4 months ago
🛶 የጣናዋ ንግሥት!
የ55 ዓመቷ "ታንኳ ቀዛፊ" እና የሁለት ጊዜ የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ! 🥇
#ethiopia | "ታንኳ ለኔ ሕይወት ነው! እህትና ወንድሞቼን ያሳደግኩበት፤ ልጄን ያስተማርኩበት ባለውለታዬ ነው" - ወ/ሮ ፀሐይነሽ ጀምበር
ባሕር ዳር ከምትታወቅባቸው ልዩ እሴቶች መካከል ከፓፒረስ (ደንገል) የሚሰራው "ታንኳ" አንዱ ነው። ታንኳ ለቱሪስቶች የፎቶ ጌጥ ቢሆንም፤ እንደ ወይዘሮ ፀሐይነሽ ጀምበር ላሉት ግን የሕይወት እስትንፋስ ነው።
የወይዘሮ ፀሐይነሽ አስደናቂ ታሪክ:
🌊 የልጅነት ሸክም:
ገና በ15 ዓመታቸው ወላጆቻቸውን በሞት ሲነጠቁ፤ ታንኳ እየቀዘፉ እንጨትና ጨፌ ወደ ባሕር ዳር በማጓጓዝ ታናናሽ ወንድም እና እህቶቻቸውን አሳድገዋል።
🌊 የቤተሰብ ምሰሶ:
ባለቤታቸውን በሞት ሲያጡም አልተሸነፉም! ጣናን እና አባይን እየገመሱ በአንዲት ልጃቸው ምክንያት ተስፋ ሳይቆርጡ ኑሮን አሸንፈዋል።
🌊 የውድድር ጀግና:
በባሕር ዳር ፌስቲባል ላይ በታንኳ ቀዘፋ ውድድር የሁለት ጊዜ (የአንደኝነት እና የሁለተኛነት) የወርቅ ሜዳሊያ አሸናፊ ናቸው።
"ልጄ አንድ ቢሆንም ያለ ማንም እገዛ ትምህርት ቤት የሚመላለሰው ታንኳ እየቀዘፈ ነው" የሚሉት እኚህ ጠንካራ እናት፤ የታንኳ ቀዘፋ ሙያን ለትውልድ እያስተላለፉ ይገኛሉ።
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደርም ታንኳን እንደ ብስክሌት የከተማዋ መለያ (Brand) ለማድረግ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል።
ለእኚህ ጀግና እናት ክብር ይገባቸዋል! 👏❤️
ሮዛ የሻነህ (አሚኮ)
#bahirdar #laketana #tankua #strongwoman #ethiopianculture #tourism #amhara #inspiration