4 months ago
"የኢትዮጵያ አጥቂዎች በፖርቹጋል ዋናው ሊግ መጫወት ይችላሉ" — ሪካርዶ ሞንሳንቶ
#ethiopia | የሳኦ ቶሜ እና ፕሪንሲፔ ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሪካርዶ ሞንሳንቶ፣ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጋር ካደረጉት ጨዋታ በኋላ ለዋልያዎቹ የፊት መስመር ተጫዋቾች ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል። አሰልጣኙ የኢትዮጵያ አጥቂዎች ያላቸው ብቃት በአውሮፓ መድረክ በተለይም በፖርቹጋል የመጫወት ዕድል ሊሰጣቸው እንደሚችል ምስክርነታቸውን ሰጥተዋል።
አሰልጣኝ ሞንሳንቶ በጨዋታው ላይ ልዩ ብቃት አሳይተዋል ያሏቸውን ተጫዋቾች በስም በመጥቀስ እንዲህ ብለዋል፦
"አቤል ያለው፣ ቸርነት እና መስፍን ልዩ የሆኑ ተጫዋቾች ናቸው። እነዚህ ተጫዋቾች በፖርቹጋል የመጀመሪያ ሊጎች ውስጥ ገብተው የመጫወት ሙሉ ብቃት አላቸው።"
አሰልጣኙ ቡድናቸው ላጋጠመው ፈተና የሜዳ ማጣትን እንደ ምክንያት አንስተዋል፦
* ባለፉት አራት ዓመታት በገዛ ሜዳቸውና በደጋፊያቸው ፊት የመጫወት ዕድል እንዳልነበራቸው ገልጸዋል።
* በኢትዮጵያ በደጋፊ ፊት መጫወታቸውን እንዳስደሰታቸው ጠቁመው፣ "በሜዳችን ተጫውተን ቢሆን ኖሮ ውጤቱ እንዲህ አይሆንም ነበር" ሲሉ ተደምጠዋል።
ስለ ስፖርቲንግ ሊዝበን አስተያየት
ከጨዋታው በፊት ስለ ስፖርቲንግ ሊዝበን ሰጥተውት ለነበረውና መነጋገሪያ ለሆነው አስተያየት ከቲክቫህ ስፖርት ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱ፦
"ያንን ያወራሁት ተጫዋቾቼን ለማነቃቃት እንጂ ለሌላ አልነበረም" በማለት ጉዳዩን ግልጽ አድርገዋል።
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #ethiopia #walias #saotomeandprincipe #ricardomonsanto #totalenergiesafcon #ethiopianfootball #footballnews

Comments