1 month ago
በቅዱስ ላሊበላ ደብር የብራና አጻጻፍና የቅዱሳት ሥዕላት ሥልጠና እየተሰጠ ነው
♦️ ህብረተሰቡ "መስተፋቅር እንሠራለን" በሚሉ አታላዮች እንዳይታለል ተጠየቀ
#ethiopia | በቅዱስ ላሊበላ ደብር በጥንታዊ የብራና አጻጻፍ፣ በቅዱሳት ሥዕላት፣ በቁም ጽሑፍና በቤተ ክርስቲያን ዜማ ትምህርቶች ላይ ያተኮረ ሥልጠና ከ30 በላይ ለሚሆኑ ተማሪዎች እየተሰጠ ይገኛል።
በቅዱስ ላሊበላ ደብር ተወልደው ያደጉትና በኢትዮጵያ የተለያዩ አካባቢዎች በመሄድ የቤተ ክርስቲያን ከፍተኛ ትምህርታቸውን ያጠናቀቁት አሁን ላይ በደብሩ እያገለገሉ የሚገኙት መምህር ልሳነ ጥበብ ሸዋንግዛው፣ የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥንታዊ የብራና አጻጻፍና የቅዱሳት ሥዕላት ጥበብ ለትውልድ ከማስተላለፍ ባለፈ ለውጭና ለአገር ውስጥ ጎብኚዎች በማስተዋወቅ ላይ ናቸው።
አሁን ላይ ደብሩ አዳሪ ትምህርት ቤት በመክፈትና በቋሚነት በጀት በመደብ 30 ተማሪዎችን በሥዕል፣ በቁም ጽሑፍ፣ በብራና ዝግጅትና በድግሰት ዘርፍ በማሰልጠን ላይ ይገኛል። ከወንዶች በተጨማሪ ሴቶችም በሚሳተፉበት በዚህ ትምህርት እንደ አቋቋም፣ ዜማ፣ ጾመ ድጓ፣ ንባብና ዳዊት ያሉ የቤተ ክርስቲያን ትምህርቶች ጎን ለጎን የሚሰጡ ሲሆን፣ በቅርቡም በርካታ ተማሪዎች ተመርቀው ለተግባራዊ ሥራ መብቃታቸው ተገልጿል።
መምህር ልሳነ ጥበብ ሸዋንግዛው እንደሚገልጹት፣ የሚሠሩት ማንኛውም የብራና ጽሑፍም ሆነ የቅዱሳን ሥዕል ከቤተ ክርስቲያኗ አስተምህሮ ውጭ ያልሆነ፣ የሃይማኖቷ መገለጫና የታሪክ ማስተላለፊያ ሀብት ነው።
መምህሩ ጥንታዊውን የብራና ጽሑፍ እና የቤተ ክርስቲያን ሥዕል ለትውልድ የሚያስተላልፉ፣ የእግዚአብሔርን ቃል የሚያስተምሩና ደቀ መዛሙርትን የሚያሰለጥኑ መንፈሳዊ አባት እንጂ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት አስተምህሮ ውጭ ከሚደረጉ መጥፎ ተግባራት ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት እንደሌላቸው ገልጸዋል።
ሆኖም ግን በቅርብ ጊዜያት ወዲህ ጥቂት አታላይ ግለሰቦች በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ቴክኖሎጂን በመጠቀም የመምህር ልሳነ ጥበብ ሸዋንግዛውን እና የሌሎች ሊቃውንትን ምስልና ድምፅ በመቀየር "መርጌታ እገሌ ነኝ፣ መስተፋቅር እንሠራለን፣ የገበያ እናስከፍታለን፣ የጠፋ ፍቅር እንመልሳለን፣ የወደቀን እናቃናለን" በሚሉ አሳሳችና ጸያፍ ማስታወቂያዎች ሕዝቡን እያታለሉ ይገኛሉ።
ይህ ድርጊት የመምህሩን መልካም ስም ለማጎደፍ፣ የላስታ ላሊበላን መንፈሳዊ ታሪክ ለማራከስና በማኅበረሰቡ መካከል አላስፈላጊ ግጭት ለመቀስቀስ የታቀደ እኩይ ሴራ በመሆኑ፣ ድርጊቱ የቅዱስ ላሊበላን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን፣ የላስታን ጨዋ ሕዝብ፣ የቅዱስ ላሊበላ ደብርን እንዲሁም የካህናት አባቶችንና ሊቃውንትን ሙሉ በሙሉ የማይወክል መሆኑ ተገልጿል።
ስለሆነም ሕዝቡ በእነዚህ አታላዮች ሳይታለል አስፈላጊውን ጥንቃቄ እንዲያደርግና በቤተ ክርስቲያኗ፣ በካህናት አባቶችና በሊቃውንት ስም የሚነግዱ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ጥሪ ቀርቧል።
ጌትነት ተመስገን
ከ ላስታ - ላሊበላ
#lalibela #ethiopia #lalibelamonastery #ethiopianorthodox #ethiopianheritage #parchmentart #ethiopianmanuscripts #sacredart #traditionalarts #aifake #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments