Logo
FIDEL POST NEWS
በመብረቅ አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።

ነሀሴ 12/2017 ዓ.ም ከቀኑ 10:00 በትግራይ ምስራቃዊ ዞን ክልተ ኣውላዕሎ ወረዳ ታሕታይ ዓድቕሳንድድ ቀበሌ " ሞፅቖ " በተባለ ልዩ ቦታ ጎድጓዳማና ሀይለኛ ዝናብን ተከትሎ በወደቀው መብረቅ የሁለት ሰው ህይወት ጠፍቷል።

የአከባቢው ተወላጆች ለቲክቫህ ኢትዮጵያ - መቐለ በሰጡት መረባ የመብረቅ አደጋው በእረኝነት ላይ የነበሩ የ13 እና 19 ዓመት ዕድሜ ያላቸው የሁለት ወንዶችን ህይወት ወዲያው አጥፍቷል።

መብረቁ በአከባቢው ባለው ሰፊ ዋሻ ተጠልለው ከነበሩት እንስሳት በ21 ጉዳት አድርሷል።

ከመብረቅ አደጋ ራሳችንን እንዴት መጠበቅ እንችላለን ?

(ተባባሪ ፕሮፌሰር ታደሰ ተረፈ የዘርፉ ተመራማሪ - ለኢቢሲ ተናግረው ከነበረው)

- በዝናብ ወቅት የቤት በርና መስኮትን መዝጋት፣

- ከከፍታ ቦታ መራቅ፣

- በመኪና ውስጥ ከሆኑ ዘጋግቶ መቀመጥ፣

- ሜዳ ላይ ለብቻ አለመገኘት፣

- መብረቅ ወደ የኤክትሪክ ገመድ ገብቶ ተጨማሪ የኤሌክተሪክ ፍሰት በመጨመር ኤሌክትሮኒክስ እቃዎችን ሊያቃጥል ይችላል፡፡ ስለዚህ ሬጉሌተር መግጠም ወይም በመብረቅ ሰዓት ሶኬቶችን መንቀል ያስፈልጋል።

- ህንጻዎች እንዳይመቱ አናታቸው ላይ የብረት ገመድ ተዘርግቶ አንዱን ጫፍ ወደመሬት በመቅበር መከላከል ይቻላል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ
መቐለ
#tikvahethiopiafamilymekelle

@tikvahethiopia
1 year ago

No replys yet!

Be the first to share what you think — your comment will appear here.