4 months ago
የአንጋፋው ድምፃዊ ጥላዬ ጨዋቃ ስራዎች ህያው ሆነው ይኖራሉ
#ethiopia | "ምስጉኑ ሾፌር"፣ "ንቦዬ"፣ "ኮረሪማ" እና "መምህሩ" በሚሉና በሌሎች በርካታ ተወዳጅ ዜማዎቹ የሚታወቀው አንጋፋው ድምፃዊ ጥላዬ ጨዋቃ በህመም ምክንያት ከዚህ ዓለም በሞት ተለይቷል።
ጥላዬ ጨዋቃ በ1961 ዓ.ም ከወዳጅ ዘመዶቹ ጋር "ደህና ሁኝ አዳማ" ብሎ ከተለያየ በኋላ፣ የምድር ጦር ኦርኬስትራን በመቀላቀል ለረጅም ዓመታት በኮከብ ድምፃዊነት አገልግሏል።
ማህበራዊ ጉዳዮችን በሙዚቃው በማቀንቀንና ለሀገሩ ትልቅ ውለታ በመዋል የሚታወቅ ጨዋታ አዋቂ የጥበብ ሰው ነበር።
ሲመኝ የነበረው ጊዜው ሞልቶለታል
አስተምሮ ሊማር ወደ ገጠር ዘምቷል ...
ጥላዬ ጨዋቃ 🙏
የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ትናንት መጋቢት 19 ቀን 2018ዓ.ም በቤተል ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ተፈጽሟል።
ለቤተሰቦቹ፣ ለወዳጅ ዘመዶቹና ለአድናቂዎቹ መጽናናትን እንመኛለን። ስራዎቹ ግን ሁልጊዜም ሲዘከሩ ይኖራሉ።
ነፍስ ይማር! 🙏✨
#ጥላዬጨዋቃ #ኢትዮጵያ #ሙዚቃ #ሀዘን #ትዝታ #ምድርጦርኦርኬስትራ #tilaayechewaqa #ethiopianmusic #legend #riptilaaye #ethiopia

Comments