23 hours ago
#sphmmc
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ በ2019 ትምህርት ዘመን በሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ (Medicine) እና በአጠቃላይ ነርሲንግ (Comprehensive Nursing) ለመማር ያመለከታችሁ የመጨረሻ ውጤታችሁን ማየት ትችላላችሁ፦
Medicine: https://sphmmc.edu.et/2026...
Comprehensive Nursing: https://sphmmc.edu.et/2026...
የመግቢያ ቀን በቅርቡ ይገለጻል ተብሏል።
@tikvahuniversity ለ2019 ዓ.ም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ ለ2019 ዓ.ም በሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ (Medicine) እና በአጠቃላይ ነርሲንግ (Comprehensive Nursing) ለመማር ያመለከታችሁና #ለቃል_ፈተና የተመረጣችሁ ፈተናው መስከረም 21/ 2019 ዓ.ም በኮሌጁ ውስጥ ይሰጣል። ➻ በሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ ያመለከታቸሁ ጠዋት እና ከሰዓት ➻ በአጠቃላይ ነርሲንግ ለመማር ያመለከታችሁ…

6 days ago
ለ2019 ዓ.ም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ ለ2019 ዓ.ም በሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ (Medicine) እና በአጠቃላይ ነርሲንግ (Comprehensive Nursing) ለመማር ያመለከታችሁና #ለቃል_ፈተና የተመረጣችሁ ፈተናው መስከረም 21/ 2019 ዓ.ም በኮሌጁ ውስጥ ይሰጣል።
➻ በሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ ያመለከታቸሁ ጠዋት እና ከሰዓት
➻ በአጠቃላይ ነርሲንግ ለመማር ያመለከታችሁ በሙሉ ጠዋት ከ2፡30 ጀምሮ መስከረም 21/2019 ዓ.ም የሚሰጥ መሆኑን ኮሌጁ አሳውቋል።
ለቃል ፈተና የተመረጣችሁ አመልካቾች ዝርዝራችሁን በኮሌጁ ይፋዊ የማኅበራዊ ሚዲያ አድራሻ ማየት ትችላላችሁ።
@tikvahuniversity ለ2019 ዓ.ም ትምህርት ዘመን በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ በሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ (Doctor of Medicine) እና በአጠቃላይ ነርሲንግ (Comprehensive Nursing) ለመማር ላመለከታችሁ የመግቢያ ፈተና ነገ መስከረም 20/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ እንደሚሰጥ ኮሌጁ አሳውቋል፡፡ የመፈተኛ ጣቢያ እና የአመልካች ቁጥር በ https://sphmmc.edu.et/S…

8 days ago
ለ2019 ዓ.ም ትምህርት ዘመን በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ በሕክምና ዶክትሬት ዲግሪ (Doctor of Medicine) እና በአጠቃላይ ነርሲንግ (Comprehensive Nursing) ለመማር ላመለከታችሁ የመግቢያ ፈተና ነገ መስከረም 20/2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ጀምሮ እንደሚሰጥ ኮሌጁ አሳውቋል፡፡
የመፈተኛ ጣቢያ እና የአመልካች ቁጥር በ https://sphmmc.edu.et/Sche... አማካኝነት ማግኘት ትችላላቹ ተብሏል፡፡
@tikvahuniversity

11 days ago
#ጥቆማ
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ ለ2026/2027 የትምህርት ዘመን የድኅረ-ምረቃ አመልካቾች መቀበል ጀምሯል፡፡
አመልካቾች ሀገር አቀፍ የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (NGAT) ተፈትነው ያለፋ መሆን ይጠበቅባቸዋል፡፡ አመልካቾቹን የሚቀበለው የትምህርት ክፍል የፅሑፍ እና የቃል ፈተናዎች ይሰጣል፡፡
የሕክምና ትምህርት ቤት (በመደበኛ መርሐግብር)
ስፖንሰር፦ በግል ወይም በመንግሥት
ፕሮግራሞች፦ በአራት የMSc ትምህርት መስኮች
የኅብረተሰብ ጤና ትምህርት ቤት (በመደበኛ እና በዕረፍት ቀናት መርሐግብር)
ስፖንሰር፦ በግል ወይም በመንግሥት
ፕሮግራሞች፦ በስድስት የMPH ትምህርት መስኮች
የነርሲንግ ትምህርት ቤት (በመደበኛ መርሐግብር)
ስፖንሰር፦ በግል ወይም በመንግሥት
ፕሮግራሞች፦ በስምንት የMSc ትምህርት መስኮች
የምዝገባ ጊዜ የሚያበቃው 👇
መስከረም 27/2019 ዓ.ም
ለተጨማሪ መረጃ፦
https://portal.sphmmc.edu....

