤተሰብ ምንጮች ድርጊቱ የራያ ዓዘቦ ምልሻ ፅህፈት ቤት ለመቆጣጠር ያለመ ነበር።
ቶክሱ በራያ ዓዘቦ ምልሻ ፅህፈት ቤት ኃላፊና በአከባቢው በሚገኘው የትግራይ ኃይል (ቲዲኤፍ) መካካል እንደነበር የገለፁት የመረጃ ምንጮች የምልሻ ኃላፊው በምን ሁኔታ እንደሚገኙ አስመልክተው ያሉት ነገር የለም።
በመኾኒ ከተማ የተፈጠረው ቶክስ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ሽብርና አለመረጋጋት ፈጥሮ ውሏል።
ባለፈው ወርሀ ሀምሌ 2017 ዓ.ም የትግራይ ደቡባዊ ዞን ዋና እተዳዳሪ በፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) ከስልጣን መነሳታቸው የሚገልፅ ደብዳቤ መፃፉን ተከትሎ የተነሳው ውዝግብ እስከ አሁን መቋጫ አላገኘም።
ፕሬዜዳንቱ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ ሃፍቱ ኪሮስ ከስልጣን እንዳነሱዋቸው ቢናገሩም ዋና እስተዳዳሪው እስከ ዛሬዋ ቀን ዞኑን ወክለው ስራዎች እየከወኑ ይገኛሉ።
የዞኑ ነዋሪዎች በመኾኒና ሌሎች ከተሞች በስልጣን ያሉት ዋና አስተዳዳሪ በመደገፍ የፕሬዝዳንቱን ውሳኔ በመቃወም ሰላማዊ ስልፍ መውጣታቸው መዘገባችን ይታወሳል።

" የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) እና የፋይናነስና ሃብት ማስተባበርያ ሃላፊ ምሕረት በየነ (ዶ/ር) እስረኛ ሆነው ፍርድ ቤት እንዲቀርቡልን እና የፍርድ ቤት ውሳኔ እንዲያስፈፅሙ ትእዛዝ ይፃፍልን " - የትግራይ መምህራን ማህበር ጠበቃ
➡️ " የእስር ትእዛዝ ይፃፍልን ጥያቄው ተቀባይነት የለውም " - የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት
ከፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ማግስት በ2015 ዓ.ም የተጀመረው የ " 17 ወራት የመምህራን ውዙፍ ደመወዝ ይከፈለን " ጥያቄ ወደ ፍርድ ቤት ከተመራ ወራት ተቆጥረዋል።
ክርክሩ በመዳኘት ላይ የሚገኘው የትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሀምሌ 15/2017 ዓ.ም ባዋለው ችሎት የመምህራን ክስ የያዘው የህግ ጠበቃ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር የሚገኘው የፌደራል የገንዘብ ሚንስቴርና የክልሉ ፋይናንስ ቢሮ ገንዘብ እንዲታገድ ወስኗል።
የፍርድ ቤት የእግድ ትእዛዝ የተጣለበት ብር ግማሽ ቢሊየን እና 17 ሚሊዮን ሲሆን ግማሽ ቢሊዮኑ የክልሉ ፋይናንስና ሃብት ማሰባሰብ ቢሮ ቀሪው 17 ሚሊዮን ብር ደግሞ የፌደራል የገንዘብ ሚንስቴር እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
አቃቤ ህግ የገንዘቡ እግድ በማስመልከት ባቀረበው ክርክር በተጠቀሰው የባንክ ሂሳብ ቁጥር የሚገኘው ግማሽ ቢሊዮን ብር ቢሮው በሃላፊነት ያስቀመጠው የክልሉ መንግስታዊ መ/ቤቶች ያልተጠቀሙበት በአደራ የተቀመጠ ነው ብሏል።
" የይታገድ " ውሳኔ የተላለፈበት የፌደራል የገንዘብ ሚንስቴር 17 ሚሊዮን ብር አስመልክቶ የተባለ ነገር የለም።
የከሳሽ ጠበቃ የመምህራን የ17 ወራት ውዙፍ ደመወዝ እንዳይከፈል እያስተጓጎሉ ናቸው ያላቸው የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ታደሰ ወረደ (ሌ/ጀነራል) እና የፋይናነስና ሃብት ማስተባበርያ ሃላፊ ምሕረት በየነ (ዶ/ር) በእስር ወደ ፍርድ ቤት ሸርበው እንዲሰረዱ ትእዛዝ ይፃፍልኝ ሲል ያመለከተ ሲሆን ፍርድ ቤቱ ጥያቄውን ውድቅ አድርጎታል።
ፍርድ ቤቱ የቀረበው ክስ አፈፃፀም ለመመልከት ለሀምሌ 22/2017 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

Comments