በትግራይ ያለው ሁኔታ ምን ይመስላል ?
" በጥሬ ማውጣት የሚቻለው ገንዘብ ብር 2 ሺህ ብቻ ነው ፤ አንዳንዶቹ ሲስተም የለም በሚል ምክንያት ጥሬ ገንዘብ መስጠት ያቋረጡ አሉ " - የመቐለ ከተማ ነዋሪዎች
(ቲክቫህ ኢትዮጵያ - መቐለ)
በትግራይ ክልል ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ተጀምሮ ከሦስት ዓመታት እጅግ አስከፊ የጦርነት ጊዚያት በኃላ ጥቅምት 24 ቀን 2015 ዓ.ም በፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት የመሬትና የሰማይ ተኩስ ቆሞ በክልሉ ተነፃፃሪ ሰላም ተረጋግጧል።
ስምምነቱ ከተፈረመ በኃላ ትግራይ ፍፁም መረጋጋት መጎናፀፍ ቢያቅታትም ባለፉት ሦስት አራት ቀናት ያለው ሁኔታ ግን ባስ ያለ በመሆኑ ህዝቡ " ዳግም የተሟላ ጦርነት ይቀሰቀስ ይሆን ? " በሚል እንቅልፍ አጥቷል።
ከጥር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በሰሜን ምዕራብ አካባቢዎች የግጭት ምልክቶች መታየታቸው ህዝቡን ከፍተኛ ጭንቀት ላይ ጥሏል።
በትግራይ ያለውን መጥፎ የጦርነት ስሜቱን ተከትሎ በተለይ ከመቐለ ውጭ በሚገኙ የክልሉ ከተሞች ከባንኮች ጥሬ ገንዘብ መጥፋት ከጀመረ ሰንበትበት ብሏል።
ከባንክ በቀን እስከ ብር 50 ሺህ ፤ ከATM እስከ 10 ሺህ ማውጣት የሚፈቅደው የብሄራዊ ባንክ አሰራር መስራት ካቆመ ቆይቷል።
የእንዳስላሰ-ሽረና አከባቢዋ ATM ማሽኖች ስራ ካቆሙ ሰነባብተዋል። ረጅም ወረፋ በመጠበቅ በባንክ ገብቶ በጥሬ ገንዘብ ማውጣት የሚቻለው ብር 2 ሺህ ብቻ ነው።
ሁኔታው በጦርነት ስጋት የመጣ ነው የተባለ ሲሆን ከመቐለ ውጪ ባሉ ከተሞች የታየው የጥሬ ገንዘብ አቅርቦት እጥረት ወደ ዋናዋ ከተማዋ ድረስ ዘልቆ ነዋሪዎችን ማስጨነቅ ከጀመረ ቀናት ተቆጥሯል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ይህን ሪፖርታዥ እስካዘጋጀበት ጊዜ ድረስ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይፋዊ መግለጫ ባልሰጠበት ዛሬ ሀሙስ ጥር 21 ቀን 2018 የአውሮፕላን በረራ ተቋርጦ ውሏል።
ይህን ተከትሎ በመቐለ የሚስተዋለው አየር ጥቅምት 2013 ዓ.ም ጦርነቱ ሊጀመር ሲል የነበረውን መጥፎ ጊዜ የሚያስታውስ ሆኗል።
ዛሬ ሀሙስ ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም በመቐለ በሚገኙ የመንግስትና የግል ባንኮች ከወትሮ በተለየ በጥሬ ገንዘብ ፈላጊዎች ተጨናንቀው ቢታዩም ባንኮቹ ለማስተናገድ ተቸግረዋል።
በርካታ የኢትዮጵያ ንግድ ቅርንጫፎች " ሲስተም የለም " በሚል ምክንያት ከአገልግሎት ውጪ ሆነው ሲውሉ ጥቂቶቹ ለአንድ ደምበኛ 2 ሺህ ብር ሲሰጡ ነበር።
ጥቂት የግል ባንኮች ጠዋት ላይ የብሄራዊ ንግድ ባንክን አሰራር በመከተል እስከ ብር 50 ሺህ ጥሬ ገንዘብ መስጠትና በATM ማሽን ማስተናገድ ቢጀምሩም በተገልጋይ ብዛት ከሰዓት በኋላ 10 ሺህ ወደ መስጠት ወርደዋል።
" ሁኔታው ተረጋግቶ በቢሊዮን የሚገመት ከባንኮች ውጭ ያለው ብር ካልተመለሰ በሚቀጥሉት ቀናት ጥሬ ገንዘብ ከባንክ የማውጣት አገልግሎት ሊቆም ይችላል " የሚል ስጋታቸውን የባንክ ባለሞያዎች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።
ከወቅታዊው ሁኔታ ተያይዞ የመቐለ ከተማ በርካታ ነዋሪዎች ምግብና ምግብ ነክ እቃዎች በስፋት ሲገዙ የተስተዋለ ሲሆን እንደ ዘይት በመሰሉ በቆየው የመግዣ ዋጋ በአንድ ባለ 5 ሊትር እስከ 500 ብር ጭማሪ ተስተውሏል።
ዛሬ ሀሙስ ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም ወደ ሁሉም የትግራይ አውሮፕላን ማረፍያዎች የተቋረጠው በረራ ነገ አርብ ጥር 21 ቀን 2018 ዓ.ም እንደሚኖር የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተጓዦች ዲጂታል ሲስተም ያሳያል።
የዛሬው በረራ ለምን እንደተቋረጠ ለመቐለ አሉላ አባነጋ አውሮፕላን ማረፍያ ጥያቄ ያቀረበው ቲክቫህ ኢትዮጵያ " በረራው የተቋረጠው በመጥፎ አየር ሁኔታ እንዳልሆ " እና ከዚህ ውጭ ያለው ምክንያት ምን እንደሆነ ከበላይ አካላት እንዳልተነገራቸውና እንደማያውቁ ተናግረዋል።
ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#tikvahethiopiafamilymekelle
@tikvahethiopia

8 months ago