Sponsored by
Surafel
3 months ago
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የ2018 የክረምት በጎ ፈቃድ ነጻ ህክምናን በይፋ ጀመረ
#ethiopia | የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ የ2018 የክረምት በጎ ፈቃድ ነጻ ምርመራ እና የህክምና አገልግሎትን በይፋ ጀመረ።
በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ በተካሄደው መርሐግብር ላይ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ሎሚ በዶ በመድረኩ የመክፈቻ ንግግራቸው እንደገለጹት " የክረምት ወራት በሀገራችን የምንረዳዳበት እና የምንደጋገፍበት ወቅት ነው ብለዋል።
ያለንን ውስን ሀብት በመጠቀም ሀገራችንን ማልማት ይጠበቅብናል ያሉት ክብርት ወ/ሮ ሎሚ በበጎ ፈቃድ አገልግሎት በመሳተፍ ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች እና በጎ ፈቃደኞች በምክር ቤቱ ስም ምስጋና አቅርበዋል።
በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አነሳሽነት የተጀመረው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አሁን ላይ ለሌሎች ሀገራት ተምሳሌት የሚሆንበት ደረጃ ላይ መድረሱን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ በመድረኩ ተናግረዋል። የበጎ ፈቃድ አገልግሎትን በጤና ስርዓት ውስጥ በማካተት ባለፈው አመት ብቻ ለ15 ሚሊዮን ዜጎች ነፃ የህክምና አገልግሎት ማቅረብ መቻሉንም ግልጸዋል።
በክረምት ወራት በጎ ፈቃድ ብቻ ባለፈው ክረምት 176,000 ዩኒት ደም መሰብሰቡን እና የህክምና መሳሪያዎች ጥገና በማካሄድ ሃብትን ከብክነት ማትረፍ መቻሉንም አክለዋል።
የዚህ አመት የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት ከሀገር ግንባታ ጋር በማያያዝ የሚካሄድ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ደኤታ ዶ/ር ደረጄ ዱጉማ ገልጸዋል በጎነት ለጤናው ዘርፍ የዘወትር ስራ መሆኑን ጠቁመው በዚህ ክረምት እስከ 20 ሚሊዮን የሚሆኑ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን ተናግረዋል።
ለቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የክረምት በጎፈቃድ አገልግሎት ድጋፍ እያደረጉ ለሚገኙ ተቋማት እና የግል ሆስፒታሎች ምስጋና ያቀረቡት የሆስፒታሉ ፕሮቭኦስት ዶ/ር ሙሉቀን ተስፋዬ: ሆስፒታሉ ከመሰረቱ ማህበረሰቡን ማዕከል አድርጎ የተቋቋመ መሆኑን አስታውሰዋል።
በመርሃ ግብሩ የህዝብ ተዋካዮች ምክር ቤት የጤና ማህበራዊ ልማት፣ ባህል እና ስፖርት ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የጤና ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማት አመራሮች፣ የግል ሆስፒታል ኃላፊዎች፣ የሆስፒታሉ አመራር እና ተግልጋዮች የተሳተፉ ሲሆን፣ ነጻ የጤና ምርመራ፣ የምክርና ህክምና አግልግሎት መስጠት ተጀምሯል።
በተጨማሪም በዚህ ክረምት መርሃ ግብር የሆስፒታሉን ድንገተኛ የህክምና አገልግሎት መስጫ ክፍልን በአዲስ መልክ ለመገንባትና ለማደራጀት የሚያስችል ስራ የተጀመረ ሲሆን ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ እና በሆስፒታሉ እየተሰጠ የሚገኘው አገልግሎት ጉብኝት ተካሂዷል።
Ministry of Health,Ethiopia
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ጌጡ
#stpaulshospital #sphmmc
#volunteermedicalservice
#freehealthcare #ethiopia
#healthcareforall

