21 days ago
ብሪክስ የኢትዮጵያ ስትራቴጂካዊ የዲፕሎማሲ ከፍታ እና አዲሱ የኃይል ሚዛን
#brics #bricsethiopia #abiyahmed #multipolarworld
" target="_blank" class="inline-link">https://new-en.yenevibe.co...

24 days ago
የኢትዮጵያ ታሪካዊ የዲፕሎማሲ ምዕራፍ ከታዛቢነት ወደ አጀንዳ ሰጪነት
*************************
በዓለም አቀፍ ፖለቲካና ኢኮኖሚ ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት ወዲህ ላለፉት ዘመናት አንድ ወገን ብቻ ይመራ የነበረው “ባለ አንድ ማዕከል” የኃይል ሚዛን አሁን በከፍተኛ ፍጥነት ወደ ባለ ብዙ ማዕከላት እሳቤ እየተቀየረ ይገኛል።
አዳዲስ የኢኮኖሚና የፖለቲካ ኃይሎች በዓለም አቀፍ መድረክ ጎልተው እየወጡ ባሉበት በዚህ ታሪካዊ ወቅት፣ ኢትዮጵያ በውጭ ግንኙነቷ ተመልካችና ውሳኔ ተቀባይ ሆና ከመቀጠል ይልቅ ንቁ ተሳታፊና የኖረ ዓለም አቀፋዊ የመሪነት ሚናዋን እንደገና እያደሰች ትገኛለች።
ይህንን የዓለም አቀፍ ሥርዓት መዋቅራዊ ለውጥ በግልጽ የሚያሳየው ታሪካዊ ክስተት ኢትዮጵያ የብሪክስ ሙሉ አባል ሆና በይፋ የተቀላቀለችበት ታኅሣሥ 22ቀን 2016 ዓ.ም ነው።
ይህም የሀገራችን ዲፕሎማሲያዊ ጉዞ አዲስ ምዕራፍ ላይ እንዳደረሰው ይታመናል። ኢትዮጵያ የብሪክስ ስብስብ አባል እንድትሆን የቀረበላት ጥሪ እና ሙሉ አባልነቷን ማረጋገጧ በተለመዱ የዲፕሎማሲ አካሄድ የተገኘ ውጤት አይደለም።
ይልቁንም ሀገራችን በምስራቅ አፍሪካ ያላትን የጂኦ-ፖለቲካዊ ክብደት፣ የሕዝብ ቁጥር ዕድገት፣ የኢኮኖሚ አቅም እና የታሪክ ባለቤትነቷን በዓለም አቀፍ ደረጃ ያስመሰከረችበት አጋጣሚ ነው።
ከዓለም ሕዝብ ቁጥር፣ አጠቃላይ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ (GDP) እና የተፈጥሮ ሀብት ከፍተኛውን ድርሻ ከሚይዙት ታዳጊ ሀገራት ጋር በጋራ መሰለፍ፣ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የፋይናንስና የንግድ ሥርዓት ውስጥ ያላትን የመደራደር አቅም በእጅጉ ያሳድገዋል።
ኢትዮጵያ የሊግ ኦፍ ኔሽንስ፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት እና የአፍሪካ አንድነት ድርጅት የአሁኑ አፍሪካ ሕብረት መስራች በመሆን በታሪክ የሚታወቅ የባለብዙ ወገን ዲፕሎማሲ ተሟጋች በመሆኗ፣ የብሪክስ አባልነቷም ይህንኑ ታሪካዊ መርህ በዘመናዊ መልኩ የማስቀጠል አካል ነው።
ይህም ታዳጊ ሀገራት እንደ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ድርጅትና የዓለም ባንክ ያሉ ዓለም አቀፍ ተቋማት በቂ ድምፅና ውክልና እንዲኖራቸው በሚደረገው ጥረት ውስጥ ኢትዮጵያ ግንባር ቀደም ተሳታፊ እንድትሆን ያደርጋታል።
በብሪክስ ስር የሚገኘው “አዲሱ የልማት ባንክ” ለኢትዮጵያ የመሠረተ ልማትና የልማት ፕሮጀክቶች ተጨማሪ የፋይናንስ ምንጭ በመሆን ከፖለቲካዊ መስፈርቶች ነፃ የሆነ አማራጭ ያቀርባል።
የብሪክስ አባልነት ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በርካታ በሮችን የሚከፍት ሲሆን፤ እንደ ቻይና፣ ሕንድ፣ ብራዚል እና ሩሲያ ካሉ የቡድኑ አባላት የሚመጣውን የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት በከፍተኛ ደረጃ የመሳብ ዕድል ይፈጥራል።
የኢትዮጵያ ምርቶች ወደ ታላላቅ የዓለም ገበያዎች ያለ ምንም ገደብ እንዲገቡና የሀገር ውስጥ የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ እንዲነቃቃም ትልቅ ዕድል የሚፈጥር ሲሆን፣ በኢንዱስትሪ፣ በዲጂታል ኢኮኖሚ፣ በታዳሽ ኃይል እና በግብርና ዘርፍ የቴክኖሎጂ ሽግግርን ያፋጥናል።
ኢትዮጵያ ብሪክስን መቀላቀሏ ከምዕራባውያን ወዳጆቿ ጋር ያላትን ግንኙነት ማቋረጥ ወይም መተው ማለት አይደለም።
ይልቁንም ሀገራችን ከምዕራቡም ሆነ ከምስራቁ ዓለም ጋር የጋራ ጥቅምን መሠረት ያደረገ የተመጣጠነ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲን የመከተል ብስለቷን ያሳያል።
ይህ አካሄድ ኢትዮጵያ በማንኛውም ወገን ጥገኛ ሳትሆን ብሔራዊ ጥቅሟን በብቃት እንድታስከብርም ያስችላታል።
ዓለም ወደ አዲስ ባለ ብዙ ማዕከል አወቃቀር በምትሸጋገርበት በዚህ ወቅት፣ ኢትዮጵያ የአፍሪካን ድምፅ በማስተጋባት የደቡብ-ደቡብ ትብብርን በማጠናከር እና የራሷን ብሔራዊ ጥቅም በማስከበር ረገድ ቁልፍ ሚናዋን መጫወቷን ትቀጥላለች።
በአድማሱ አራጋው
#brics #ethiopiandiplomacy #multipolarworld #newdevelopmentbank #ethiopiarising

Comments