1 month ago
አህቴን በጀርባዬ አዝዬ ወላጆቼን እፈልጋለሁ!
#ethiopia | ታዳጊው በኔፓል ሰሞኑ በተከሰተው የጎርፍ አደጋ ታናሽ እህቱን በጀርባው በማዘል በሞት የተነጠቁትን ወላጆቹን በመፈለግ ላይ ይገኛል።
ይህ ታዳጊ በአደጋው ምክንያት ወላጆቹ በሞት የተለዩ ቢሆንም ከዛሬ ነገ ይገኛሉ በሚል ተስፋ ዛሬም ድረስ ፈለጋውን አላቋረጠም።
ገና ነፍስ ያላወቀው ይህ ታዳጊ ህጻን እምቦቅቅላ እህቱን አዝሎ ወላጆቹን በመፈለግ ተጠምዷል።
አደጋው ተከትሎ የወጡ መረጃዎች እንደሚያሳዩት ከ400 በላይ ህጻናት ከቤተሰቦቻቸው ተለይተው እንደሚገኙ ጠቁሟል።
የጎርፍ አደጋው ከ90,000 በላይ ሰዎችን ያፈናቀለ ሲሆን ከ700 በላይ ሰዎች ህይወታቸውን አሳጥቷል።
በተጨማሪም በርካቶች እስካሁን የት እንደደረሱ ደብዛቸው ጠፍቷል።
አለም አቀፍ የእርዳታ ድርጅቶች በሺዎች የሚቆጠሩ ህፃናት ከአደጋው ጋር ተያይዞ አስቸኳይ የሰብአዊ እርዳታ ይሻሉ ብለዋል።
ከቤተሰቦቻቸው የተለያዩ ህፃናት ደግሞ ከወላጆቻቸው የማገናኘት ስራ እየተሰራ ይገኛል።
ሔኖክ ወ/ገብርኤል
#ethiopia #getutemesgen #nepalfloods #nepal #floods #heartbreaking #naturaldisaster

4 months ago
ፊሊፒንስ : በመሬት መንቀጥቀጥ የ 32 ሰዎች ሕይወት አለፈ
#ethiopia | በደቡባዊ ፊሊፒንስ ሚንዳናኦ ደሴት አቅራቢያ ያጋጠመ እና በሬክተር ስኬል 7.8 መለኪያ የተመዘገበ ከፍተኛ የመሬት መንቀጥቀጥ አደጋ የ32 ሰዎችን ሕይወት ማለፉ ተረጋግጧል።
የአገሪቱ ይፋዊ መግለጫዎች እንደሚያመለክቱት ከሟቾቹ በተጨማሪ ከአንድ መቶ በላይ የሚሆኑ ዜጎች ላይ የተለያዩ የአካል ጉዳቶች ደርሰዋል።
ይህ አውዳሚ የተፈጥሮ አደጋ መጀመሪያ ላይ በፊሊፒንስ፣ ኢንዶኔዥያ፣ ጃፓን እና አውስትራሊያ የባሕር ሞገድ ወይም የሱናሚ ሥጋት አሳድሮ የነበረ ቢሆንም፣ የተሰጡት የቅድመ ማስጠንቀቂያዎች ብዙም ሳይቆዩ ተነስተዋል።
አደጋው በመኖሪያ አካባቢዎች ላይ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት እና የሕንፃዎች መደርመስ ምክንያት በተለይም በሳራንጋኒ እና በጄኔራል ሳንቶስ ክልሎች ላይ ከፍተኛ ውድመት አድርሷል።
እስከ አሁን ድረስ የሃያ ሰዎች ደብዛ የጠፋ ሲሆን፣ ወደ አሥር ሺሕ የሚጠጉ ነዋሪዎች ደግሞ ደህንነታቸው ወደተጠበቀ ስፍራ ለመሸሽ ከቀያቸው ለመፈናቀል መገደዳቸው ታውቋል።
የአገሪቱ ፕሬዝዳንት ፈርዲናንድ ማርኮስ ጁኒየር የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች የአደጋውን ጉዳት ለመቀነስ እና ድጋፍ ለማቅረብ በቅንጅት እየሰሩ መሆኑን ገልጸዋል።
እንደ ቢቢሲ ዘገባ ከሆነ በአካባቢው የሚገኙ የትምህርት ተቋማትም ለጊዜው ተዘግተው እንዲቆዩ ትዕዛዝ ተላልፏል።
#digitalhagerie #earthquake #philippines #naturaldisaster #asianews #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments