4 months ago
🇺🇸🇪🇹 "ግድቡ የናይልን ውሃ ዘግቷል... ነገር ግን ሁለታችሁንም ለማገናኘት እሞክራለሁ" - ዶናልድ ትራምፕ
#ethiopia | ትራምፕ በድጋሚ የግብፅን አቋም የሚያንጸባርቅ አወዛጋቢ አስተያየት ሰጡ!
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከግብፁ ፕሬዝዳንት አብደል ፋታህ አል-ሲሲ ጋር ባደረጉት ውይይት፤ በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የግብፅን አቋም የሚደግፍ ንግግር ማድረጋቸው ተሰምቷል።
ትራምፕ ምን አሉ?
1️⃣ "ውሃው ተዘግቷል":
ትራምፕ ስለ ግድቡ ሲናገሩ፤ "ድንገት የውሃው ፍሰት በጣም ግዙፍ በሆነ ግድብ ተዘግቷል፤ ለአንድ ሚሊዮን ዓመታት ያህል ሲያገኙት የነበረውን ውሃ እንዳያገኙ ተደርጓል" ሲሉ ተደምጠዋል። እሳቸውም በግብፅ ቦታ ቢሆኑ እንደማይደሰቱ ገልጸዋል።
2️⃣ ስለ መሪዎቹ:
የግብፁን ፕሬዝዳንት "በጣም ጠንካራ መሪ" ሲሉ ያሞገሱት ትራምፕ፤ ስለ ኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትርም "አንተን እንደማውቅህ በደንብ ባላውቃቸውም፤ ኢትዮጵያም ጠንካራ መሪ አላት" ሲሉ ተናግረዋል።
3️⃣ ሽምግልና:
ጉዳዩ "በጣም አደገኛ ደረጃ" ላይ መድረሱን የጠቁሙት ትራምፕ፤ የተቋረጠውን ድርድር ለማስቀጠል እና ሁለቱን መሪዎች ለማገናኘት እንደሚሞክሩ ቃል ገብተዋል።
ይህ የትራምፕ አስተያየት በግድቡ ዲፕሎማሲ ላይ ምን ተፅእኖ ይኖረው ይሆን?
Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን)
#gerd #ethiopia #egypt #donaldtrump #niledam #diplomacy #abiyahmed #sisi