1 month ago
በ2019 በጀት ዓመት ኩባንያችን ሰፊ ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኢንቨስትመንቶችን በማድረግ የሀገራችንን ዕድገት ለማፋጠንና የዜጎችን ሕይወት ለመቀየር በርካታ ቁልፍ ስትራቴጂያዊ ሥራዎችን ለማከናወን አቅዷል፡፡
በዚህም መሠረት በበጀት ዓመቱ ከ644,000 በላይ ለሚሆኑ የምህዳር አጋሮቻችን (ወኪሎች፣ አቅራቢዎችና የVAS አጋሮች) የገቢ ምንጭ የሚፈጥር ሲሆን፤ ከ49,200 በላይ ለሚሆኑ ሠራተኞችም አስተማማኝ የሥራ ዕድል እንዲቀጥል ያደርጋል።
በተጨማሪም ቀደም ሲል የተፈጠሩ 2.4 ሚሊዮን ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆኑ የገቢ ምንጮችን በማስቀጠል፣ ተጨማሪ 163,375 አዳዲስ ቀጥተኛ የሥራ እና የገቢ ዕድሎችን ለመፍጠር ግብ ይዟል።
ኩባንያችን አገራዊ የፋይናንስ አቅምን ለማጠናከር 43.1 ቢሊዮን ብር የትርፍ ክፍፍል (Dividend) ያለመ ሲሆን፤ 83.8 ቢሊዮን ብር ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልሆነ የግብር ገቢ ለሀገራችን ለማበርከት አቅዷል።
በማኅበረሰብ ድጋፍና በጎ አድራጎት ረገድም 8.1 ቢሊዮን ብር ለብሔራዊ የአደጋ ስጋት ምላሽ ፈንድ እንዲሁም ሀገራዊ የልማት ፕሮጀክት ድጋፎችን ሳይጨምር 533 ሚሊዮን ብር ለተለያዩ የማኅበራዊ ኃላፊነት (CSR) ፕሮጀክቶች ያውላል።
በዘላቂ አረንጓዴ ኦፕሬሽን ልማት ረገድም በአረንጓዴ ኃይል አጠቃቀም፣ በካርበን ቅነሳ፣ በፋይናንስ አካታችነት እና በሳይበር ደኅንነት ላይ ትኩረት በማድረግ አገራዊ ተልዕኮውን በቁርጠኝነት ለመወጣት ይሠራል።
ለበለጠ መረጃ፡ https://bit.ly/3UvAR5j
#ethiotelecom #telebirr #nexthorizon #nationaldevelopment #csr #esg #gsma #itu

Comments