19 days ago
የምርጫ ቦርድ የክትትል ቡድኖች በምርጫ አካባቢዎች ላይ ያጠኑትን የፀጥታ ሪፖርት አቀረቡ
**************
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 7ኛው ጠቅላላ ምርጫ በሚካሄድባቸው አካባቢዎች ላይ ሥምሪት ሰጥቷቸው የነበሩ የክትትል ቡድኖች ያጠኑትን ዝርዝር ሪፖርት በይፋ ተረክቧል።
ቦርዱ ቀደም ሲል በጥር ወር 2018 ዓ.ም. ከተለያዩ ተቋማት የተሰበሰበውንና በአረንጓዴ፣ ቢጫና ቀይ የተፈረጀውን የፀጥታ መረጃ መሠረት በማድረግ ውይይቶችን አድርጓል።
ይሁን እንጂ ከመንግሥት አካላትና ከተፎካካሪ ፓርቲዎች በደረሱ መረጃዎች መካከል የነበሩትን ልዩነቶች በጥልቀት ለመመርመር መጋቢት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. የጋራ የክትትል ቡድን አዋቅሮ ሥምሪት ሰጥቷል።
ከፓርቲዎች፣ ከሲቪል ማኅበረሰብና ከቦርዱ የተውጣጡትና በዘጠኝ ንዑሳን ቡድኖች የተደራጁት እነዚህ አካላት ያከናወኑትን የመስክ ምልከታ አጠናቀው ግንቦት 6 ቀን 2018 ዓ.ም. ሪፖርታቸውን አቅርበዋል።
የመድረኩን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ የክትትል ቡድኑ መሬት ላይ ያለውን ተጨባጭ ሁኔታ አጣርቶ ሥራውን በማጠናቀቁ ምስጋና አቅርበዋል።
የዚህ መድረክ ዋነኛ ዓላማ የቀረበውን የጥናት ውጤት በማድመጥ ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥና የባለድርሻ አካላትን ኃላፊነት በምክረ-ሐሳብ ለማበልጸግ መሆኑንም ገልጸዋል።
በቀረበው ሰፊ ሪፖርት ላይ ከፀጥታ ሁኔታው ባሻገር የየአካባቢዎቹ የፖለቲካ ምኅዳርና ፓርቲዎች በነፃነት ተንቀሳቅሰው ለመሥራት ያላቸው አስቻይ ሁኔታ ተዳሷል። በተጨማሪም የሕዝቡ ተነሳሽነትና የምርጫ ካርድ አወሳሰድ ሒደትን ጨምሮ በርካታ ወሳኝ ጉዳዮች ተመልክተዋል።
ይህ የክትትል ሪፖርት በአብዛኛዎቹ የምርጫ አካባቢዎች ላይ ሂደቱን ለማስቀጠል የሚያስችል ምቹ ሁኔታ መኖሩን ቢያረጋግጥም፣ አሁንም ልዩ ትኩረት የሚሹ ቦታዎች መኖራቸውን አመልክቷል።
በጥናቱ ግኝቶች ላይ የቦርዱ ሰብሳቢ ሜላትወርቅ ኃይሉ እና ምክትል ሰብሳቢው ተስፋዬ ንዋይ መድረኩን በመምራት ከተሳታፊዎች ጋር ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱም ስለ አጠቃላይ የፀጥታና መዋቅራዊ ተግዳሮቶች እንዲሁም መወሰድ ስለሚገባቸው የዕርምት ዕርምጃዎች ሰፊ ሐሳብ ተንጸባርቋል።
የተሳታፊ ፓርቲዎችና የሲቪል ማኅበረሰብ ተወካዮች ቦርዱ በቀጣይ ሊያደርገው ስለሚገባው ጥብቅ ቁጥጥር ገንቢ አስተያየቶችን የሰጡ መሆኑን ከምርጫ ቦርድ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
#ethiopianbroadcastingcorporation #nebe #ethiopianelection #securityreport

Comments