8 months ago
የኢትዮጵያ ድል በሲቪያ ማራቶን፦ ሹራ ቂጣታ በፎቶ ፊኒሺንግ አሸነፈ! 🥇🏃♂️
በስፔን ሲቪያ በተካሄደው 41ኛው የማራቶን ውድድር፣ የኢትዮጵያ አትሌቶች በወንዶች ምድብ ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመግባት የድል አርማቸውን ከፍ አድርገው አውለብልበዋል።
ታሪካዊው ትንቅንቅ፦
በአትሌት ሹራ ቂጣታ እና አስራር ሀይረዲን መካከል እስከ መጨረሻዋ መስመር የተደረገው ትንቅንቅ የበርካቶችን ቀልብ ስቦ ነበር። ሁለቱም 2፡03.59 በሆነ እኩል ሰዓት ቢገቡም፣ በፎቶ ፊኒሺንግ (Photo Finish) ሹራ ቂጣታ ቀዳሚ በመሆን አሸናፊ ሆኗል። ደጀኔ ሃይሉ ደግሞ በ2፡04.15 3ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቅቋል።
ሌሎች ውጤቶች፦
🏅 ወንዶች፦ ካፒታል ደገፋ፣ ፅዳት አበጀ፣ ፈይሳ ሙሉ እና ልመንህ ጌታቸው ከ5ኛ እስከ 8ኛ በመውጣት በደረጃ ሰንጠረዡ የኢትዮጵያን የበላይነት አሳይተዋል።
🥉 ሴቶች፦ በሴቶች ምድብ አትሌት ሙላት ተክሌ 2፡22.03 በሆነ ሰዓት 3ኛ ደረጃን በመያዝ ለሀገሯ የነሐስ ሜዳሊያ አስገኝታለች። በምድቡ ፊንላንዳዊቷ አሊሳ ቫይኒዮ አሸናፊ ሆናለች።
በዓለም አቀፍ መድረክ ሀገራቸውንና ባንዲራቸውን ከፍ ላደረጉ አትሌቶቻችን እንኳን ደስ አላችሁ! 👏
#ethiopia #sevillemarathon #athletics #shurakitata #marathonvictory #spain #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን

Comments