4 months ago
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ለዶክተር ሰለሞን አሊ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አፀደቀ
#ethiopia | የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ ማኔጅመንት ቦርድ ሰኔ 9 ቀን 2018 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ ለዶክተር ሰለሞን አሊ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታውቋል።
ኮሌጁ የባለሙያውን ሰነዶችና የስራ አፈፃፀም በዝርዝር ከገመገመ በኋላ ይህንን ከፍተኛ የትምህርት ማዕረግ አፅድቆላቸዋል።
ፕሮፌሰር ሰለሞን አሊ በህክምና ምርምርና በማይክሮባዮሎጂ ዘርፍ በስፋት የሚታወቁ አንጋፋ ስፔሻሊስት ናቸው።
የምርምር ስራዎቻቸውም በዋናነት በተላላፊ በሽታዎች፣ በፀረ ጀርም መድኃኒቶች መላመድ እንዲሁም አዲስና ዳግም በሚቀሰቀሱ የቫይረስ አይነቶች ላይ ያተኮሩ ናቸው።
ፕሮፌሰሩ ባለፉት 20 ዓመታት በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅና በጅማ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በመምህርነት፣ በምርምርና በሕክምና አገልግሎት አገራቸውን በቅንነት ያገለገሉ ዓለም አቀፍ ተሞክሮ ያላቸው ምሁር ናቸው።
በማስተማር ስራቸውም በርካታ የሕክምና፣ የጤና ሳይንስ፣ የማይክሮባዮሎጂና የክሊኒካል ሬዚደንት የቅድመና ድህረ ምረቃ ተማሪዎችን አፍርተዋል።
እስካሁንም በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ባላቸው የምርምር መጽሔቶች ላይ 56 የምርምር ውጤቶችን ያሳተሙ ሲሆን ስድስት ታላላቅ ዓለም አቀፍ የትብብር የምርምር ፈንዶችንም ማሸነፍ ችለዋል።
በተጨማሪም ፕሮፌሰር ሰለሞን አሊ የሀገሪቱን የምርምርና የማይክሮባዮሎጂ አገልግሎት መሠረተ ልማት ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና ተጫውተዋል።
በዚህም በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሕክምና ኮሌጅ የመጀመሪያውን የጤና ምርምር መጽሔት፣ ዘመናዊ የተላላፊ በሽታዎች የዘረመል ምርምር ላቦራቶሪ፣ ለቀጣይ ጥናቶች የሚሆኑ ናሙናዎችን ለረጅም ጊዜ ማቆያ ማዕከልና የማይክሮባዮሎጂ መረጃዎችን በዲጂታል መንገድ የማደራጃ ሥርዓት መስርተዋል።
ፕሮፌሰር ሰለሞን አሊ በጤናው ዘርፍ ላበረከቱት የላቀ ሙያዊ አስተዋፅኦ በቅርቡ ከጤና ሚኒስቴር የ2018 ዓ.ም የብሔራዊ እውቅና ሽልማት መበርከቱ ይታወሳል።
The Managing Board of Saint Paul’s Hospital Millennium Medical College (SPHMMC), at its regular meeting held today, June 16, 2026, approved the promotion of Dr. Solomon Ali to the rank of Full Professor.
After carefully reviewing her academic, clinical, research, and service achievements, the Board endorsed his promotion in recognition of his outstanding contributions to medical education, research, and institutional leadership
Professor Solomon Ali is a distinguished microbiologist and medical research specialist whose work focuses on infectious diseases, antimicrobial resistance, and emerging/reemerging viral pathogens.
He has served his country for over 20 years at St. Paul’s Hospital Millennium Medical College (SPHMMC) and Jimma University (JU), contributing extensively to academic, clinical, and research activities.
Professor Solomon has trained, mentored, and supervised undergraduate, Master’s, and PhD students, guiding numerous research theses. Throughout his academic and research career, he has published more than 56 articles in reputable international journals and has secured six major competitive international research grants. Prof. Solomon has also played a pivotal role in strengthening research and health service infrastructures.
He has established Millennium Journal of Health, the first scholarly journal in SPHMMC, Infectious Diseases Research and Molecular Laboratory (IDReaM Lab) with integrated bio-banking system, and digitalizing hospital microbiology service laboratory data management system through a DHIS2 based platform.
Recently, Prof. Solomon Ali received national recognition from the Federal Ministry of Health of Ethiopia as the recipient of the 2026 Award for outstanding professional contribution in the health sector.
#stpaulshospital #medicalresearch #microbiology #educationethiopia #healthethiopia #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

