29 days ago
ወንድማማቾቹ ታረቁ!
ማሚላ እና ኪቺኒ ከ12 ዓመት በኋላ እንደገና አንድ ሆኑ
#ethiopia | በኢትዮጵያ የሙዚቃ ታሪክ በጋራ ባበረከቱት ሥራ እና በደቡብ የሙዚቃ ባህል ውስጥ ባላቸው ተወዳጅነት የሚታወቁት ድምፃውያን ማሚላ እና ኪቺኒ፣ ለ12 ዓመታት ያህል የቆየውን አለመግባባት በመተው ታርቀዋል።
እርቁ የተፈጸመው በሰይፉ ፋንታሁን 50ኛ የልደት በዓል ላይ ሲሆን፣ ሰይፉ ፋንታሁን፣ ብርሃኑ ተዘራ፣ ታደለ ሮባ እና ዘላለም ኩራባቸው ጨምሮ ሌሎች የጥበብ ሰዎች ለእርቁ መሳካት የበኩላቸውን አበርክተዋል።
ሰይፉ ፋንታሁን ሁለቱ አርቲስቶች የቆየውን ግጭት በመተው ይቅር እንዲባባሉ በማድረግ፣ በመጨረሻም እንዲቃቀፉ አድርጓል።
በዝግጅቱ ላይም ቀልድና ቁምነገር የተቀላቀለበት ድባብ ተፈጥሯል።
ሰይፉ በቀድሞው ግጭት ላይ በቀልድ መልክ፣ “በ2019 ሰይጣንን ወጋሁት” ሲል ብርሃኑ ተዘራ ደግሞ “መጣላት ያለ ነው፣ ግን መጠላላት ይቅር” ብሏል።
ታደለ ሮባም “እርቁ ከልብ ይሁን” በማለት መልዕክቱን አስተላልፏል።
በተያያዘም ሁለቱ ድምፃውያን በቅርቡ በሀዋሳ በሚካሄድ የሙዚቃ ዝግጅት ላይ እንደገና በአንድ መድረክ ላይ ለመቅረብ እንደተዘጋጁ ተገልጿል።
ከ12 ዓመታት ክርክር በኋላ የተፈጸመው ይህ እርቅ ለአድናቂዎቻቸው ታላቅ ደስታን ያመጣ ሲሆን፣ ፍቅር፣ ይቅርታ እና ወንድማማችነት ከማንኛውም አለመግባባት በላይ እንደሆኑ የሚያስታውስ መልዕክት ሆኗል።
እግዚአብሔርን ማየት መሸነፍ ነው። ይቅርታ ሲታሰብ አምላኩን ለማያይ ልብ አቀበት ነው።
ማሚላ እና ኪቺኒ
እንኳንም ተቃቀፋችሁ።
🙏 እግዚአብሔር ይመስገን!
#ethiopia #mamela #kichini #seifufantahun #ethiopianmusic #peace #love #forgiveness #artists #music
#ethiopianmusic #mamela #kichini #seifufantahun #hawassa #peace #forgiveness #getutemesgen #getu #ጌጡ #ጌጡተመስገን #addisababa

Comments