2 months ago
በቀን ከ2.5 ሚሊዮን ቶን በላይ ምግብ ያላግባብ ይጣላል!
#ethiopia | የአለም የምግብ ፕሮግራም በየቀኑ ከ2.5 ሚሊዮን ቶን በላይ ምግብ ወደ ቆሻሻ ገንዳ ይጣላል ብሏል።
የአለም የምግብ ፕሮግራም (WFP) እና የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም ይፋ ያደረጉት መረጃ እንደሚያሳየው በአሁኑ ወቅት በመላው አለም ከ800 ሚሊዮን በላይ ወገኖች በምግብ እጦትና በረሃብ አለንጋ እየተገረፉ ይገኛሉ።
በሚሊዮን የሚቆጠሩ ህፃናትና እናቶች የዕለት ጉርስ አጥተው በፀሎትና በተስፋ በሚጠባበቁበት በዚህ ወቅት በየቀኑ ከ2.5 ሚሊዮን ቶን በላይ የተዘጋጀ ምግብ ያላግባብ ይባክናል ብለዋል።
የዚህ ትልቅ ብክነት ዋና ምንጭ ትልልቅ ፋብሪካዎች ወይም ሱፐርማርኬቶች አለመሆናቸው ነው ድርጅቶቹ የገለጹት።
ከጠቅላላው የምግብ ብክነት ትልቁን ድርሻ 60 በመቶ የሚይዘው በየቤቱ የሚጣለው ምግብ ነው።
ሆቴሎችና ምግብ ቤቾች 28 በመቶ የሚሆነውን ያባክናሉ።
ሱፐርማርኬቶችና አነስተኛ ሱቆች ደግሞ 12 በመቶ ያህሉን ምግብ ያላግባብ ያስወግዳሉ ነው የተባለው።
የተባበሩት መንግስታት የአካባቢ ጥበቃ ፕሮግራም እንደሚለው የሚጣለው የምግብ አይነት ብቻ ሳይሆን እሱን ለማምረት የፈሰሰው ውኃ የወጣው ጉልበት የተደከመበት ለም መሬትና አየር ላይ የሚለቀቀው በካይ ጋዝ ጭምር ነው ብሏል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #foodprogram #unitednation #environment #supermarket #hotels #households

Comments