8 months ago
"አንዲትም እናት በወሊድ ምክንያት መሞት የለባትም!"
— በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ለጋዜጠኞች የተሰጠ ልዩ ስልጠና
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ (SPHMMC) ከ SPIRHR ጋር በመተባበር፣ በሚዲያ ባለሙያዎች አማካኝነት የእናቶችን ሞት ለመቀነስ ያለመ ወሳኝ የንቅናቄ ስልጠና ዛሬ አካሂዷል።
📊 ለምን ትኩረት ያስፈልጋል? (ቁልፍ ጥናቶች እና ዳታ)
በስልጠናው ላይ የቀረቡና በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት፣ በእናቶች ጤና ዙሪያ አሁንም ትልቅ የቤት ስራ ይጠብቀናል፦
ገዳዩ መንስኤ፦ በኢትዮጵያ ለሚከሰተው የእናቶች ሞት ከ30% በላይ የሚሆነው በወሊድ ወቅት በሚከሰት ከፍተኛ የደም መፍሰስ (PPH) ምክንያት ነው። ይህ ደግሞ በደም ባንክ አቅርቦትና በፈጣን የህክምና እርዳታ መከላከል የሚቻል ነው።
የክትትል ክፍተት፦ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት፣ ቢያንስ 4 እና ከዚያ በላይ የቅድመ ወሊድ ክትትል (ANC) የሚያደርጉ እናቶች፣ ካልተከታተሉት ጋር ሲነፃፀሩ በወሊድ ወቅት ለሞት የመጋለጥ እድላቸው በከፍተኛ መጠን ይቀንሳል። ሆኖም በሀገር አቀፍ ደረጃ ሁሉንም ክትትል የሚያደርጉ እናቶች ቁጥር አሁንም ማደግ ይኖርበታል።
የሰለጠነ የሰው ኃይል፦ በቤት ውስጥ የሚደረግ ወሊድ ለእናቶች ሞት ዋነኛ መንስኤ መሆኑ የተጠቀሰ ሲሆን፣ በጤና ተቋም በሰለጠነ ባለሙያ መውለድ የሞት ምጣኔን እስከ 80% የመቀነስ አቅም እንዳለው የዘርፉ ጥናቶች ያረጋግጣሉ።
💡 የሚዲያው ሚና እና የቀረበ ጥሪ
"ጋዜጠኝነት ህይወት ያድናል!" በሚል መንፈስ በቀረበው ስልጠና ላይ፣ እናቶች ስለሚከተሉት ነጥቦች ግንዛቤ እንዲኖራቸው ሚዲያው እንዲሰራ ተጠይቋል፡-
የአደጋ ምልክቶች፦ በእርግዝና ወቅት የሚታዩ እንደ እግር እብጠት፣ ራስ ምታት እና ደም መፍሰስ ያሉ ምልክቶች የታዩባት እናት በአስቸኳይ ህክምና ማግኘት እንዳለባት።
የደም ልገሳ ባህል፦ እናቶች በደም እጥረት እንዳይሞቱ የደም ልገሳ ባህል ማደግ እንዳለበት።
የድህረ ወሊድ ክትትል፦ ብዙ እናቶች ከወለዱ በኋላ ክትትል እንደማያደርጉ የተጠቀሰ ሲሆን፣ ከወሊድ በኋላ ባሉት 42 ቀናት ውስጥ የሚከሰቱ ችግሮችን ለመከላከል ክትትል ወሳኝ መሆኑ ተብራርቷል።
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ባለሙያዎች እንደገለጹት፣ እናቶች በጤና ተቋማት የሚሰጡ አገልግሎቶችን በሙሉ ልብ እንዲጠቀሙ የሚዲያ ተቋማት መረጃን ተደራሽ የማድረግ ኃላፊነት አለባቸው።
"ጤናማ እናት፣ ጤናማ ትውልድ!"

በእናቶች ጤና ዘገባ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ!
#fastmereja I የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ (SPHMMC) ከቅዱስ ጳዉሎስ ሆስፒታል የማህፀን እና ፅንስ ትምህርት ክፍል(SPIRHR )ጋር በመተባበር በዛሬዉ እለት ከግል፣ ከመንግስት እና ከኦንላይን የሚዲያ ተቋማት ለተውጣጡ ጋዜጠኞች በእናቶች ጤና ዘገባ ላይ ስልጠና ሰጥቷል።
ስልጠናዉ በእናቶች ጤና ፣እርግዝና፣ ልጅ መውለድ እና ከወሊድ በኋላ እንክብካቤን እንዲሁም የእናቶች ሞት ዋና ዋና ምክንያቶችን እንዲሁም የቅድመ ወሊድ እንክብካቤ እና የክህሎት የወሊድ አገልግሎቶች ዙሪያ በዘርፉ ባለሙያዎች ሰፊ ገለፃ ተደርጓል።
እናቶች በጤና ተቋም ተገቢውን የቅድመ ወሊድ ክትትል እንዲያደርጉ ለማስቻል የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መስራት እንደሚገባም ተገልጿል።
እንዲሁም በወሊድ ወቅት የደም መፍሰስ የሚያስከትለውን ሞት ለመቀነስም ከደም ባንኮች ጋር በቅርበት በመስራት በወሊድ ወቅት የሚከሰተዉን ሞት መቀነስ እንደሚቻልም ተጠቁሟል።
እናቶች በጤና ተቋማት ስለሚሰጡ አገልግሎቶች የጠራ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና የአገልግሎት ተጠቃሚ በመሆን የራሳቸውን ጤና እንዲጠብቁ አሳስቧል።
በመድረኩ በጤና ተቋማት ስለሚሰጡ አገልግሎቶችና የእናቶች ቅድመ ወሊድና ድህረ ወሊድ አስፈለጊነት ዙሪያ በባለድርሻ አካላት ማብራሪያ የተሰጠ ሲሆን በተሰጠው ማብራሪያ ዙሪያ ውይይት ተደርጓል።

Comments