7 months ago
🇸🇳 የሴኔጋል "አንበሶች" በሽልማት ተንበሸበሹ! 🦁💰
#ethiopia | የአፍሪካ እግር ኳስ ንጉሥነታቸውን ያስመሰከሩት የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን አባላት፣ በሀገሪቱ ወጣት ፕሬዝዳንት ባሲሩ ዲዮማዬ ፋዬ አማካኝነት በታሪክ የማይረሳ እና እጅግ ድንቅ የሆነ የክብር አቀባበል እንዲሁም የሽልማት ናዳ ወርዶባቸዋል።
ፕሬዝዳንቱ ለቡድኑ አባላት ካበረከቱት ፈርጀ ብዙ ሽልማቶች መካከል ዋና ዋናዎቹ፦
💵 የገንዘብ ሽልማት፦
* ለቡድኑ አባላት በጥሬ ገንዘብ 535,000 ዶላር ተበርክቷል።
* እያንዳንዱ ተጫዋች ለቤት መስሪያ የሚሆን 135,000 ዶላር ተጨማሪ ስጦታ አግኝቷል።
* ለአሰልጣኞች እና ለቡድን አጋዥ አባላት ደግሞ 90,000 ዶላር ተሰጥቷል።
🏗️ የመሬት ስጦታ፦
* ለእያንዳንዱ ተጫዋች በዋና ከተማዋ ዳካር መሐል 1,500 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው መሬት።
* ለአሰልጣኝ ቡድኑ አባላት 1,000 ካሬ ሜትር መሬት።
* በአጠቃላይ መንግስት 68,000 ካሬ ሜትር መሬት ለቡድኑ አባላት በስም አዙሯል።
🎖️ የክብር ማዕረግ፦
ከገንዘብ እና ከመሬት ስጦታው ባለፈ፣ ፕሬዝዳንቱ ለታሪካዊው ድል ባለቤቶች የሀገሪቱን ከፍተኛ የክብር "የኮማንደር ማዕረግ" (National Order of the Lion) ሰጥተዋል።
በድምሩ የሴኔጋል መንግስት ከ 6.2 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለዚህ ድል ወጪ ማድረጉ ታውቋል። ይህ እርምጃ ሀገሪቱ ለስፖርቱ ያላትን ትልቅ ክብር እና ለወጣቶቿ የምትሰጠውን ማበረታቻ በግልጽ ያሳየ ሆኗል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#senegal #africanchampions #bassiroudiomayefaye #terangalions #footballnews #africacup #inspiration #ethiopia

🇸🇳"የአፍሪካ ዋንጫ ቆይታዬ እዚህ ላይ ያበቃል" የሳድዮ ማኔ
#ethiopia | የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን ስያሜን በዓለም መድረክ ከፍ ያደረገው ድንቅ ኮከብ ሳድዮ ማኔ፣ የዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ የፍጻሜ ጨዋታ በውድድሩ ታሪኩ የመጨረሻው እንደሚሆን በይፋ አስታወቀ።
⚽ የጀግና ስንብት
ሀገሩን ለፍጻሜ እንድትደርስ በግብፅ ላይ ወሳኝ ጎል ያስቆጠረው ማኔ፣ ከጨዋታው በኋላ በሰጠው መግለጫ እንዲህ ብሏል፦ "ይህ የመጨረሻ አፍሪካ ዋንጫዬ ነው። በመጨረሻው የፍጻሜ ጨዋታዬ ላይ በመሳተፌ በጣም ደስተኛ ነኝ፤ በጨዋታው እየተደሰትኩ ለሀገሬ ዋንጫውን ለማምጣት ከፍተኛ ጥረት አደርጋለሁ።"
🗣️ የአሰልጣኙ ምላሽ፦ "ሴኔጋል ማኔን ትፈልገዋለች"
የማኔን ውሳኔ ተከትሎ የሴኔጋል አሰልጣኝ ፓፔ ቲያው ለአጥቂው ያላቸውን አድናቆትና ፍላጎት ገልጸዋል። አሰልጣኙ "ማኔን ሴኔጋል አሁንም ትፈልገዋለች" ያሉ ሲሆን፣ ኮከቡ ውሳኔውን ቀይሮ ለተጨማሪ ዓመታት በብሔራዊ ቡድኑ እንደሚቆይ ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል።
🏆 የማኔ አሻራ በአፍሪካ ዋንጫ
ሳድዮ ማኔ ለሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን የነፍስ ወከፍ ሞተር ሆኖ የቆየ ሲሆን፣ በውድድሩ ታሪክም የማይረሳ አሻራ ጥሏል። የዘንድሮውን ዋንጫ በማንሳት በክብር ለመሰናበት ያለው ህልም የብዙዎች የሴኔጋል ደጋፊዎች ምኞት ነው።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#ሳድዮማኔ #ሴኔጋል #አፍሪካዋንጫ #እግርኳስ #sadiomane #senegal #afcon #footballnews #terangalions

Comments